ንግስት ጣይቱ ስም አውጥተውላት የቆረቆሯትን ዋና ከተማም ስሟ ሲቀየር እያያችሁ ዛሬም የኢትዮጵያ አቅጣጫ አይታየንም ማለት ይከብዳል። አሁን የሆነውን የአዲስ አበባ ጉዳይ በራሱ እንኳን መልስ ካልሰጠን ከዚህ በፊት ከሆኑት ጋረ እና እየሆኑ ካሉት ነገሮች ጋር አብረን በማየት የበለጠ ግልጽ የሆነ መልዕክት ሊሰጠን ይገባል።
ወያኔ በኦሮሞ ከንቲባዎችና ባለስልጣኖች እጅ ነው ላለፉት 25ዓመታት ሶሻል ኢንጂነርጋቸውን በአዲስ አበባ ላይ ሲሰሩ የነበረው ፦ እንግዲ የትግሬ እና የኦሮሞ ብሄርተኞች የጋራ ሃገር መገንባት ከሆነ አላማቸው ለምን የዘር ግዛት አበጁ?የራሳችን(ሃገር በቀል)ፌደል እያለ ለምን የሰው ፊደል መጠቀም አስፈለጋቸው?አንድ ሃገር ካለን ለምን አሰብን ስንጠይቅ ይከፋቸዋል?በታሪክ ሂደት ስሞች በተደጋጋሚ ተቀያይረዋል ፥ አሁን ታዲያ ለምን የስም ክለሳ ያደርጋሉ?ለምን ሃገራችሁ አይደም እያሉ አፈር ገፍተን ከምንኖረበት መሬት እያፈናቅሉ ያባሩናል?ኤርትራን አስገንጥለው ኢትዮጵያ ?ለሱዳን ግዛታችንን እየሰጡ ኢትዮጵያ ? የኛን ዘር እያጠፉ ግዛታቸውን እያስፋፉ ኢትዮጵያ ?
የኔ ጥያቄ ግን ለምን በዘር በተዋቀረ ምድር ላይ ሃገሬ ብላችሁ ትኖሩ ዘንድ አማሮች እንዴት ልባችሁ ፈቀደ ነው?መችስ ምንም አይመጣብንም ብዙም ችግር የለውም ኢትዮጵያ ብቻ ትኑርልን የሚል ቅዠት ውስጥ ሆነን ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ነገር በዘር እንደሚሰራ ሳያይ ወይም ሳይሰማ የቀረ የለም ፤ ይህን እያወቅህ በዚህ አይነት ሃገር ውስጥ መቀጠል ብትፈልግ እንኳ የራስህን የአማራ ብሄርተኝነት ካልገነባህ በስተቀር በዚህ ህብረሰብ ውስጥ መትረፍ(survive ማድረግ) አትችልም ።
superman ነኝ ብለህ ካላመንክ በስተቀር በደቦ የሚጫወተውን በግልህ ተፎካክረህ አታሸፈውም ፥ ፍታሃዊ ውድድር(fair game) አይደለምና። የሰው ልጅ ማህበራዊ ፍጡር ነው ፤ እናም ማህበረሰቡ ከሚያፈራው የተወሰነ(limited) አንጡረ ሃብት(resource) ውስጥ የተወሰነ ለማግኘት ነው ግለሰቦች የሚሻሙት። እንደ ምዕራባዊያኑ አይነት የተሻለ ፍታሃዊ በሚባሉ ማህበረሰብ ውስጥ የተሻለ ፍትሃዊ የሆነ ፉክክር ይካሄዳል ፥ ግለሰቦችም የተሻለ እድል ይኖራቸዋል (የልፋታቸውን ለማግኘት) ፤ እንደ ቻይና አይነት ማህበረሰብ ውስጥ ደሞ በተለያዩ ዘዴዎች(በዝምድና በሙስና በስርቆት ወዘተ) የተወሰኑ ግለሰቦች በሌላው ላይ አድቫንቴጅ እየወሰዱ ፍትሃዊ ያልሆነ እሽቅድምድም በማኪያሄድ ማህበረሰቡ(ቻይና እነደ ሃገር) ካፈራው አንጡረ ሃብት ፍታዊ ያልሆነ ሃብት በቅርምት ለግላቸው ይወስዳሉ። አንድ ህብረተሰብ ከሚያፈራው(ከሚያመርተው)አንጡረ ሃብት የተሻለ ሼር ለማግኘት ስትል ከልጅነትህ ጀምሮ እራስህን በትምህርት እና በስራ ጠምደህ ነው የምትኖረው ፤ አርሰህ እና ቆፍረህ እራስህን የምትመግብ ገበሬ ብትሆን እንኳ ከዚህ ስሌት ልታመልጥ አትችልም ፥ አምርተህ የምትሸጠውን ሰብልና ለፍጆታህ መልሰህ የምትገዛቸውን ነገሮች ዋጋ በመጨረሻ የሚወስንብህ ህብረተሰቡ ስለሆነ። በዚህ ሁኔታ ነው ሰዎች የተሻለ ሃብተ ለማግኘት ወይም ያላቸውን ለመጠበቅ በሚደረግ ውድድር ህብረተሰብ እየሰራና(operate) እየተንቀሳቀሰ ያለው።
በኢትዮጵያ አንዳንዶቹ የዘር ወይም የነገድ ብሄርተኝነት(ህዝባውነት) ከ60ዓመት እስከ 260ዓመት ጀምሮ በጊዜ ህደት በፈረጠመ የዘር ብሄርተኝነት ውስጥ አሁን የሚገኙ ሲሆን ሌሎቹ ጭራሹን በታሪካቸው ከጎሳ ስነልቦና በህብረተሰብ የለውጥ ሂደት ውስጥ ከነአካቴው ገና ያላለፉ ናቸው። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ኢፍታዊ የሆነ የግለሰቦች እሽቅድምድም ብቻ አይደለም ያለው። አማራ በስነልቦናው ግለኛ(individualistic) ባህል ያለው ህዝብ ከመሆኑ አንጻር አደጋው የሚመጣው እዚህ ጋር ነው። እንዳልነው ህብረተሰቡ ከሚያመርተው አንጡረ ሃብት የልፋቱን ለማግኘት ሁሉም መስመሩ ላይ ይገኛል ፥ ነገር ግን አማራ በግሉ ለዚህ ውድድር ሲቀርብ ሌሎቹ በዘራቸው በደቦ ለፉክክሩ ይቀርባሉ ፤ ሳይጀመር ውጤቱ የታወቀ ያለቀለት ውድድር ማለት ነው። ብትማርም ብትሰራም ስምህና ብሄርህ እየታየ ነው እድል የሚሰጥህ ፤ የመጣህበት ክልል የመኪና ታርጋህ እየታየ ትራፊክ ያንገላታሃል ፣ ለስራ ብታመለክት ስምህና ብሄርህ ታይቶ ነው እድል የምታገኘው ፥ የራሳቸውን ዘር አጥተው ቢቀጥሩህም የስራ እድገትህን እንደተመኘሃት ሳታያት ታልፋለህ ፥ ለምን?በዘር ብሄርተኝነት ታንጸዋላ ፥ አማራው ደሞ እስካሁን በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት(ለአማራው ሁሉማ አንድ ነው ወይም ነበረ)።
የዘር ብሄርተኝነትን ውጤት በምሳሌ ፦ ልጁ የወለጋ ልጅ ነው ፥ በጆግራፊ ይሁን በሂስትሪ(ትዝ አይለኝም)ለአስተማሪነት ተመርቆ አዲስ አበባ ይመደባል፤ አዲስ አበባ ለምደባው ቢሮ ገብቶ ያናገረው ሰውዬ ስሙን አይቶ አሪፍ ት/ት ቤት እንደመደበውና ብዙ እንዳይጨናነቅ ደሞ በሲቪክ ዲፓርትመንት እንደተመደበ ለኔ በግልጽ አጫውቶኛል ፤ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ነው እንግዲህ በዕጣ መመደብ የነበረበትን ት/ት ቤት ትተን ሜጀር ያደረገበትን ፊልድ እንኳ ተጥሎ ለምቾቱ ሲባል በማይነሩ ሲቪክ እንድያስተምር የመደቡት። እግዲህ በዚህ ህብረተብ ውስጥ ነው ሌሎቹ በደቦ አንተ ደሞ በግልህ ለፉክክር የምትቀርበው። አማራ በአብዛኞቹ አይን እኮ እንዲያውም እልም ያልክ ጠላት ነህ ፥ በሰላም እንዴት እንደሚገላገሉህ ነው ምኞታቸው ፤ እናም አየህ አንተ በግልህ ትቀርባለህ ሌሎቹ ደሞ በዘራቸው በደቦ ይወዳደራሉ ሃገሪቷ የምታፈራውን ውስን ሃብት ለመቀራመት። ታዲያ ለምን አማራ ? ለማተሸንፈው ውድድር እራስህን ለምን ታቀርባለህ?
ፍትሃዌና እኩል የሄነ እድል ማግኘቱ ቀርቶብህ የመኖር ጫንቃው ቢኖርህ እንኳን እነሱ የኛ የሚሉትን ክልል ቀርጸው ግዛቱን በጊዜ ሂደት(ተጨማሪም ለማግኘት እየሰሩ) ለማይቀረው ግንጠላ ሲገዘጋጁ በግልጽ እያየህ የትኛው የጋራ ሃገር እና ሃብት ይተርፋል ብለህ ነው ዝምም… ?አማራ ካልነቃህ ከዚህ ቀደም ከተሰጡህ የተለያዩ ደውሎች ላይ ተጨማሪ ደውል(ፊንፊኔ) ነው አሁን እየተሰጠህ ያለው..
የአማራን ብሄርተኝነት የመገንባቱ ሰዐት አሁን ነው፥ its today or never !
Average Rating