www.maledatimes.com የህወሃት ደኅንነቶች የኮሎኔል ደመቀን የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ለመጥለፍ ሙከራ አደረጉ | በኮሎኔሉ ላይ 9 የሰለጠኑ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የህወሃት ደኅንነቶች የኮሎኔል ደመቀን የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ለመጥለፍ ሙከራ አደረጉ | በኮሎኔሉ ላይ 9 የሰለጠኑ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል

By   /   July 13, 2017  /   Comments Off on የህወሃት ደኅንነቶች የኮሎኔል ደመቀን የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ለመጥለፍ ሙከራ አደረጉ | በኮሎኔሉ ላይ 9 የሰለጠኑ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 16 Second

 

ከሙሉቀን ተስፋው

 

በጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ቤተሰቦች ላይ የደኅንነቶች ጫና ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ፡፡ የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የክስ ሒደት እየታየ የተዘጋጁ ምስክሮች ፍርድ ቤት ቃላቸውን በሚሰጡበት ሰዐት ሐምሌ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. የአገዛዙ ደኅንነቶች የኮሎኔሉን የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ጠልፈው ለመውሰድ ሲሞክሩ በሕዝብ ርብርብ መክሸፉን በአካባቢው የነበሩ እማኞች ገልጸውልናል፡፡

እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገመቱ ወጣት የደኅንነት አባላት በዕለቱ ጠዋት ጀምሮ የኮሎኔል ቤተሰቦች በሚኖሩበት ቤት በር አካባቢ ቆመው መዋላቸውን የሚገልጹት ምንጮች ምን እንደሚፈልጉ ሲጠየቁ ‹‹ሰው እየጠበቅን ነው›› የሚል መልስ በትግርኛ ቅላጼ ባለው አማርኛ እንደመለሱላቸው ገልጸው ለረዥም ሰዐታት በአካባቢው መቆማቸው እንዳጠራጠሯቸው ተናግረዋል፡፡ ከሰዐት በኋላ የኮሌኔሉን ልጅ ጠልፈው ለመውሰድ በማባበል ላይ እያሉ የኮሎኔል ደመቀ የቅርብ ዘመድ የድረሱልኝ ጩኸት በማሰማቷ በአካባቢ የነበሩ ጥቂት ሰዎች ተሰባሰቡ፤ ከዚያም እነማን ናችሁ መታዎቂያ አሳዩን የሚል ጥያቄ ከተሰበሰቡት ጥቂት ወጣቶች ሲቀርብላቸው ወደ ማስፈራራት እንደገቡና በኋላ የሰው ቁጥር እየጨመረ ሲሔድ በተሸከርካሪ በፍጥነት መሰወራቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡


ይህ በዚህ እንዳለ ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን 2009 ዓም ድረስ በኮሎኔል ላይ 9 የሚሆኑ የሰለጠኑ ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበው መመስከራቸውን ሰምተናል፡፡ አብዛኛዎቹ ምስክሮች ከትግራይ ፊታቸውን ተሸፋፍነው በጥቁር መኪና በፖሊስ ታጅበው ፍርድ ቤት እንደገቡና ወዲያውኑ ወጥተው እንደተሰወሩ የፍርድ ሒደቱን የተከታተሉ ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ በዋለው ችሎት የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኃላፊ የነበረውና ሸፍቻለሁ በማለት ለአገዛዙ ሲሰራ የነበረው ኮማንደር ዋኘውን ጨምሮ እነ ኮማንደር ማሙየ መመስከራቸውን አውቀናል፡፡


የዐማራ ተጋድሎ አብሳሪው የጀግናው ኮሎኔል ደመቀ የፍርድ ሒደት ሆን ተብሎ የዐማራ ተጋድሎ አንደኛ ዓመት በሚታሰብበት ቀን እንደተደረገ የሚገልጹት ምንጮች የኮሎኔሉን ሞራል ለመጉዳት የታሰበ ቢሆንም ጀግናው ግን የበለጠ የተረጋጋና አስፈሪ ግርማ ሞገስን ተላብሶ እንደነበር ፍርድ ቤት የነበሩ ግለሰቦች ገልጸውልናል፡፡ 8 የመከላከያ ምስክሮች ከሐምሌ 25 እስከ 27 ቀን ድረስ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 13, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 13, 2017 @ 12:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar