www.maledatimes.com መንግስት በመምህራን ላይ የበቀል በትሩን አሳረፈ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መንግስት በመምህራን ላይ የበቀል በትሩን አሳረፈ

By   /   October 24, 2012  /   Comments Off on መንግስት በመምህራን ላይ የበቀል በትሩን አሳረፈ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 33 Second

ባለፈው አመት የመጋቢት ወር ለመምህራን ተጨምሯል ከተባለው የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ስራ የማቆም ውሳኔ ማሳለፋቸውና ይህንኑ
መተግበራቸው አይዘነጋም፡፡ መንግስት አስተማሪዎቹን አነሳስተዋል ካላቸው መምህራን ውስጥ ስድስት ያህሉን ከስራ ገበታቸው በማፈናቀል ለሚበዙት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡ በያዝነው አመት መጀመሪያ ላይ ለአምስት
ቀናት የትምህርት ጥራት ፓኬጅን በማስመልከት ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡
በውይይቱ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ አስተማሪዎች ወደ ስራቸው ከተመለሱ ጥቂት ቀናት በኋላ ያልጠበቁት ነገር እንደገጠማቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈቀዱት መምህራን ይናገራሉ፡፡ 120 የሚደርሱ ነባር መምህራን ያለ ፍላጎታቸውና ያለ ማህበራቸው ተሳትፎ ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እንዲዘዋወሩ ተደርገዋል፡፡ የዝውውራቸውን ምክንያት በመግለጽ የደረሳቸው አንድ ገጽ ወረቀት ዝውውሩ “ለተሻለ ስራና አገልግሎታቸውን ለማቃናት” ስለመሆኑ የምትገልጽ ናት፡
፡ ነገር ግን በዝውውሩ ውስጥ እንዲካተቱ የተደረጉ መምህራን በመጀመሪያ በነበሩባቸው ትምህርት ቤቶች ከተማሪዎቻቸው ጋር ጥሩ ግኑኝነት የመሰረቱና የመማር ማስተማሩ ሂደት የተሳካ እንዲሆን ባበርከቱት አስተዋእጾ
በየጊዜው የምስጋና እና የምስክር ወረቀቶች የተሰጣቸው ናቸው፡፡ መምህራኑ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያስተምሩ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ዝውውር ከደረጃቸው ዝቅ ተደርገው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲያስተምሩ ተደርገዋል፡፡ ዝውውሩ በትምህርት ሚኒስትርና በመምህራን የውስጥ ደንብ መሠረት የተከናወነ አለመሆኑን የሚያወሱት መምህራኑ “አንድ መምህር ከአንድ ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ሊዘዋወር የሚችለው በመምህሩ ጥያቄ፣ ከሚሰራበት ትምህርት ቤት ጋር በመነጋገርና በመምህራን ማህበሩ እውቅና ነው፡፡ነገር ግን የአሁኑ ዝውውር ያለ መምህሩ ጠያቂነትና ያለ ምንም አይነት ምክክር የተደረገ በመሆኑ ህገወጥ ነው” ይላሉ፡፡
በ2004 ለመምህራኑ የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ተደርጓል መባሉን በመቃወም ድምጻቸውን አሰምተው ከነበሩ የኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት መምህራን መካከል 10ሩ እንዲሁም በወንድራድ ትምህርት ቤት የመብት ጥያቄ
ካነሱ መምህራን አራቱ በዝውውሩ ከቦታቸው በመነሳታቸው ለተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ ተዳርገዋል፡፡ ዝውውሩን የበቀል እርምጃ በማድረግ እንደሚመለከቱት የሚጠቅሱት መምህራኑ ለሚመለከተው አካል ቢያመለክቱም ከዚህ የከፋ ነገር ሊደርስባቸው እንደሚችል እንደተነገራቸው በሀዘን ስሜት ይጠቅሳሉ፡፡

ፍኖተ ነጻነት

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 24, 2012 @ 11:38 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar