www.maledatimes.com ዜና ጎንደር በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ አሁንም ምስክሮች አልተሰሙም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዜና ጎንደር በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ አሁንም ምስክሮች አልተሰሙም

By   /   June 28, 2017  /   Comments Off on ዜና ጎንደር በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ አሁንም ምስክሮች አልተሰሙም

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 9 Second

(ሰኔ 20/2009 ዓ.ም) የእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ቀሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር፡፡ ዳኞች የቀረበ ምስክር መኖር አለመኖሩን አቃቤ ህግን ሲጠይቁ ከችሎት ውስጥ አንድ ሰው ምስክር መሆኑን በመግለፁ ከችሎት እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ አቃቤህግ የቀረበው ምስክር 2ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ላይ የሚመሰክር መሆኑን በመጥቀስ ምስክርነቱ እንዲሰማለት ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግ በተጨማሪም ቀሪዎቹ ምስክሮች በስልክ ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑን እና በዛሬው ቀጠሮ ያልቀርቡ ከሆነ በቀጣይ ቀጠሮ የሚያቀርቧቸው መሆኑን የሚገልፅ ከፖሊስ የተፃፈ ደብዳቤ ይዞ የቀረበ ሲሆን ዳኞች የተከሳሽ ጠበቆችን በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየት ጠይቀዋቸዋል፡፡ አቃቤ ህግ በቂ ጊዜ ተሰጥቶት እንደነበረ፣ በባለፈው ቀጠሮ ተመሳሳይ ምክንያት ተሰጥቶ ቀጠሮ እንደተሰጠ እንዲሁም ተደጋጋሚ ቀጠሮ ምስክሮችን ለመስማት የተሰጠ በመሆኑ፤ ተከሳሾች ዋስትና ተከልክለውና ከቤተሰብ ርቀው የሚገኙ በመሆናቸው እና የተፋጠነ ፍትህ ከመስጠት አኳያ የቀረበው ምስክር ብቻ እንዲመሰክር እና የተቀሩት ምስክሮችን አቃቤ ህግ ማቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ እንዲታለፉ ጠይቀዋል–ጠበቆች፡፡ ቀሪዎቹ ምስክሮች የሚጠበቁ ከሆነ እና ዛሬ የቀረበው ምስክር ከቀሩት ምስክሮች ጋር በተመሳሳይ ጭብጥ የሚመሰክር ከሆነ ከሌሎቹ ጋር በአንድ ቀን መመስከር እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

ንግስት ይርጋ

አቃቤ ህግ በበኩሉ የቀረበው ምስክር የሚመሰክርበት ጭብጥ ከሌሎቹ ጋር አንድ አይነት ሆነም የተለየ መስቀለኛ ጥያቄ መጠየቅ ስለሚቻል አትመሰክርም የሚባልበት አግባብ እንደሌለ የተናገረ ሲሆን ቀሪ ምስክሮችን በተመለከተ ፓሊስ በፅሁፍ የላከውን ምክንያት ፍ/ቤቱ መዝኖ እንዲወስን ጠይቋል፡፡

 

5ኛ ተከሳሽ የሆነው በላይነህ አለምነህ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመጠበቅ የተጠየቀውን ቀጠሮ በመቃወም የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል፡፡ “እኛ የታሰርነው እና ድርጊቱ ተፈፀመ የተባልነው ከባህርዳር እና ከጎንደር ምስክር እየተጠበቀ ያለው ከአዲስ አበባ፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? በባለፈው ቀጠሮ ምስክር ረጅም ቀጠሮ እየተሰጠን ያለው አቃቤ ህግ ምስክሮችን እስኪያሰለጥን ድረስ ነው ወይ ብለን አስተያየት ሰጥተን ነበር፡፡ ዛሬ የመጣው ምስክር ችሎት ቁጭ ብሎ እኛን ሲሸመድደን ነው የነበረው፡፡ የፍትህ ሳምንትን ስናከብር 7ት አመታችን ነው፡፡ ሃገር ግን በኮማንድ ፖስት እና በእዝ እየተመራ ነው፡፡ አቃቤ ህግ ታሳሪዎችን የሚያጉላላው ለምንድነው? ልጅ የለውም እንዴ? ትውልድ ቂም ይዞ እንዲኖር ነው? እኛ ማእከላዊ የደረሰብንን ግፍ ተሸክመን ነው እዚህ የምንቆመው፡፡ አቃቤ ህግ መቼ ነው ለፍትህ የሚሰራው? አቃቤ ህግ እስከመቼ ነው በዚች ሃገር ህልውና የሚቀልደው? እኛ አምባገነን ስርዓቱ እንደሚለው አይነት ሰው አይደለንም፡፡ ሰላማዊ ታጋይ ነኝ፡፡ በወጣትነቴ ለዚህች ሃገር ብዙ ከፍያለሁ፡፡ አሁንም ብዙ ይጠብቀኛል፡፡ ለሃገር የሚጠቅም ነገር መስራት እፈልጋለሁ፡፡ ፍ/ቤት አቃቤህ ግን ማዘዝ ከቻለ ለምንድነው ሃይ የማይለው?”

 

ዳኞች የአቃቤ ህግን እና በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አስተያየት ከሰሙ ምሳ ሰዓት በመድረሱ የቀረበውን ምስክር እና በተነሳው ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት ለከሰዓት ቀጠሮ የሰጡ ሲሆን 5ኛ ተከሳሽ (በላይነህ አለምነህ) የአቃቤ ምስክሩን በተመለከተ ያነሳው አስተያየት ተገቢ መሆኑን ተናግረው፤ በችሎት የአቃቤ ምስክር መኖሩን እንዳላወቁና ለወደፊቱ እንደሚጠነቀቁ ገልፀዋል፡፡

በከሰዓቱ ችሎት አንድ ዳኛ በመጉደሉ በቢሮ ነበር ዳኞች የተሰየሙት፡፡ አቃቤ ህግ እና የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ቀርበው ውሳኔውን ሰምተዋል፡፡ አቃቤ ህግ የቀረበው ምስክርን እንደማይፈልገው እና እንዳሰናበተው በመናገሩ 2ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ላይ ይሰጣል የተባለው ምስክርነት ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ ቀሪ ምስክሮችን ለመጠባበቅ የመጨረሻ ቀጠሮ ለሃምሌ 11/2009 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ዜናው የተገኘው ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ነው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 28, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 28, 2017 @ 7:53 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar