(ዘሐበሻ) በኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን የሰሜን ምእራብ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ያገለግሉ በነበረበት ከሀገረ ስብከቱ ካዝና አንድ ነጥብ ስድስት ሚልየን ብር አጉድለዋል ተብሎ ክስ ሲቀርብባቸው የቆየ ሲሆን አቡነ ዘካሪያስ ይህንን ብር ያጠፉት በወቅቱ የሀገረስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከነበሩት ግለሰብ ጋር የነበረ ሲሆን ከገንዘቡ መጥፋት በኋላ እርሳቸው ወደ አሜሪካ ፤ ሥራ አስኪያጁ ደግሞ ወደ ጂንካ ተዘዋውረው ሲሰሩ ነበር::
አቡነ ዘካሪያስ በዚህ በባከነው አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር ምክንያት በጊዜው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በነበሩት እና በሌሎችም ላይ ክስ በተመሠረተበት ወቅት ተከሳሾች በሰጡት ቃል «መንፈሳዊ አባታችን ስላዘዙን ወጪ አድርገናል» በማለታቸው ብፁዕነታቸው «ኃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ፣ የጠፋውንም ገንዘብም ከምእመናን ልጆቼ ለምኜ እከፍለዋለሁ» ማለታቸው በተለየዩ ሚዲያዎች ቀርቦ ነበር::
አቡነ ዘካሪያስ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በተደረገላቸው መዋጮ ያጠፉትን ገንዘብ ለጎጃም ሃገረ ስብከት የመለሱ ሲሆን እርሳቸውም ከረዥም ጊዜ የኒዮርክ ኑሮ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ይታወሳል::
በአሁኑ ወቅት አቡነ ዘካሪያስ ሃገር ቤት ቆይተው ወደ አሜሪካ ሊመለሱ መሆኑን የተገነዘቡ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ራሳቸውን በማደራጀት ኢትዮጵያ ያለው ኢምባሲ የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ እንዲከለክላቸው የሚጠይቅ ፒትሽን ማሰባሰብ ጀምረዋል::
በፒትሽኑ ላይ በሃገር ቤት እያሉ ስላጠፉት ገንዘብ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል የሚሉ ምክንያቶች ተቀምጠዋል:: በተለይም በአሁኑ ሰአት በችካጎ የምትገኘውን ቅድስት ድንግል ማርያም ደብር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በማስገባታቸው እና በቅድሞው የአትላንታ ቤተክህነት መሪ የነበሩትን እና በጆርጂያ አንፈልጋቸውም ተብለው እንዲባረሩ የተደረጉትን ቆሞስ ለችካጎ በእራሳቸው ስልጣን ከወያኔ አባላቶች ጋር በመተባበር አስቀምጠዋል ተብለው ጥርስ የተነከሰባቸው ሲሆን አሁንም በዚሁ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ውዝግብ የተፈጠረ እየተፈጠረ ያለ ከመሆኑ በላይም ፣ምንም አይነት መፍትሄ ለማምጣት እንዳልተቻለ ታውቆል ፣ እኝሁ ግለሰብ ብጹእ አቡነ ዘካርያስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ጠንቅ እንደሆኑ ህዝበ ምእመናኑ ይመሰክራሉ ።
የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከዘሃበሻ ጋር በመተባበር ይህንን ልዩ ዘገባ በተለያዩ ጊዜያት እየተከታተልን መዘገባችን ይታወሳል ፣በተልይም የችካጎ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አባላቶች ሆነው ከህዝቡ ተነጥለው የቤተክርስቲያኗን ቁልፍ በመቀየር ፣የግል ንብረታቸው ለማድረግ የሞከሩት እነዚሁ የፖለቲካ እስረኞች እና የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች በእኝሁ ግለሰብ ትእዛዝ እንደሚንቀሳቀሱ ፣ ማናቸውንም ነገሮች ያለእርሳቸው ትእዝዝ መፈጸም የለበትም ብለው የሚያምኑ መሆናቸውን ፣ከቅርብ ክትትላችን ካየነው ዘገባ ለመረዳት ችለናል ። በተለያዩ ጊዜያት የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ለመዘገብ ቢገባም ክፉኛ የሆነ ሃይለ ቃላት ከእነዚሁ የወያኔ አባላቶች እና የቤተክርስቲያን አፍራሾች እንደሚደርስበት ለመረዳት ችለናል ። የአቡኑን ፕሪትሽን ለመከታተል ክስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ ።
Average Rating