በርካታ የወዳጅነት ጥያቄ በፊስ ቡክ በኩል ከየተለያዩ ወገኖች የሚደርሰኝ ቢሆን ሁሉንም መቀበልና ማስተናገድ አልቻልኩም ። ይህን ከግምት በማስገባት በአንዛኛው የማሰራጫቸውን ትኩስ መረጃዎችና ሰሞነኛ የማለዳ ወጎች ለሁሉም እንዲዳረስ Public ለማድግ ተገድጃለሁ ! ዋና አላማዬ በአረቡ አለም ያለው ስደተኛ ድምጽ እንዲሰማ የበኩሌን እገዛ ማድረግ ነው ። ከዚህ ባለፈ ስደተኛው ለሁለንተናው መረጃ ቅርብ እንዲሆን ማደረግና በመረጃ ልውውጥ እየታገዘ የተሻለ ህይዎትን እንዲገፋ እገዛ ማድረግ ነው !
የመረጃ ቅበላዬ ከላይ ከጠቀስኩት የስደተኛው ህይዎት ባለፈ በአረቡ አለም እየሆነ ስላለው ማሳዎቅና መረጃ ማካፈል ነው ። አረቡን አለም በርቀት ለሚያወረቀው ወገን በመረጃ አቅርቤ ስለ አኗኗር ባህሉ ፣ ስለ ሐይማኖት፣ ፖለቲካና ኢኮኒሚው ሚዛናዊ የሆነ አስተማሪ መረጃን ማካፈልም ፍላጎቴ ነው ። ለዚህም የመረጃ ግብአት ይጠቅማሉ የምላቸውን መረጃዎች አቅም በፈቀደ መጠን እየሰበሰብኩ አካፍላችኋለሁ ። የወዳጅነት ጥያቄ አቅርባችሁልኝ ያልተቀበልኳችሁም ሆነ የተቀበልኳችሁ ወዳጆች ወደ ገጼ ገብታችሁ Follow ቦታ ካለ ፈግሞ Follow First ብታደርጉኝ መረጃው እንደተለጠፈ በቀጥታ በገጻችሁ ሊመጣላችሁ ይችላል ። እናም Follow ማድረጋችሁን አትርሱ ።
መረጃዎቸን ወደ ኋላ እየሄዳችሁ ተመልከቷቸው ፣ ስለ ተጨባጭ መረጃዎችን እመኑኝ ! የወዳጆቸን ቀልብ ለመሳብ ብዬም ሆነ ለክብርና ለዝና ያልሆነና የሚያጓጓ መረጃ አላስተላልፍም ። ምንጊዜም በማቀብላችሁ መረጃ ትክክለኛነት ኃላፊነትን እወስዳለሁ ። መረጃ በወደጅነት እንሰንብት !
እናም አንኳር መልዕክቴን ልድገኘው ወደ ገጼ ገብታችሁ Follow ቦታ ካለ ፈግሞ Follow First ብታደርጉኝ መረጃው እንደተለጠፈ በቀጥታ በገጻችሁ ሊመጣላችሁ ይችላል ። እናም Follow ማድረጋችሁን አትርሱ ! …Follow me , let us voice together voice of voiceless ! Let the world know the truth ! በዩ ቲዩብ Youtube እገኛለሁ https://www.youtube.com/user/nsirak09 ብላችሁ ፣ Twiteer ላይ @nsirak ብላችሁ ተከተሉኝ ፣ የስደተኛውን ድምጽ አብረን እናሰማ ፣ መንግስት ጩኸት ምሬት በደላል ምስጋናችን ይስማስ ፣ አለም እውነታችንም ይወቀው !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 17 ቀን 2009 ዓም
Average Rating