www.maledatimes.com የሰሜን አሜሪካ እግርኳስ ጨዋታ መዝጊያ ዝግጅት በብጥብጥ ተፈጸመ !!”በጣም ታሳፍራላችሁ ይሄ የኢትዮጵያዊነት ባህል አይደለም ” ፌደሬሽኑ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰሜን አሜሪካ እግርኳስ ጨዋታ መዝጊያ ዝግጅት በብጥብጥ ተፈጸመ !!”በጣም ታሳፍራላችሁ ይሄ የኢትዮጵያዊነት ባህል አይደለም ” ፌደሬሽኑ

By   /   July 9, 2017  /   Comments Off on የሰሜን አሜሪካ እግርኳስ ጨዋታ መዝጊያ ዝግጅት በብጥብጥ ተፈጸመ !!”በጣም ታሳፍራላችሁ ይሄ የኢትዮጵያዊነት ባህል አይደለም ” ፌደሬሽኑ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 48 Second

34ኛው የሰሜን አሜሪካ እግርኳስ ጨዋታ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት ተጀምሮ በትላንትናው እለት 7/8/2017 የተፈጸመ ሲሆን በመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በሰአቱ ዝግጅቱ ባለመከናወኑ እና ሙዚቀኞች በሰአቱ ባለመግባታቸው ታዳሚውን ህዝብ አስቆጥቶአል ።
ከለሊቱ ሁለት ሰአት ላይ በሙዚቃ አዳራሹ የገቡት ጃኪ ጎሲ እና አብነት አጎናፍር ሲሆኑ ሌሎች የሙዚቃ ባንዶች እና ብዟየሁ ደምሴ እና ራስ ባንዶችን በወቅቱ ወደ አዳራሹ የሚያመጣ ሰው ባለመኖሩ ብጥብጡን እንዲከፋ አድርጎአል ።
በተለይም በዝግጅቱ አዳራሽ ውስጥ የተሰበሰበው ማህበረሰብ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ሲሰባብሩ የታዩ ሲሆን አዳራሹን በመጠጥ እና በውሃ ሲያበሰብሱት ታይተዋል።
ለረጅም ሰአታት ብጥብጡ ቢያይልም በመካከል የሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት ለሰላም ማስከበር ተጠርቶ ለማረጋጋት ቢሞክሩም ይበልጥ እንዲባባስ አድርገዋአል፣ ከዚህም ይበልጥ ደግሞ ጥቂት ሰዎች በምትቀሰቅሱት እረብሻ ሙዚቃው ሊከናወን አልቻለም ሲሉ ድክመታቸውን በማህበረሰቡ ለመሸፈን ሞክረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሙዚቃው መጀመር ከሚገባው ሰአት አራት ሰአታት ሙሉ ወድ ሁዋላ ዘግይቶ የተጀመረው የሙዚቃ ዝግጅት በጃኪ ጎሲ ሊጀመር የነበረ ሲሆን ህዝቡ ከማመጹም በላይ በጃኪ ላይ ጉዳት ለማድረስ ከማቀዳቸውም በላይ አስፈሪ የሆነ እንቅስቃሴ ለማድረገ ወስነው ነበር ሆኖም ግን አዘጋጆቹ ይህንን ሁኔታ በማገናዘባቸው የተነሳ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በገባውን ድምጻዊ አብነት አጎናፍን ወደ አዳራሹ እንዲገባ በማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር እንዲጋፈጥ አድርገውታል ፣ ይህንንም በመረዳት አብነት አጎናፍር በተረጋጋ አንደበት እና ሰራአት ባለው ቋንቋ ህዝቡን ማረጋጋት የቻለ ሲሆን ፣ ጥቂት የማይባሉ የዚሁ የሽብር ተሳታፊዎች ከማለዳ ታይምስ እና ዘሃበሻ አዘጋጆች ጋር በሚያደርጉት የመረጃ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጸብ ውስጥ እንዲገቡ አድርገዋቸዋል ። የፌደሬሽኑ ስህተት ከአመት አመት የማይሻሻል ቢሆንም ካሜራዎቻችን እየቀረጹ ነው እርስ በእራሳችን ከምንጠቃቃ ብንጠነቀቅ ይሻላል በማለት የዘሃበሻን ጋዜጠኛ ፣ የዳንኤል ገዘሃኝ ካሜራ መሰበር እንዲሁም ሄኖክ ደገፉን እና የማለዳ ታይምስ አዘጋጅ ዘላለም ገብሬን ለመደብደብ መነሳታቸው ምክንያት ሆኖአል።
“በጣም ታሳፍራላችሁ ይሄ የኢትዮጵያዊነት ባህል አይደለም ” እየበጠበጣችሁ ያላችሁት በጣም ጥቂት ሰዎች ናችሁ ” በማለት የገለጹት ሃሳብ በእራሳቸው ማፈር ይገባቸዋል እንጂ ማህበረሰቡን ታሳፍራላችሁ ማለታቸው ህዝቡን መናቅ ነው በማለት የህግ ባለሙያ ተክሌሚካኤል አበበ ገልጾአል ።
የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌደሬችን በየአመቱ ሲዘጋጅ ሰላሳ አራት አመት ያለፈው ሲሆን በ2018 የሚዘጋጀው የሰላሳ አምስተኛው ፕሮግራም አትላንታ መዘጋጀት ሲገባው ወደ ዳላስ መሄዱ ሙሰኝነት አለበት ያሉ የፌደሬሽኑ የቦርድ አባላት የገለጹ መሆናቸውንም የማለዳ ዘጋቢ ከስፍራው አጠናቅሮአል ።
በሌላም በኩል ፌደሬሽኑ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ነጻ መሆን ይገባዋል ፣ ግንቦት ሰባትም ይሁን ወያኔ ለእኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው የፖለቲካ እምነታችሁን ወደ ህዝብ ድርጅት ማምጣት አይገባችሁም ሲሉ ፣የተለያዩ ማህበረሰቦች ገልጠዋል ፣ በዚህ አመት በግንቦት ሰባት እና የግንቦት ሰባት አጋር ድርጅት ሆነው የሚሰሩ ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች በፌደሬሽኑ ውስጥ ተጠቅጥቀው መክረማቸው አግራሞትን ፈጥረዋል። በዚህ ልዩ ዘገባ ላይ ሙሉውን ቪዲዮ ይዘን በቅርቡ እንቀርባለን ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on July 9, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 9, 2017 @ 7:21 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar