www.maledatimes.com “ማእከላዊ ውስጥ ሴትነቴን ተመስርተው ጥቃት ፈጽመውብኛል” – አክቲቪስት ንግስት ይርጋ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“ማእከላዊ ውስጥ ሴትነቴን ተመስርተው ጥቃት ፈጽመውብኛል” – አክቲቪስት ንግስት ይርጋ

By   /   July 12, 2017  /   Comments Off on “ማእከላዊ ውስጥ ሴትነቴን ተመስርተው ጥቃት ፈጽመውብኛል” – አክቲቪስት ንግስት ይርጋ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 17 Second


#Ethiopia #AmharaProtests #FreeNigist

ስም፡- ንግስት ይርጋ ተፈራ
ዕድሜ፡- 24 አመት
አድራሻ፡- ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18
አሁን በእስር የምገኝበት፡- ቃሊቲ እስር ቤት 

 

ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሀምሌ ወር 2008 ዓ.ም በጎንደር ተደርጎ የነበረው ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፎ አድርገሻል የሚል ነው፡፡

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- የሽብር ክስ ሲሆን (‹‹ህዝባዊ አመጾችን››) በማደራጀትና በሰልፎቹም በመሳተፍ ‹‹የሽብር ቡድኖችን ተልዕኮ በመቀበል ለማስፈጽም መንቀሳቀስ›› የሚል ነው፡፡ የተጠቀሰው የህግ ክፍል ደግሞ የጸረ-ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3፣ 4 እና 6 ላይ የተመለከቱትን ድርጊቶች በመተላለፍ ወንጀል ከሌሎች አምስት ሰዎች ጋር በአንደኛ ተከሳሽነት ነው የተከሰስሁት፡፡
የክስ ሂደቱን የሚያየው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልድታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡

1. በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እስር ቤት በቀዝቃዛና በጨለማ ክፍል ውስጥ ለረጅም ቀናት አስረውኛል፡፡
2. ያለማንም ጠያቂ፣ ያለሁበት ሁኔታ ሳይታወቅ ታፍኜ ለሳምንታት እንድቆይ ተደርጌያለሁ፡፡

3. በማታ ለምርመራ በሚል ከታሰርሁበት ክፍል እያስወጡ ሰብዓዊ ክብሬን በሚያዋርዱ ተግባራትና ማሰቃየት ተፈጽሞብኛል፡፡
4. ክብሬን የሚነኩ፣ በማንነቴ ላይ የተመሰረቱ ስድቦች ተሰድቤያለሁ፡፡

5. ሴትነቴን ተመስርተው ጥቃት ፈጽመውብኛል፤ ሴት ሁኜ መፈጠሬን እንድትጠላ የሚያደርጉ ተግባራትን ፈጽመውብኛል፡፡
6. እርቃኔን አቁመው ተሳልቀውብኛል፡፡

7. የእግር ጥፍሮቼን መርማሪዎቼ ነቃቅለዋቸዋል፡፡ ጥፍሮቼን ከነቀሉ በኋላም ጥፍሮቼ የነበሩበትን ቦታ ቁስል እየነካኩ አሰቃይተውኛል፡፡
8. ጸጉሬን በመንቀልም የኢ-ሰብዓዊ ተግባር ሰለባ አድርገውኛል፡፡

9. ክስ ተመስርቶብኝ ቃሊቲ ከተዛወርሁም በኋላ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ አልቆመም፡፡ ጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡፡ እኔን መጠየቅ የሚችለው ቀድሞ ስም ዝርዝራቸው ለእስር ቤቱ አስተዳደር የታወቁ የቤተሰብ አባላት ብቻ ናቸው፡፡ ያም ሆኖ የቤተሰብ አባላትም ቢሆን ከምዝገባ ዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ካልሆኑ መጠየቅ አይፈቀድም፡፡ በማነኛውም የስራ ሰዓት ሳይሆን ከስድስ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል ለሰላሳ ደቂቃ ብቻ ነው የምጠየቀው፡፡ ይህ ገደብ እንዲሻሻልልኝ ለፍርድ ቤት በተደጋጋሚ አቤት ብልም መሻሻል አልቻለም፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 12, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 12, 2017 @ 5:03 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar