www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ለምን ብጥብጥ ተነሳ? | ሪፖርታዥ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ለምን ብጥብጥ ተነሳ? | ሪፖርታዥ

By   /   July 10, 2017  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ለምን ብጥብጥ ተነሳ? | ሪፖርታዥ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 17 Second

(ዘ-ሐበሻ) ለ34ኛ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል በዋሽንግተን ግዛት ትልቁ ከተማ ሲያትል ለአንድ ሳምንት ያህል እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዶ በሚያሳፍር መልኩ ተጠናቋል:: በሲያትል በተደረገው የስፖርት ፌስቲቫል ላይ በርካታ መልካም ነገሮችን እንዳየነው ሁሉ ጥቂት የሚያሳፍሩና ወደፊት ሊታረሙ የሚገባቸው ድርጊቶችን ተመልክተናል::

ይህን የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ኢትዮጵያውያን ታግለው ከአላሙዲ ገንዘብና ከሕወሃት መንግስት ተጽዕኖ ያላቀቁት ሲሆን ለዚህም ድርጊታቸው ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል:: አሁንም ግን ፌዴሬሽኑ በሌላ ድርጅት ተጽዕኖ ውስጥ እንዳለ የታዘብንበት ሁኔታ አለና ፌዴሬሽኑ ይህን በቀጣይ ዝግጅት እንደሚያርም ተስፋ አለን:: አለበለዚያ ግን ተመልሰን የማንፈልገው ውጥንቅጥ ውስጥ እንደምንገባ የሚታዩ ነገሮች አሉና ፌዴሬሽኑ ራሱን መፈተሽና ከማንኛውም ሃይማኖትም ሆነ ድርጅት ራሱን ነጻ ማድረግ ይኖርበታል::

ኢትዮጵያውያንን ከመላው ዓለም እያገናኘ የሚገኘው ይኸው ፌዴሬሽን በነጻ የሚያገለግሉት የቦርድ አባላቶቹን ጽናት እና ጥረት ማድነቅ ይገባል:: እናመሰግናቸዋለንም:: እነዚህ የቦርድ አባላት ይህን ፌዴሬሽን ከየትኛውም ድርጅት ገለልተኛ የማድረጉን ስራ ካሁኑ ካልሰሩት የታሪክ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል::

በዘንድሮው የሲያትል የኢትጵያውያን ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ በመክፈቻው ዝግጅት ላይ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ሰው መገኘቱ የሚያኮራ ነው:: የሲያትል ሕዝብ ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በቀጣይ ይህን ታላቅ ዝግጅት ለሚያዘጋጁ ከተሞች አስተምሮት ያለፈው ነገር እንዳለም ይሰማናል::

ንግድ ቤቶች ልክ በሌሎች ከተሞች እንደታየው ዋጋ ጨምረዋል:: ወገንን ለአላስፈአጊ ኪሳራ መጣል የሚያስተዛዝብ ቢሆንም እንደዚህ ባለው ዝግጅት ላይ የተወሰነ ዋጋ የማሳደግ ነገር ቢጠበቅም ከአቅም በላይ ማድረጉ ግን በወገን ላይ ተጨማሪና አላስፈላጊ ጫናን እንደመፍጠር ይቆጠራል::

በመክፈቻው ቀን ሕዝብ በብዛት ቢገኝም ፌዴሬሽኑ ግን በቂ ዝግጅት ያደረገ አይመስልም:: በአንድ ስታዲየም አቅጣጫ በኩል የተቀመጡ ወገኖች የመክፈቻውን ዝግጅቶች በድምጽ የተከታተሉት ሲሆን በሌላ አቅጣጫ ያሉት ግን ምን እየተደረገ እንዳለ በድምጽ አለመስማታቸውን አስተውለናል:: ይህን የሚያህል ትልቅ ዝግጅት አዘጋጅቶ በሁሉም ስታዲየም ክፍል የሚሰማ ድምጽ ሲስተም አለማዘገጀታቸው እንደደካማ ጎን ይቆጠራል:: በቀጣይ ዓመት ይህ እንደሚስተካከል ተስፋ አለን::

በመድረክ መሪዎች በኩል ፌዴሬሽኑ ማሰብ ያለበት ነገር አለ:: በተደጋጋሚ በየዓመቱ የሚመጡት ተመሳሳይ የመድረክ መሪዎችን ፌዴሬሽኑ በሌሎች ብቃት ባላቸው ሰዎች መተካት እንደሚኖርበት ዘንድሮ ታዝበናል:: የመድረክ መሪዎቹ ለራሳቸው ዝና እንጂ ለሕዝቡ እንደማይጨነቁ መረጃዎችንም በተገቢው መንገድ እንደማያደርሱ ህዝቡ ሲነጋገርበት አስተውለናልና ፌድሬሽኑ በዚህ በኩል ሥራ ይጠብቀዋል::

አርብ ዕለት የኢትዮጵያ ቀን ሲከበር የነበረው ድባብ ደስ ይላል:: ግን በየዓመቱ የሚቀርበው የጥበብ ሥራ ተመሳሳይነቱ ሕዝቡን በቀጣይ ዝግጅት ላይ እንዳያርቀው ያስፈራልና ፌዴሬሽኑ ተጨማሪ አርቲስቶችን ቢያሳትፍ የተሻለ ነው:: በተወዛዋዦች በኩል በቂ ልምምድ እንዳልተደረገ የያዝናቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያሳብቃሉ:: ለአንድ ሰው ኮንትራት ሰጥቶ በየዓመቱ ሕዝቡን ከማሰልቸት ለተለያዩ ሰዎች በየዓመቱ ዕድል ቢሰጥ ወይም የኢትዮጵያ ቀንን ለሚያዘጋጁ ወገኖች እንደጨረታ ነገር ተደርጎ ዝግጅቶች ቀድመው ቢገመገሙ የተሻለ የኢትዮጵያ ቀንን ማክበር ይቻላል ብለን እናስባለን::

ቅዳሜ በመዝጊያው ዝግጅት ላይ የነበረው ነገር አሳፋሪ ነበር:: በቀጣይ ይህ ስህተት እንዳይደገም ለተፈጠረውም ነገር ፌዴሬሽኑም ሆነ ከፌዴሬሽኑ ጋር አብረው የሚሰሩ ፕሮሞተሮች ጠንክረው መሥራት ይገባቸዋል:: ከምሽቱ 10 ሰዓት የተጠራ ሕዝብ ለመዝጊያ ዝግጅት ጓግትፕ ለ4 ሰዓት ያህል ዝግጅቱን ማዘገየትና ሕዝቡን ማጉላላት ተገቢ አይደለም:: በአይናችን እንዳየነው አርቲስቶቹ ለመዝጊያው ዝግጅት የመጡት ከነጋ በኋላ 2 ሰዓት ላይ ነው:: እንደዚያም ሆነው ዝግጅቱን ቶሎ አለመጀመራቸው ሕዝቡን አስቆጥቶ “50 ዶላሬ” እያለ እየዘፈነ እንዲቃወምና ወደመድረኩም ጠርሙሶችና ቁሳቁሶች እንዲወረወሩ ምክንያት ሆኗል::

አዘጋጆቹ ወዲያው ይቅርታ መጠየቃቸው የሚያስመሰግን ቢሆንም መድረኩን የያዘው ሰው አዳራሽ ሙሉ ህዝብ እየተቃወመ “የምትበጠብጡት ጥቂት ሰዎች ናችሁ” ብሎ መናገሩ ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራል:: ሲጀመር ትንሽ የሚባል ሰው የለም:: ቀጥሎም ሕዝቡ “ዋ እያለ” ሲያስጠነቅቅ ቆይቶ ነው ት ዕግስቱን አጥቶ ወደማይገባ ተግባር የተሸጋገረው::

ይህ የመዝጊያ ዝግጅት ለአራት ሰዓታት ያህል በመዘግየቱ በርካታ ወገኖች በነጋታው እሁድ ወደየመጡበት ከተማ ስለሚመለሱ ችግር እንደፈጠረባቸው እኛ ካረፍንበት ሆቴል ውስጥ ከነበሩ ወገኖች ተረድቻለሁ:: በነጋታው በረራ ላለበት ሕዝብ ሰዓት ማክበር እንደቅድሚያ ነገር ሊቆጠር ይገባልና በዚህ ዝግጅት ተመልካቹም አዘጋጆቹም እንደተማሩበት ተስፋ እናደርጋለን::

በዚህ የመዝጊያ ኮንሰርት ላይ አብነት አጎናፍር; ብዟየሁ ደምሴና ጃኪ ጎሲ እንደሚገኙ ቀድሞ ተገልጿል:: በዚህ መዝጊያ ዝግጅት ላይ ፕሮግራማቸውን ሊያቀርቡ የመጡት እነ ፋንትሽ በቀለ ዝግጅታቸውን ሳያቀርቡ ተቃውሞውን ሰምተው ተመልሰዋል:: ጃኪ; አብነትና ብዟየሁም በዚህ ታላቅ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ አራት ዘፈን ብቻ እያንዳንዳቸው ዘፍነው መሄዳቸው ሕዝቡን እንዳስቆጣው ከሰበሰብናቸው መረጃዎች ለመረዳት ችለናል::

ሰው አልተሰበሰብና አልዘፍንም የሚሉ አርቲስቶች ካሁን በኋላ መማር ያለባቸው አክብሯቸው በሰዓቱ ለተገኘው ሕዝብ ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም አክበረው ሥራቸውን መጀመር ነው:: ሰው አልተሰበሰብም ብሎ ሥራን አለመጀመር ግን ሕዝብን እንደመናቅ ይቆጠራልና አርቲስት ሆይ ንቃ:: ገንዘቤ ነው የምትለውን ሕዝብ አክብር::

እዚህ ላይ ሳናነሳ የማናልፈው ነገር የአብነት አጎናፍርን ጉዳይ ነው:: አራት ሰዓት በመዘግየቱ የተቆጣውን ሕዝብ ለማረጋጋት በቅድሚያ ጃኪ እንዲወጣ ታስቦ ቢሞከረም የማይሆን ሆነ:: ሆኖም ግን አብነት “ጥፋቱ የኛ አይደለም ይቅርታ አድርጉልን” በሚል መድረክ ላይ ወጥቶ “ሆ ብዬ መጣሁ” የሚለውን ተወዳጅ ዘፈኑን አቅርቦ ሕዝቡን በማረጋጋቱና ትልቅ ኃላፊነት በመውሰዱ አድናቆታችንን ልንገልጽለት እንወዳለን::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on July 10, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 10, 2017 @ 2:14 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar