” የሳውዲ ምህረት አዋጅ ተስፋና ስጋት ! “
============================
ከኮከቧ ወጣት አንጋፋ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ ከጽዮን ግርማ ጋር ነገ በሚጠናቀቀው የሳውዲ የምህረት አዋጅ ተስፋና ስጋት ዙሪያ ያደረግነውን ሞቅ ያለ ውይይት ተጋበዙ 🙂 አድምጡት ፣ ሳንናገረው የቀረ ካለ አስተያየት ስጡበት ፣ የጠፋነው ካለም አርሙት በውይይቱ ላይ ” የምህረት አዋጁ ይራዘማል ወይስ አይራዘ ምም ?” በሚለውና በመፍትሔ ሀሳቡ ዙሪያ ከወዳጄ ከጋዜጠኛ ስለሽ ጋር በሀሳብ እንለያያለን ። በምህረት አዋጁ መራዘም ዙሪያ እኔ የምህረት አዋጁ ይራዘማል በሚለው የጸና እምነት አለኝ ። እሱ አይራዘምም ባይ ነው ! ስደቱን ለማስቆምበተሰጠው የመፍትሔ ሀሳብም ዙሪያ በእኔ እምነት በድህነት የተደቆሰን ማህበረስብ ፣ ተምሮ ስራ ያጣ በሚሊዮን የሚቆጠር ወጣት ዜጋ ስደትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ በያዘበት ሀገር ብቸኛ መፍትሔ አይገኝም እላለሁ ። በሀገራችን ሁኔታ ስደቱን ለማስቆም ካሉት አማራጮች መካከል ዜጎች ወደ አረብ ሀገራት ለስራ የሚሰማ ሩባቸውን ስምምነቶች በጥሩ ደመወዝና ጥቅማጥቅም አስጠብቆ መደራደር ከመፍትሔዎች አንዱ ነው ። ከሀገራት ጋር የሚደረገው ድርድር ህዝቡ የማወቅ መብት አለው ፣ ድርድሩና ስምምነቱ ለህዝቡ መደበቅ የለበትም ፣ ግልጽ መሆን ይገባዋልም እላለሁ!
ሌላው ዋንኛ መፍትሔ የምለው በምንም መንገድ የተሰደደውን ዜጋ ሰብአዊ መብት ማስከበር ነው ። ይህን ሁሉ ለማድረግ ደግሞ የፖለተካ ሹመኛ ሳይሆን የእውነት ክህሎት ያለው ተቆርቋ ሪ በቂ የመብት አስከባሪ ዲፕሎማት በየአረብ ሀገራት በማሰማ ራት ነው ። ከላይ ያስቀምጥኳቸው መፍትሔዎች በቀላሉ ሊተገበ ሩ የሚችሉ ናቸው ብየ አምናለሁ ። በዚህም ላይ መነጋገር መወያየትና ሀሳብ መስጠት ይቻላል ።
ለማንኛውም ከውይይቱ የቀረው ሀሳቤን አካፍያችኋለሁ ፣ በዚህም በኩል ሀሳባችሁን ስጡ ! በዋናነት ግን ከጋዜጠኛ ጽዮን ጋር እኔና ስለሽ ያደረግነውን ውይይት አድምጡት ፣ ሳንናገረው የቀረ ካለ አስተያየት ስጡበት ፣ ያጠፋነው ካለም አርሙት ! ሰላም ለእናንተ ይሁን !
ቸር ይግጠመን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 17 ቀን 2009 ዓም
Average Rating