www.maledatimes.com የቦብ ማርሌይ ሃውልት ፈረሰ ፣የወጣው ወጭ ኪሳራ ላይ ወደቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቦብ ማርሌይ ሃውልት ፈረሰ ፣የወጣው ወጭ ኪሳራ ላይ ወደቀ

By   /   June 29, 2017  /   Comments Off on የቦብ ማርሌይ ሃውልት ፈረሰ ፣የወጣው ወጭ ኪሳራ ላይ ወደቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 27 Second

ጌጡ ተመስገን

#ETHIOPIA | ዛሬ – የቦብ ማርሌይ አደባባይ በትራፊክ መብራት ተተክቷል የዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት የቦብ ማርሌ የልደት በዓል በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ። የወቅቱ የከተማው ከንቲባ ከኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ያለውን ቦታ ‹‹ቦብ ማርሊ አደባባይ›› ብለው ሰየሙት። አርቲስት ዘለቀ ገሠሠ፣ አዲስ ገሠሠ እና አዋድ አሕመድ ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር የቦብ ማርሊ ሃውልት እንዲቆም አስቻሉ። ከ12 ዓመታት በኋላ ለአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፍሰት እንቅፋት በመሆኑ በቀለበት መንገዱ ከሚገኙ አደባባዮች መካከል መፍረስ አለባቸው ተብለው ከተለዩት አደባባዮች መካከል አንዱ የሆነው፣ ይኸዉ የሬጌው ሙዚቃ ንጉሥ ቦብ ማርሌ ምሥለ ቅርፅ ያረፈበትና በሥሙ የሚጠራው አደባባይ ሆነ፡፡ በኢምፔሪያል ሆቴል አካባቢ ከአራት አቅጣጫዎች ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግደውን ይህ አደባባይ ከላይ ፈረሰ፡፡ ዛሬ – የቦብ ማርሌይ አደባባይ በትራፊክ መብራት ተተክቷል

 

አደባባዩ ከተሰየመ አይቀር ለምን ሃውልቱ አይቆምም በሚል ሃሳብ ያመነጩት ወንድማማቾቹ ዘለቀ ገሰሰ እና አዲስ ገሰሰ፤ የቦብ ማርሌይን ሃውልት በእውቁ ሰዓሊና ቀራፂ ብዙነህ ተስፋ ማሰራታቸውን ይታወቃል ይሄው ሃውልት ሚያዚያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም እንደተመረቀ ይታወሳል

3 ሜትር ከ80 ሳንቲ ሜትር ቁመት ያለውን የቦብ ሃውልት የሰራው ቀራፂ ብዙነህ ተስፋ በሰጠው አስተያየት፤  “ሃውልቱ ከሁሉም በላይ በሙዚቀኞችና በሙዚቃ አፍቃሪዎች ተነሳሽነት መተከሉ አስደሳች ነው ማለቱም የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነበር

በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ጃሉድ አወል፣ ዘለቀ ገሰሰ፣ አብነት አጎናፍር፣ ኬኒ አለን፣ ሲድኒ ሰለሞን፣ ጆኒ ራጋ፣ ራስ ጃኒ፣ ሸዋንዳኝ ሃይሉ፣ የሺ ደመላሽ እና ሌሎችም ዕውቅ ድምፃውያን የተካፈሉበት ሲሆን ጃኖ፣ መሃሪ ብራዘርስና ብሉ ቫይብስ የሙዚቃ ባንዶች አቀንቃኞ ጋር በማጀብ ስራ ሰርተዋል ፣ ከፍተኛ የሆነ ወጭ የወጣበት ይሄው ሃውልት ከጥቂት አመታት በሁዋላ መፍረሱ አግባብ አለመሆኑ ተገልጧል።

በሌላም በኩል በመዲናይቱ አዲስ አበባ የተሰሩት የውስጥ ለውስጥ የከተማ መንገዶችም ሆኑ የፈጣን ጉዞ መንገድ ሃይ ወይ በብዙው ማስተር ፕላኑ ትክክል ያልሆነ እና አደባባይ የሚበዛበት በመሆኑ ለትራፊክ ፍሰት ያለው ጉዳት በብዙ እንደሆነ ባለሙያዎች ጠቁመዋል ፣ በፍጥነት በሚኬድበት መንገድ ላይ አደባባይ በየትኛውም አለም የማይሰራ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ከቻይና ኩባንያ ጋር በመተባበር የተሰራ በመሆኑ ፣መንገዶቹ በሙሉ በአደባባይ የተሞሉ መሆናቸውን አንዳንድ የማለዳ ታይምስ እና ዘሃበሻ  ተከታታዮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጠዋል

የGetu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ምስል

የGetu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ምስል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 29, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 29, 2017 @ 11:57 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar