===================================
* ጉዳቱን ከአንደበቱ ..
* የአባወራው ጉዳይና አስተምሮቱ …
ወጣቱ አባወራ መሀመድ ሁሴን ስለሆነው ሁሉ ፋጣሪውን ባያማርርም ዛሬ ብቸኛ አይደለምና ከወራት በፊት ሳውቀው የጨለመ የሚመስል ተስፋው በወገኖቹ አይዞህ ባይነት ብሩህ እየሆነለት መጥቷል ! ከፈጣሪ በታች ወገን ለወገኑ መድሐኒት ስለመሆኑ ምስክር ነኝና የማውቀውን አወጋችኋለሁ ….
የመሀመድ ህመም መረጃ በመሰራጨቱ ለስራ ጉዳይ ያመራ ወደ ኩንፊዳ ያመራ አንድ ወንድም ከትናንት በስቲያ
ሌሊት ደወሎ በኩንፊዳ የመንግስት ሆስፒታል እንደሚገኝ አሳወቀኝ ፣ደስ አለኝ ! ይህው መሀመድን በአካል የጎበኘው ወንድም ወገኖቹ መሀመድ ያለበትን ሁኔታ ይረዱት ዘንድ ያለበትን ሁኔታ ቀርጸህ ላክልኝ አልኩት ፣ ጉዜ አልፈጀበትም ፣ የሆነውን እኔ ከጻፍኩት በተጨማሪ ትረዱት ዘንድ ወንድማችን ሚከተለውን የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃ ልኮልኛል ! ተመልከቱት …
የአባወራው ጉዳይና አስተምሮቱ …
=====================
መሀመድ እንዲህ ተሰናከልኩ ብሎ ፈጣሪውን አያማርርም ፣ ይልቁንም ስለሆነው ሁሉ ለፈጣሪው ምስጋና ከማቅረብ አይቦዝንም ። ለመሀመድ እርዳታ ሳሰባስብ በመንገዱ የታዘብኩት ፣ የተመለለትኩት ብዙ ነው ። ልጇ በጠና የታመመባት እናት ለእርሷ ከተሰጣት የመመላለሻ ዳረንጎት ለመሀመድ ይሁን ብላ የሰጠችኝን እርዳታ ልብን ጠልቆ የሚነካ ነበር ! … በአረብ አሰሪዎችዋ ቤት ጠርታ እርዳታ ያደረገችውን አንድ ፍሬ ጉብል ሳውዲ ያደረሰ መንገድ መሀመድ የመጣበት የየመኑ ህገ ወጥ መንገድ ነበር። ልጅ ሆና የተሰደደችበትና ታሪክና የእሷንና የአሰሪዎቿን ደግነት ከህሊናየ የማይጠፉ የዛሬ ኩነት ፣ የነገ ትዝታዎች ናቸው ። …ሰሞነኛው የመሀመድ እርዳታ ስብሰባ መንገድ ያሳየኝ ብዙ ለነገ ትዝታ የሚሆን የማንታች ን መገለጫ ብዙ አለ … ብቻ ሞልተን ከተረፍነው ሀበሾች ወንድም እህቶች መካከል እጅግ በጣም ጥቂት ደጋጎች ያላቸውን በማካፈል የሌላቸው በገንዘብ የማይተመን የሞራል አለኝታነታሁን ለመሀመድ ስላሳያችሁ ምስጋናየ ወደር የለውም !
ሰው ሰውን ሰውን የሚረዳና የሚደግፈው ” ከተቸገረው ጋር ተካፍለህ ብላ !” የሚለው ቅዱስ ቃል ሰርጾ የገባው እንደሁ ነው ። ሰው መረጃ ከሌለው ባዶ እቃ ነው ፣ ሰው ነንና በስደቱ አስከፊ ህይዎት ያላየነውን እናይ ፣ የረሳነውን እናዘክር ዘንድ ” የተቸገረን እርዱ ፣ እንርዳ !” የሚሉትን ያብዛልን ። በዋናነት የሚረዳው አንድየ ነው ፣ ሰው ደግሞ ምክንያት ነው ! ብርቱ ፣ ጠንኳሮችን የሚያሸበርከውን ፣ ከፍ ያሉትን የሚያወርደው ፣ ካልተጠበቀ ውስጠ ደዌ በሽታ በአደጋና በመሳሰሉት ሁኔታ የወገንን እግረና እጅ ተቀስፎ ስንመለከት ከመሸፋፈን ይልቅ በአደባባይ እርዳታና መፍትሔ ማፈላለጉ ተገቢና ከማናችንም የሚጠበቅ ቅዱስ ተግባር ነው !
ከወራት በፊት እዚህ ጅዳ ኢነኪሽ በተባለ መንደር እንጀራ ልገዛ በገባሁበት ሲቅ የሱቁ ባለቤት ስለ መሀመድ መረጃ ደረሰኝ ፣ መሀመድ ተስፋ ቆርጦ ከሆስፒታሉ ሰራተኞችና ጠባቂዎች ግብግብ ገጥሞ ነበር ፣ ደውሎልኝ ብዙ አወራን ተረጋጋ ! መረጃውን ለጅዳ ቆንሰል አቀበልኩ ፣ ጎበኙት ! ከሳንምንታት በኋላ እንደሚሳፈር ተነገረኝ ! ከወራት በኋላ መሀመድ በላከልኝ መልዕክት ወደ ሀገር ቤት እንዳልተላከ አዝኖ ያን ሰሞን የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ ከፍቶት ነበር ! የእርዳታ ጥሪ አቀረብን …
ዛሬ ወንድም መሀመድ የትናንቱ አይደለም ፣ በመንፈስ ጥንክሮ ሮመዳንን እየጾመ ናፍቆት በከረመ የወገኑ አይዞህ ባይነት ተስፋው በርቷል ! እነሆ ላደረጋችሁለት የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ያመሰግናችኋል !
ከኔምንም በላይ ብዙ ሆነን ፣ ጥቂት አዋጥተን አባወራውን ወጣት ለመደገፍ የሚታስፈልገን ፈቃደኝነቱ ነው ! ያለው የቁርሱን ግማሽ ይረዳል ፣ የሌለው በሞራልና በጸሎት መሀመድን ይደግፍ !
እርዳታው ይቀጥላል ፣ እስካሁን በሞራልም በገንዘብም ከጎናችን ለቆማችሁ ላደረጋችሁት ሁሉ ለእኔም ኃይል ብርታት ሁናችሁኛልና አመሰግናለሁ !
ከፈጣሪ በታች ወገን ለወገኑ መድሐኒት ነው !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 21 ቀን 2007 ዓም
Average Rating