ከቬሮኒካ መላኩ
ዛሬ ብአዴን የተባለው ድርጅት አስገራሚ እና ለመዋጥ እጅግ የሚከብድ መራራ ሀቅ ይዞ ወጥቷል ። ብአዴን የተናገረው እንደወረደ ሲቀርብ << በአማራ ክልል ውስጥ በደርግ ጊዜ ከተተከሉ የኤሌክትሪክ ማሰራጫዎች ውጭ ምንም አይነት አዲስ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ባለፉት 25 አመታት አልተሰራም >> ይላል። ይሄን አይነት የኢኮኖሚ አፓርታይድ እና “ባንቱስታይዜሽን ” በኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩን ሁሉም ህዝብ አውቆ ለአመታት ሲፅፍና ሲናገር የኖረ ቢሆንም ይሄ መራራ ሀቅ ከብአዴን ሲነገር ያስገርማል።
…
ብአዴን ዛሬ ሃቁን ቢተነፍሰውም ይሄን ጉዳይ የአማራ አርሶ አደር ከ20 አመታት በፊት ተናግሮ ነበር ።
ገና ከጅምሩ አማራ ክልል ከሚገኘው የሀይል ማሰራጫ ተነስቶ የአማራ ክልል ከተሞችን በድቅድቅ ጨለማ ውጦ እያለፈ ሄዶ ለትግራይ ሃያ አራት ሰአት ኤሌክትሪክ ሲሰጥ የታዘበው የአማራ አርሶ አደር በራሱ ቀበሌ የሚያልፈውን የኤሌክትሪክ ግንድ እየቆረጠ ማረሻ ሰራበት ። በዚህ የተበሳጩት ወያኔዎች የመብራ ፖሉ በሚያልፍበት እያንድንዱ የአማራ ገበሬ ደጃፍ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ህግ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፥፥ ይኸውም ከዚያን ግዜ ጀምሮ አንድ የመብራት ፖል ቢወድቅ በአቅራቢያው ያለው ገበሬ ቤትና በሬ ተሸጦ ለመብራት ሃግል ገቢ ይሆናል የሚል ነበር ።ከዚያን ግዜ ጀምሮ የጎጃምና የጎንደር ገበሬ ክረምት ከበጋ በተራ በተራ እየወጣ ግንዱን ሲጠብቅ ያድራል።
ታዲያ በደረቀ ሌሊት ተገትሮ ያዩት ሰዎች ” ጨለማ ውስጥ ምን ታደርጋለህ ?”ብልው ሲጠይቁት
” መቀሌን እራት እያበላሁ ነው !” ብሎ በሚያምር ቅኔ ይሄን ገደብ የለሽ አፓርታይድ ገልፆታል ።
…
ዛሬ ትግራይ በመሠረተ ልማት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ እና በቢዝነስ ከኢትዮጵያ ግንባር ቀደም መሆኗን በመስማት ሳይሆን አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ትግራይ ውስጥ ያልተገነባ ፋብሪካ የለም፡፡ ወጣቱ ትግራይን ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ እንዲያመጣ በመላው ኢትዮጵያ ተሰማርቷል፡፡ ትግራይ ውስጥ ያሉ አዛውንት እና መከላከያ ሠራዊት ብቻ ናቸው፡፡ ኤፈርት የተባለው የህወሀት የኢኮኖሚ ድርጅት ሀብት በአፍሪካ ተወዳዳሪ እንደሌለው አቦይ ስብሀት በአሜሪካ ድምጽ ቀርበው መስክረዋል፡፡ አሁን ያለማጋነን በኢትዮጵያ የትግራይ ሀብት ድርሻ ከ50 ፐርሰንት በላይ ነው፡፡ በእርግጥ የኤፍርት ሀብት ምንጭ ኢትዮጵያ ናት ትግራይ አይደለችም፡፡
…
ዋናው ጉዳይ ችግሩን ማውራት ብቻ ሳይሆን ዋናው መመለስ ያለበት ጥያቄ ” ይሄ እጅግ አስከፊ የአንድ ጎሳ ባንቱስታይዜሽን እንደት ሊስተካከል ይችላል? ” የሚለው ነው ።
እኔ የማምንበት መፍትሄ
አለማችንን የ 1 ሺህ አመታት ታሪክ ያጠኑት የስታምፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ዋልተር ሺዴል ያቀረበው የተዛባና አድሎአዊ የኢኮኖሚ ፍትህና ፣ ፖለቲካዊ ቀያሪ መዘውሮች ናቸው ።
ፕሮፌሰሩ እንዳረጋገጠው እንደዚህ ያለ ስር የሰደደ አድሏዊ ስርአት የሚያስተካክሉት :
1 ጦርነት
2~ አብዮትና ፖለቲካዊ ለውጥ፣
3~ የመንግስት መፍረስ
4 ~ ወረርሽኝና በሽታ ናቸው ይላል ( 4ኛውን እኔ አላምንበትም)
እነዚህ ነገሮች ነባራዊውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስርአት በመቀየር በአለም ማህበረሰብ እኩልነት ያሰፍናሉ ብሏል ።
ኢትዮጵያም ውስጥ እንደ ወያኔ ያለውን ይሉኝታ ቢስ ለአንድ ጎሳ የቆመ ስርአት የምትገላገለው በጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ከላይ ፕሮፌሰሩ ባስቀመጡት የስር ነቀል ለውጥ መሳሪያዎች ብቻ ነው።
Average Rating