www.maledatimes.com የማለዳ ወግ … ከዛሬው የስጋት ማጥ የከተተን መንገድ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ … ከዛሬው የስጋት ማጥ የከተተን መንገድ !

By   /   June 27, 2017  /   Comments Off on የማለዳ ወግ … ከዛሬው የስጋት ማጥ የከተተን መንገድ !

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 26 Second

==============================
* እመኑኝ …የተጎዱዳነው አረቦች ከፍተውብን አይደለም …
* የተጋረጠውን ስጋት በተባበር የመረጃ ቅበላ መመከት ይቻላል
* ሁለቱ አንኳር መልዕክቶች …
* መረጃየን ከፖለቲካ፤ ከዘርና ከሃይማኖት ጋር አታነካኩት

እመኑኝ …
=======
እመኑኝ … ነገን ከዛሬ እንማርበት ዘንድ ፤ ስጋት መከራው ይቀልልን ዘንድ የሚያገባን እንናገራለን ፤ እንመካከራለን እመኑኝ … እዚህ ያደረሰ መንገድ የግል ተመክሮየን ላካፍላችሁ !እመኑኝ … የጎዱን አረቦች ከፍተውብን አይደለም ። እመኑኝ … አረቦች ከሀገራቸው መንግስ በላይ ሆነው ፤ ሰብአዊ መብታችን ጥሰውት ፤ ወደ ፍትህ አካላት አቅርበናቸው ፤ ፍትህ ተነፍጎን ፤ ፍትህ ርቆን አላየሁም ፤ አልሰማሁም !እናም እመኑኝ … የጎዱን አረቦች አይደሉም !

እመኑኝ …የጎዳን እራሳችን በራሳችን ነን …እመኑኝ ከዛሬው ስጋት ማጥ የከተተን መንገድ ይታወቅ ነበር … ይነገር ነበር … የጎዳን የዜጎቹን ድምጽ የማይሰማን መንግስት ነው … የጎዳን በአደባባይ የሚቀርበውን እውነት ትቶ ሹሞቹን ብቻ የሚሰማው መንግስታችን ነው የጎዳን … ከሁሉም በላይ የጎዳን ከቤተሰብ እስክ ማህበረሰብ ፤ ከአረብ ሀገር ኤጀንሲ እስከ ሀገር ቤት ደላላ ፤ ከቀበሌ እስከ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እህቶቻችን የሚደርስባቸውን ግፍና ስለሚሰራው ስራ ተበዳይ እማኝ ይዘን የምንመክር የምንዘክር ዜጎችን የማይሰሙን ፤ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ የመብት አስጠባቂ ሁነኛ ተወካይ ዲፕሎማቶች ነው የጎጉን … መብት አስከባሪ ሁነኛ ተከራካሪ ሁነኛ ተወካይ ዲፕሎማቶች አጥተን ስደቱን አከፍቶብናል ! እውነቱ ይህ ሆነና የዛሬ የሳውዲ የምህረት አዋጅ ሲገባደድ መጭ ስጋቱ አድጓል ። ስጋቱ ደግሞ ከግማሽ ሚሊዮን የማያንሰው በሳውዲ ስደተኛ ብቻ አይደለም ። በሚሊዮን የሚቆጠር ቤተሰብ ፤ ዘመድ አዝማድና ፤ ጎረቤት የሀገርና የመንግስት ጭምር ስጋት ሆኖ ሀገር ምድሩ ሰለ ሳውዲ መምከር መነጋገሩ ጉዳቱ በተዘዋዋሪም ቢሆን ያልሰሙን ተወካዮቻችን ያመጡብን ጣጣ ነው !ሁነኛ ተቆርቋሪ መንግስት ቢኖረን ዛሬ የምናዎራው ምናልባትም ቢበዛ እስከ 10 ሽህ የሚደርሱ ህገ ወጥ ዜጎች በሆነ ነበር !ዳሩ ግና ያ ህልም ሆኗል :( እናም ዛሬም ጉዳያችን ነውና እንወያያለን!

ከአድማስ ራዲዮ ጋር ተወያየን …
==================
በሀገረ አሜሪካ አትላንታ የሚገኘው አድማስ ራዲዮ ተዋዳጅ አዘጋጅጋዜጠኛ ከቴዎድሮድ ደጌ ጋር በምህረት አዋጁ ማብቂያ ዋዜማ ለሃያ ደቂቃ ያህል ተወያየን ። የስደተኛው እንግልት ፤ ተስፋውና ስጋቱ ምን ይመስላል ? ምን ይከሰታል ብለን እንጠብቅ ? የሚለው ከቴዲ ጋር ባደረግኩት የቀጥታ ስርጭት ቃለ ምልልስ ለአድማጮች ግንዛቤ ለመስጠት ሞክሬያለሁ ። ባሳለፍናቸው ሁለት ሳምንታት እንዳደረግኳቸ ቃለ መጠይቆች ይህንንም ደፍሬ መደመጥ ያለበት ውይይት እንደሆነ እመክራለሁ፤ ፈቃድዎ ከሆነ ያድምጡት ። ላላዳመጠ መረጃውን ያሰራጩት፤ የወገናው ጉዳይ ለሚያገባቸው ፤ መፍትሔ መስጠት ለሚችሉት ለሚመለከታቸው ሁሉ በማዳረስ የወገንዎን እንግልትና በደል መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የዜግነት ድርሻዎን ይዎጡ !

ሁለቱ አንኳር መልዕክቶች …
================
1) መረጃዬ ለመፍትሔ ነው
ከብርሃን ፍጥነት መሳ ለመሳ በሚሾረው የመረጃ ቅብብል በአረቡ አለም የሚገኙ ስደተኛ ወገኖቻችንን የተዳፈነ ያልተሰማ ድምጽ በማሰማት የማቀብልዎ መረጃ የራስን ክብርን ከፍ ለማድረግ ፤ ለመታወቅና ለተያያዥ ጥቅማ ጥቅምን ለመቃረም እንዳልሆነ ከሁሉ አስቀድመው ይረዱልኝ ዘንድ እማጸንዎታለሁ ። ዋና አላማዬ በምኖርበት ከባቢ በቅርበት የማየውን ስደተኛ ወገን መከራ እንዲያቆም በመረጃ ቅብብሉ መፍትሔ ማፈላለግ ነው !መነሻና መድረሻ ይህው ነው !

2)መረጃየን መሰረቱ ሰብዕና ነው
መረጃዎቸ ሰብአዊነትን መሰረት ያደረጉ ናቸው እንጅ ዘር ፤ ፖለቲካና ሃይማኖትን አይወግኑም ። ከሁሉም ነጻ ሆኘ መረጃ ሳቀብል ወገኔን ከገጠመው የስደት እንግልት ለመታደግ እንጅ የሹሞችን ስራ ላራክስ አይደለም ። በተቀመጡበት የከበደ የሃገርና የህዝብ ኃላፊነት የተቀመጡት ሹሞች ለተገፊው መብት ማስከበር ቀናኢ ሆነው ሳይሰሩበት ስመለከት በመረጃ ማስረጃ ግፍና በደሉን ነቅሸ እያወጣሁ መብት ማስከበሩ እንዲሻሻል የበኩሌን ድርሻ ለመወጣት የምተካ ባተሌ ነኝ !

እንደኔ እንደኔ ከጥላቻ የወጣና በሰብእና የተቃኘ ትክክለኛ መረጃን በመቀባበል በአሁኑ ሰአት በሳውዲው ስደተኛ የተጋረጠበትን የአደጋ ስጋት መመከት ይቻል ይመስለኛ ። ያን ማድረግ የሚቻለን ግን በዘርና በሃይማኖት ሳንለይ በመተባበር ብቻ ነው ። መረጃውን ከፖለቲካ ፤ ከዘርና ከሃይማኖት ጋር ሳናነካካ ከተጠቀምንበት በስጋት አደጋ ማጥ የገባውን ስደተኛ መታደግ አይገደንም !ውይይቱን በዚህ መንፈስ ታደምጡልኝ ዘንድ እማጸናችኋለሁ !አንኳር መልዕክቴም ይህው ነው !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 27, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 27, 2017 @ 1:02 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar