www.maledatimes.com የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት – * ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት * ቅጅ /ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት – * ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት  * ቅጅ /ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ 

By   /   June 28, 2017  /   Comments Off on የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት – * ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት  * ቅጅ /ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ 

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 43 Second
የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት
==============================
* ለአንባሳደር አሚንና ለአንባሳደር ውብሸት ባላችሁበት
* ቅጅ /ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ
     መረጃን ማቀበሌ ወንጀል ሆኖ ” የነቢዩ ሲራክ ልጆች ከሚማሩበት የጅዳ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲታገዱ ” የሚለው የካድሬዎች ሀሳብ ያን ሰሞን ቀርቦ እንደነበር በድጋሜ በማረጋገጤ አዝኘ ነበር ያደርኩት ።  … ስለ እውነት ለመናገር ፣ ስለ እውነት እየተገፉ መኖር ግድ ይላል ብዬ የሚሰራው ባይደንቀኝም በዘመነ ኦሪት እንኳ ባልታዬ ህግ ልጆች በአባታቸው ” ወንጀል ” ስማቸው ሲጠራ መስማት ልቤን በሀዘን ሰብሮት አድሯል  🙁 እናም ሁሉንም ለመርሳት ልጆቸን እረፍት ወደ ማይሰማ ወደ ማይናገረው ቀይ ባህር ይዣቸው ዘና ልበል ብዬ ማልጀ ስነሳ ሌላ አሳዛኝ መረጃ ደረሰኝ ። መረጃው እንዲደርሰኝ ያደረገው ደግሞ አንድ አደር ባይ ወዳጄ ነበር ፣ ወዳጄን እኔን ያመመኝ አሞት ስለማያውቅ የዜጎች ጉዳይ አግብቶኝ የተገፊውን ድምጽ ሳሰማ ” ሥራ ፈት ነህ  !” እያለ ያላግጥብኝ ነበር። ዛሬ ግን የራሱ የሆነች እህት በሪያድ አየር መንገድ ለቀናት በደረሰባት እንግልት ተደናግጦ” አገር ይያዝ” ጩኸት አሰማኝ  ። ቀጠለና ዜጎች እየተሰቃዩ ነው የታላችሁ በማለት ከጅዳ ቆንስል እስከ ሪያድ ኢንባሲ ሹም ወዳጆቹን ጨምሮ መረጃውን እኔው ጋር አድርሶታልና አዘንኩ … ደጋግሞ ሲደውልልኝና መረጃ ሲሰጠኝ ዝም ብየ ሰማሁትና ለመሆኑ እኔ ስናገር ሥራ ፈት እያልክ  አልነበር?  ዛሬ ችግሩ በዘመድህ መጥቶ መናገር መናደድ ጀመርክ?   እስከ አሁንስ የት ነበርክ ? ማለቴ አልቀርም ። እሱ ግን አፈረ ፣ እኔም  ያፈረውን አድርባይ  ወዳጄን መጎሻሸሙን አልወደድኩትም …በወዳጄ ዛሬ መቆርቆር አላዘንኩም የሰጠኝን መረጃ ተከትዬ ያሰባሰብኩት እውነት ግን በእርግጥም ያስከፋል ። ይህን መልዕክት እንድጽፍ ላችሁ ያነሳሳኝ ጉዳይም ይኸው የደረሰኝ መረጃ ነው ።
  ላለፉት ሶስት ወራት ሌት ተቀን ግሩም በሆነ ዝግጅት የከረመው የኢንባሲና የቆንስል መረጃ ቅበላ በመቋረጡ የተከተለውን ውዥንብር እንደ ዜጋ ታዝቤያለሁ ። የኢንባሲና የቆንስል መረጃ ቅበላ በማቆሙም ቦታውን ባልተካም በመረጃ እጦት ስደተኛው እንዳይንገላታ ባሳለፍናቸው ሁለት ሳምንታት የምችለው ለማድረግ ሞክሬያለሁ ። አሁንም የምቀጥለው በዚሁ መንፈስ ነው  … የኢንባሲና የቆንስል ለመረጃ የተዘጋው በር ከተከፈተ እኔ ብዙም ላይክና ሸር ፈላጌ ዝር ላልል ቃል ልግባላችሁ  ! ብቻ ለዜጋው መረጃ ያስፈልገዋልና የተዘጋውን በር ክፈቱለት ለማለት  ለመማጸንና ለመምከርም ጭምር ነው ።
   በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ችግር በጅዳና በሪያድ አየር መንገዶች እየተንገላታ ያለው ሰው ለቅሶ ዛሬም ደርሶኛል ። በምህረት አዋጁ መራዘም ዙሪያ በሚናፈሰው መረጃ ለሚዋልለው ዜጋ እያደረጋችሁ ያለውን ጥረትና እውነቱን አስረዱት ።  ”  የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል !” ተብሎ በሳውዲ ፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ መመለስ ስለመጀመሩ ጉዳይ ግልጽ መረጃ ከእናንተ ይጠበቃል ።  ከቀናት በፊት በጀዛን ትናንት ደግሞ በጅዳ አንዳንድ ተመላሾች ” የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል !” ተብለው በፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ ተከልክለው እንደነበር ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች በግል መረጃውን አረጋግጫለሁ። በዚህና በዚያ  በተለያዬ አቅጣጫ የሚሰማው መረጃ ብዙዎችን ግራ እያጋባ ይገኛል ።
     በሚሰራጩት መረጃዎች ፣ እየተደረገ ስላለው ጥረትና  ተዛማጅ የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ በሳውዲ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በምህረት አዋጁ ወቅት ያደርጉት እንደነበረው ሳያቋርጡ መረጃን ሊሰጡ ይገባል የሚለው የብዙ ወዳጅ ተከታዮቸ መልዕክት ነው ። በእርግጥም ወቅታዊ መረጃን ሲሰጡ ከርሞ አሁን በወሳኙ ጊዜ ማቋረጥ  በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ዜጋ ብቻ ሳይሆን በመላ አለም ያለው ሚሊዮን ሀገር ወዳድ እንዳይረጋጋ ያደርጋል ። በውል የተጠና የመረጃ ቅበላው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ እና የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በወሳኙ ጊዜ ያቋረጣችሁትን የመረጃ ቅበላ ትቀጥሉ ዘንድ እመክራለሁ  !  በየአየር ማረፊያዎች ቀንና ማታ ቀርቶ ለሰአታት መቋቋም በሚከብደው ደረቅ ሀሩር ጸሃይ ሙቀት እየተለበለበ ያለው ወገን ያለበትን ሁኔታ መከታተልና መደገፍ ፣  መረጃ ፣ ማብራሪያ በሉት ምክር ካስፈለገ በቦታው እየተገኙ መስጠት ተገቢ ነው እላለሁ !
  ይህን ምክር እንድጽፍ ያነሳሳኝ መታበይ እንዳይመስላችሁ ። በቂ ምክንያት አለኝ  ” ላለፉት ሶስት ቀናትበሪያድ አየር መንገድ አውላላ ሜዳ ላይ ተሰቃየን ” በሚል የሚደርሱኝ መረጃዎች እጅግ  ውስጥን ይረብሻሉ  🙁  እናንተም በዚህ ዙሪያ ምንም አይነት ወቅታዊ መረጃ ስለማታቀርቡ በእንግልት ላይ ያሉ ዜጎች  የመረጃ እጦት ሌላ ፈተና እንደሆነባቸው መረዳት ችያለሁ ! እባካችሁ ዜጎች መረጃን  ከእናንተ ከህዝብና መንግስት አገልጋዮች የማግኘት መብታቸውን አለንና እሱኑ መብት አክብሩልን   !
የግርጌ ማስታወሻ
====∞===== = ለወዳጆቸና ለተካታታዮቸ ፣ ይህ መልዕክት ለኃላፊዎች እንዲደርስ Share እና Like ማደረጋችሁን አትዘንጉ ፣ ሁላችንም  ስለተገፉት ዜጎች ድምጽ መሰማትና መፍትሔ ማግኘት መትጋት ግድ ይለናል  !
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 21 ቀን 2009 ዓም
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 28, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 28, 2017 @ 11:12 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar