www.maledatimes.com በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ/ም ይጠናቀቃል | መንግስት በይፋ አዋጁ እንደሚነሳ አላሳወቀም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ/ም ይጠናቀቃል | መንግስት በይፋ አዋጁ እንደሚነሳ አላሳወቀም

By   /   July 13, 2017  /   Comments Off on በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ/ም ይጠናቀቃል | መንግስት በይፋ አዋጁ እንደሚነሳ አላሳወቀም

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 54 Second

 

(የጀርመን ድምጽ ራድዮ) መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የታወጀዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ/ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በመንግሥት በኩል ሰላምና መረጋጋት ወደ ቦታዉ መመለሱን ቢገልፅም እስካሁን በይፋ አዋጁ እንደሚነሳ አላሳወቀም።

ከማሕበረሰቡ በኩልም ቢሆን ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል መነሳት አለበት ቢሉም፣ ገሚሱ ደግሞ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች ችግሮች ስላሉ አዋጁ መነሳቱ ላይ ጥርጣሬ አላቸዉ።

በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 93፣ ንዑፅ አንቀፅ 3 ሥር የአቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚንስትሮች ምክር ቤት እንደሚታወጅና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ ለስድስት ወራት ሥራ ላይ እንደሚዉል ይደነግጋል። የሚንስትሮች ምክር ቤት አዋጁ እንዲራዘም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጠየቀዉ ፓርላማዉ በሁለት ሦስተኛ አብላጫ ድምፅ አፅድቆት አዋጁ በየአራት ወሩ እየታደሰ በተከታታይ ሥራ ላይ እንዲዉል ሊያደርግ እንደሚችልም ሕገ-መንግሥቱ ይጠቅሳል። የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለዉን በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወደ መንግሥት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅሕፈት-ቤትም ሆነ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊዎች ጋር በተደጋጋሚ ብንደዉልም ለዛሬ የመንግሥት ቃል አቀባዮችን ማግኘት አልቻልንም።

ይሁን እንጅ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጅ ዞን መልካ-ሶዳ አካባቢ ወክል በፓርላማ የሚገኙት አቶ ቦነያ ኡዴሳን አዋጁን አስመልክቶ የተሰማ አዲስ መረጃ አለ ወይ ብለን ጠይቀን ነበር።

አቶ ቦናያ: -«ሚንስትሮች ምክር ቤት አዋጁ ይቀጥል አይቀጥል የሚለዉ ላይ ጥያቄ ማቅረብ አለበት። ሚንስትሮች ምክር ቤት በዚህ ምክንያት መነሳት አለበት ወይም በዚህ ምክንያት መቀጠል አለበት ብሎ የሚያቀርበዉን ሃሳብ ፓርላማዉ ተመልክቶ፣ መከራከርም ካለበት ተከራክሮበት፣ ይቀጥል ወይም አቀጥል የሚለዉ ላይ አብላጫ ድምጽ ካገኘ ተግባራዊ ይሆናል። አሁን ግን ከሚንስትሮች ምክር ቤት የመጣ መረጃ የለም። ይቀጥላል፣ አቀጥልም የሚለዉን ዛሬ ላይ ሆነን መናገር አንችልም።»
ዶቼ ቬሌ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመወጠል እና ያለመቀጠል ሁኔታዉን በተመለከተ ኅብረተሰቡ ዘንድ ያለዉን አስተያየት ለማሰባሰብ ሞክሯል። በቡሌ-ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል እንጅኔሪንግ የሁለተኛ ዓመት ተማር የሆነችዉ አልማዝ ስጦታዉ አዋጁ ሰላም ቢሰፍንም «ቢቀጥል ጥሩ ይመስለኛል» ትላለች።

በፍቃዱ ሃይሉ የሰብዓዊ መብት አቀንቀኝ ነዉ። አዋጁ ከታወጀ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለወራት ታስሮ ተለቋል። በአዲስ አበባ ያለዉ እንድምታ «አብዛኛዉ ሰዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መኖሩን የዘነጋዉ ይመስላል» ይላል። አዋጁ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ አካባቢ ሰላም ባያመጣም ፀጥታ አምጥቷልም ይላል።

ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በዶይቼ ቬሌ የዋትስፕ አድራሻ የድምጽ አስተያየታቸዉን የላኩልንም አሉ። ስማቸዉ ያልገለፁት አንዱ አድማጭ፤ አዋጁ በአማራ ክልል በጎንደር አካባቢ ፀጥታን በማምጣት አኳያ ምንም አልቀየረም ይላሉ።

በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ገጽ ላይ፤ ሊሊ ገበረ ዋህድ የተባሉ፤ «አዋጁ ጸረ ሰላሞችንና ተላላኪዎቻቸዉን ልክ ያስገባ ስለሆነ አሁንም ግብአተ መሬታቸው እስኪፈጸም ድረስ ይቀጥላል» ሲሉ፤ አዜብ ቶላ ደግሞ «ዘረኛ መንግሥት በሞት አፋፍ ላይ ነው ያለው፣ ከአሁን በኋላ ያለ አስቸኮይ አዋጅ ሊያስተዳድር አይችልም» የሚል አስተያየታታቸዉን አስፍረዋል።

 

ዘገባው የመርጋ ዮናስና የሸዋዬ ለገሰ ነው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 13, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 13, 2017 @ 12:20 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar