www.maledatimes.com የስብሀት ነጋ ስድብ ከበርሊን ጀርመን - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የስብሀት ነጋ ስድብ ከበርሊን ጀርመን

By   /   October 24, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 27 Second

 

ፁሁፌን ከስብሰባው ቦታ ልጀምር ቀኑ ጥቅምት 9/2/2005 አርብ ጀርመን በርሊን የጀርመን ሶሻል

ዲሞክራት ፓርቲ/ኤስፔዴ/ በጀርመን ፌድራላዊ ምክር ቤት ቡንደስታግ ባዘጋጀው ና በተካሄደው

ያፍሪካ ህብረት ውይይት ላይ ተገኝተው ነበር። በዚህም ውይይት የተሳተፉ የኢትዮጽያ ባለስልጣናት

አቶ ስብሀት ነጋና አቶ ሞገስ ተክለሚካኤል የአለም አቀፍ የሰላምና ልማት ተቐም ተወካዮች ናቸው።

በውይይቱም ሰዎስት ጉዳዮች አብይ ርእስ ነበሩ።

1ኛ// ኢትዮጽያን በተመለከተ፤ከጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ሞት በሗላ የመንግስት ፖሊሲ ይቀየራል ወይስ ይቀጥላል?

ኢትዮጽያስ ወደፊት በምን ዓይነት መንገድ ትሄዳለች?

2ኛ// በመጭው መጋቢት በኬንያ ስለሚካሄደው የሸንጎ ምርጫ ያለም አቀፉ ህብረተሰብ የሚያደርገው ተሳትፎ ምን

ምን እንደሚሆን?

3ኛ// የማሊ ጉዳይ ናቸው ።

የኢትዮጽያን መንግስት ፖሊሲ በተመለከተ አቶ ስብሀት ሲናገሩ፤>> መለስ አንድ ሰው ነው። አንድ ሰው ስለሞተ

የድርጅቱ ዓላማ አይቀየርም ! ምንም አይነት የፖሊሲ ለውጥ አይኖርም<< ሲሉ ባጭሩ አስቀምጠዋል።

ስለኢትዮጽያ የወደፊት ሁኔታ ደግሞ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል እሳቸው የሚወክሉት መንግስት>> የፊውዳል ርዝራዦች ና

የደርግ ተከታዮችን ለመቖጣጠር ብዙ ዘመን እንዳሳለፈ ና ደግሞ ደርግ ጥሎት የሄደውን ሰርአት የሌለውንና ስርአት

የማያውቀውን የኢትዮጽያ ህዝብ ስናስተምር ብዙ ብዙ ግዜ አጥፍተናል፤ አሁንም በመጨረሻ ልል የምፈልገው የኢትዮጽያ ህዝብ ለዲሞክራሲ

ብቁ አይደለም<< ብለው ተናግረው ሲጨርሱ ከስብሰባው ከታደሙ ኢትዮጽያኖች ጥያቄ ና ሁካታ ተነሳ አንድ ኢትዮጽያዊ

>>ስርአት የሌላችሁ እናንተ ናችሁ ከላይ ሆናችሁ ለህዝብ ውሸት የምትደሰኩሩ የምትሳደቡ<< ሲል ቤቱን አናግቶታል ።

ሌሎችም እንዲሁ በምርጫ 97 የሞቱና የቖሰሉ ወገኖች ፎቶ በሰፊው እያሳዩ ነበር  በዚህም ወንጀል እደኬንያ ባለስልጣናት

ለፍርድ መቅረብ አለባችሁ የሚሉ ሀይል ቃላቶች ተጀመሩ እዚህ ላይ ጀርመናዊዋ የመድረኩ አወያይ የጠየቅንው ጥያቄ

የኢትዮጽያ መንግስት ፖሊሲ ይቀየራል አይቀየርም ነበር ሆኖም በዙም አልሰማንም ብለው ያጣጣሉት ሲሆን፤ ስብሰባውን

ያዘገጋጀው የሰባዊ ኮሚቴ በሸንጎ ውስጥ ተወካይ የሆኑት የሶሻል ዲሞክራት ተጠሪ ሚስተር ክርስቶፍ እስትራሸር>> በሌላ ግዜ

የኢትዮጽያ መንግስትንና ተቃዋሚዎችን የሚያወያይ መድረክ እናዘጋጃለን በዚህ ግዜ ለማለት ግን አንችልም<< በማለት ሁከቱን

ለማርገብ የፈለጉ ይመስላል።

ከዚህ በታች የራሴን አስተያየት እሰጣለሁ ! እናንተስ ምን ትላላችሁ?

የወያኔን አገባብ አሁን ለይ ሆኛ ሳየው እኔም ከተሳተፍኩበት አንፃር መለቴ ወያኔ አልነበርኩም ግን ደግፌአለሁ ደርግ እንዲወድቅ

ከመፈለግ አንፃር ለወያኔ አጨብጭቤአለሁ፤ ጮኬአለሁ፤ ተከራክሬአለሁ ታዲያ ምን ያደርጋል አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቸ መጣ

ብሏል ቴዲ አፍሮ እንደኔ ቢጨንቀው እሱ እንኳ በዘፈኑ ተንፍሶል እኔ እንዴት ልተንፍስ እል ነበር !

የሆኖ ሆኖ ግን ከሁለት ወር ግድም ለመለስ ያለቀሱትን ጥቅመኞች ህዝብ እንዳለቀሰ በማስመሰል ጨዋና የሰለጠነ ህዝብ

ሲሉት የነበረው አሁን ግን እዚህ ለዲሞክራሲና ለስልጣኔ ብቁ አይደለም ያሉት ተምታቶባቸው ሳይሆን በትክክል ውሾች

እዳለቀሱ ይገባኛል፤ህዝቡም እንዳላለቀሰላቸው አቶ ስብሀት የመሰከሩ ይመስለኛል።

ሌላው የኢትዮጽያ ህዝብ ስልጡን እንደሆነና ስነስርአት የሚየውቅ የዲሞክራሲ ነፃነቱን የሚናፍቅ መሆኑን ካሁን ልጀምርላቸው

ከሗላ መቸም ስለማያውቁት የኢትዮጽያ ህዝብ  ስርአት፤የተጋድሎ ታሪክ አልነግራቸውም። ከሳቸው ዘመን ልጀምርላቸው እንጂ፤

ለአቶ ስብሀት!

1. ለመሆኑ እናንተ ስትገቡ የደርግን ስርአት ለመጣል ከፊትም ከሗላም ይህ ህዝብ አልተሰለፈም? ቤት የዋሉ አዛውንቶች ሳይቀሩ

እልል አላሉም ታዲያ ይህ የስልጣኔ መገለጫ የዲሞክራሲ ነፃነት ፍላጎት ነፀብራቅ አልነበረም?  ያለመንግስትስ ላልተወሰነ ቀን

ያለምንም ችግር መቖየቱ ስርአት የሌለው ስለሆነ ነው?

2. በምርጫ 97 አለም ጉድ ያለበት የውሸት ምርጫችሁ እንደዚያ በነቂስ ወጥቶ በስርአት መምረጡ ለዲሞክራሲ ብቁ ስላልነበረ

ነው ?

3. አሁንስ ምንም ልታደርጉት ያልቻላችሁት የሙስሊም ኢትዮጽያኖች ተቃውሞና ሰልፍ ለይ የሚያዩት ስርአት ና ዲሞክራሲያዊ  ጥያቄ የኢትዮጽያኖች ስርአት ከናንተ አቅም በላይ የሆነ ስለሆነ ንግግርዎት የተስፋ መቁረጥ ንግግር ያስመሰለብዎት ይመስለኛል።

በመፀሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ የጌታ ቃል አለ << ሀጢያታቸውን ይቅር ባልኳቸውና በታገስኳቸው መጠን የለም አሉኝ<<

ስለዚህ አቶ ስብሀት ካለፉት ታሪኮች እርሶና መሰለችዎ መማር ስላልቻላችሁ የምትሰድቡት ህዝብ አነድ ቀን መልስ ይሰጣችሓል።

Kidane Gebregziabher

Germen

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 24, 2012 @ 11:35 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “የስብሀት ነጋ ስድብ ከበርሊን ጀርመን

  1. አንዳንዴ እኛ እትዮጵያኖች አንድ ሰው የሚለውን ውይም የሚናገረውን ከመተንተንና ለምን እንዲህ ሊል ቻለ፤ ምንስ አይቶ ነው፣ ምንስ ሊያስተምረን ነው እንዲህ ያለው ብለን ከማመዛዘን ይልቅ ቁጣና ስድብ ማውረድ ልማዳችን ነው። በ እኔ አስተያየት ይሄ ጠባያችን ነው እድሜ ልካችንን በአምባ ገነን ንጉሶችና ስልጣን በጨበጠ ውርጋጥ ስንገዛ የኖርነው። ምን ቀን አብረን አድመን እድማችንን እስከ መጨረሻው አድርሰን መንግስት የገለበጥነው። እኔ የማውቀው አብረን አድመን ግብ ልናደርስ ጥቂት ሰዓት ሲቀረን ከውስጣችን አንዱ ሸጦን ሁላችንንም እዳ ያገባናል። አቦይ ሰብሃት እውነቱ ነው፤ እኛ ኢትዮጵያኖች ዲሞክራሲ ምን ማለት መሆኑን ካወቅን በጣም ቆይተናል፤ ዲሞክራሲ ያለበትም አገር ብዙወቻችን ተምረናል፡ ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሃገርም እንደሚበለጽግ እናውቃለን፤ ግን ዲሞክራሲን ለማግኘት ምንና ምን ማድረግ እንዳለብን የምናውቅ አይመስለኝም። እኛ እትዮጵያኖች የምናውቀው ሰው ክበላያችን ክሚሆን ሌላ የማናውቀው አንቀጥቅጦ እንዲገዛንና እንዲያላግጥብን እንወዳለን። አቦይ ስብሃትም ይሄን ጠባያችንን አውቆ ነው የሚሰድበን፤ በጃነሆይ ጊዜ ስንት ግልበጣ ነው የከሸፈው፡
    መንግስቱ ሲገዛን ማነው አንገዛም በቃን ብሎ አብሮ ተመካክሮ ሊገለብጥ የሞከረ። የገዛ ጓደኞቻችን አየር ሃይሎችና አንዳንድ የጦር ሃይል መኮንኖች አብረው ተመካክረው ለሃገር ይጠቅማል የመንግስቱ አካሄድ አገሪቱን በደለ፤ ያለ አቅሙ ክ አሜሪካ ጋር ግብ ግብ ይዞ ተው ቢባል አልሰማም አለ ብለው ተማምለው ሳለ የገዛ ጓደኛቸው አብሮ ያደመ ሄዶ ሽጦ አስጨረሳቸው። ያ ኩዴታ ቢሳካ ኖሮ አሜሪካ ወደ እነ መሰለ ዞሮ በሽፍታ ዉርጋጥ አያስገዛንም ነበር። እንድ ሰብሃት ያለ የ አረቂ ቤት ሰካራም አይገዛንም ነበር። 21 ዓመት ሙሉ በአንድ ዉርጋጥ ስንገዛ ማነው በቃን አንገዛም ብለን በረሃ የገባን። ለመሆኑስ አሁን ያለው መንግስት ነገ ጥሎ ቢሄድ የትኛው ፓርቲ ነው የሚተካቸው። አለ የሚባለው ፓርት እርስበርሱ ተበላልቶ በዱላ እንደሚፈረካከስ አልጠራጠርም፤ ብታምኑም ባታምኑም ኢትዮጵያኖች እርስ በራሳችን እንኳ አንተማመን፡
    እርስ በርሱ የማይተማመንና የማይከባበር ህዝብ ዘላለም በባእድ ሲተዳድረ ይኖራል።

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar