የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ሃሙስ ሀምሌ 6/2009 ዓም በዋለው ችሎት በኦፌኮው ም/ል ሊ/መንበር በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀረበውን የሽብር ወንጀል ክስ በመቀየር ፣ በወንጀለኛ ህጉ አንቀፅ 257 ሀ ስር የተደነገገውን ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ በይኗል።
በጉርሜሳ አያና መዝገብ ከተከሰሱት መካካል ከ ተራ ቁጥር አንድ እስከ 13 የተካተቱት ተከሳሾች የቀረበባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ተቀይሮ መገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት በሚለው የጸረ ሽብር አዋጅ አንቀጽ 7/1 እንዲካለከሉ በይኗል።
ተከላከሉ ከተባሉት ውስጥ ጉርሜሳ አያና፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ አብደታ ነጋሳ፣ ፣ ገላና ነገራ፣ ጌቱ ግርማ፣ በየነ ሩዳና ተስፋየ ሊበን የሚገኙ ሲሆን፣ ጭምሳ አብደሳ፣ ፍራኦል ቶላ፣ ጌታቸው ደረጀ እና አሸብር ደሳለኝ ደግሞ ከክሱ ነጻ ተብለዋል።
ከ14 እስከ 22 ባለው ተራ ቁጥር የተቀመጡት ደረጀ መርጋ፣ የሱፍ አለማየሁ፣ ኢካ ተክሉ፣ ገመቹ ሻንቆ፣ መገርሳ አስፋው፣ ለሚ ኢዴቶ፣ አብዲ ታምራት እና አብዲ ኩምሳ ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው አንቀጽ 7(1) ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።
አቶ በቀለ ገርባ እንዲከላከሉ የተጠቀሰባቸው አንቀጽ እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር የሚያስቀጣ ቢሆንም የዋስትና መብትን ግን አይከለክልም። አቶ በቀለ ዋስትና እንዲፈቀድለት በጠበቆቹ በኩል ጥያቄ አቅርቦ የነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ‹‹በፅሁፍ አስገቡ›› የሚል ትእዛዝ በመስጠት በእለቱ ውሳኔ ሳይሰጥ አልፎታል፡፡
ፍርድ ቤቱ ከሃምሌ 8-12 ጊዜ ውስጥ የመከላከያ ምስክሮችን ይሰማል ተብሎ ይጠበቃል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating