www.maledatimes.com የወገራ ገበሬዎች ላይ የታወጀው ፍጅት እና የእኛ ዝምታ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የወገራ ገበሬዎች ላይ የታወጀው ፍጅት እና የእኛ ዝምታ

By   /   June 29, 2017  /   Comments Off on የወገራ ገበሬዎች ላይ የታወጀው ፍጅት እና የእኛ ዝምታ

    Print       Email
0 0
Read Time:51 Second

የወገራ ገበሬዎች

ከሙሉቀን ተስፋው

አገዛዙ በዐማራ ገበሬዎች ላይ ይፋ ጦርነት ካወጀ አንድ ዓመት ሆነው፡፡ በተለይ ደግሞ የወገራ ገበሬዎች ላይ ከባድ መሣሪያ ሳይተኮስ፣ የገበሬዎች ቤት ሳይቃጠል፣ ሰው ሳይሞት ሳምንት አይደፍንም፡፡ የትግሬው አገዛዝ በከባድ መሣሪያ ቤቶችን ሲያነድ፣ ሕጻናትንና አቅመ ደካሞችን ሲገደል እያየንና እየተመለከትን ምንም እያደረግን አይደለም፡፡ ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ትኩረት እንኳ እንዲያገኝ እያደረግን አይደለም፡፡ በወገራ መንግሥትን ይጥላ፣ ይውደድ አገዛዙ ጉዳዩ አይደለም- በአካባቢው የተገኘ ዐማራ የሆነ ሁሉ እስካፍንጫው በታጠቀ የትግሬ ጦር ዒላማ ይደረጋል፡፡

በርካቶች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል፤ ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው ተለይተዋል፡፡ የአባውራ ሴቶች ይደበደባሉ፡፡ ይህ የአለፉት ስምንት ወራት የወገራ ገበሬዎች ሁኔታ ነው፡፡ ይህችን ትንሽ ማስታዎሻ ስጽፍ እንኳ ሁለት ወንድማማቾች በከባድ መሣሪያ ወድቀዋል- የአባ ጋሻው ልጆች (መልካሙና አደራጀው)፡፡ የወገራ ገበሬዎችን አንድም ሳይለይ ነው አገዛዙ ጦርነት የከፈተባቸው፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት በግብርናውም ሆነ በጉብዝናው የታወቀ አቶ ጓዴ ጌጡ የሚባል ወጣት ነበር፡፡ ሦስት የትግሬ ወታደሮች ከበቡት፡፡ ሦስቱንም አጋደማቸው፤ በመጨረሻ በትግሬ እጅ አልወድቅም ብሎ ራሱን ሰዋ፡፡ ገበሬው ያለበት ሁኔታ ይህ ነው፡፡ በየቀኑ ወደ አካባቢው የሚጨመረው ጦር ከሕዝብ ጋር ሳይሆን ከውጭ ወራሪ ኃይል ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው የሚመስለው፡፡

ስለ ወገራ ገበሬዎች ዝም ማለት የለብንም!! የሕዝባችን ዕልቂት ሊገደን ይገባል!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 29, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 29, 2017 @ 12:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar