www.maledatimes.com በጣና ሐይቅ ላይ ኑሯቸውን መሰረት ያደረጉ ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አደጋ ላይ ወድቀዋል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጣና ሐይቅ ላይ ኑሯቸውን መሰረት ያደረጉ ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አደጋ ላይ ወድቀዋል።

By   /   July 13, 2017  /   Comments Off on በጣና ሐይቅ ላይ ኑሯቸውን መሰረት ያደረጉ ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አደጋ ላይ ወድቀዋል።

    Print       Email
0 0
Read Time:49 Second

 

ከ50 ሺህ ሔክታር በላይ የሚሆነውን የጣና ሐይቅ በመሸፈን አደጋ የጋረጠው የእንቦጭ አረም የባህር ዳር ከተማን ጨምሮ በምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብና ሰሜን ጎንደር ዞኖች የሚገኙ ህይወታቸውን ብርጣና ሐይቅ ከሚገኝ የምስኖ እና አሳ ምርት ያደረጉ ዜጎች ላይ መውደቃቸውን መረጃዎች አመላክተዋል። በተለይም የጣና ሐይቅ በሚያዋስናቸው ሰሜን ጎንደር፣ ጎርጎራ፣ አቼራ፣ ደንቢያ፣ ደንቢትና ማክሰኝት አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በተስፋፋው አረም ምክንያት የአሳ ምርቱ በእለት ተእለት በማነሱ ከብቶቻቸው አረሙን ሲበሉ በመጫጫታቸው እና የውሃው መጠን እየቀነስ በመሄዱ ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን ለማወቅ ተችሏል።

በዘርፉ ምርምር ያደረጉ ምሁር ለኢሳት እንደገለፁት ከሆነ በጣና ሐይቅ የተከሰተው ችግር አገራዊ ተደርጎ በመውሰድ አስቸኳይ ርብርብ ማድረግ ካልተቻለ የጣና ሐይቅ እንደ ሐረማያ ሐይቅ ሙሉ ለሙሉ የመድረቅ እጣ ፋንታ ሊያጋጥመው እንደሚችልና በሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አካባቢያቸውን በመልቀቅ ለስደት እንደሚዳረጉ አስጠንቅቀዋል። ተመራማሪው አክለው እንደገለፁት ከሆነ የአዲስ አበባን ያህል ስፋት በሸፈነው የእንቦጭ አረም ምክንያት በሀይቁ ውስጥ ያለው አልሚ ምግብና ውሃ እየቀነሰ በመሄዱ አሳን ጨምሮ በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ህይወት ያላቸው ፍጡራን የመጥፋት አደጋ አጋጥሟቸዋል።

ችግሩ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን ጉዳዩ አገራው አጀንዳ ተደርጎ እንዲውሰድ ቢጎተጉቱም በህወሓት የሚመራው መንግስት ትኩረት መስጠት አለመፈለጉ እንዳሳዘናቸው ተመራማሪው ለኢሳት ገልፀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 13, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 13, 2017 @ 1:23 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar