www.maledatimes.com የግብር አሰባብሰብ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ክልሎችም ይቀጥላሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የግብር አሰባብሰብ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ክልሎችም ይቀጥላሉ

By   /   July 24, 2017  /   Comments Off on የግብር አሰባብሰብ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ክልሎችም ይቀጥላሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 3 Second

በመዲናችን አዲስ አበባ እና በክክል ከተሞች የተካሄደው የቀን ገቢን አስልቶ የተተመነው የታክስ (ግብር አሰባሰብ ስርአት የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እንንደሚያመጣ ተፈረⶆል ። እንደ አንዳንድ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አገላለጽ ከሆነ መንግስት ይህንን ያህል ጫና በማህበረሰቡ ላይ ልጭን የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በእራሱ በመንግስት ባለስልጣናት በስውር የተመዘበሩ ገንዘቦችን በህዝቡ ላብ ሊተካው ስላሰበ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ።

በተለይም በክልሎች የተነሳው አድማ በተለያዩ ከተሞች መዛመቱ አሁንም አዲስ አበባን መጨመሩ መንግስትን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሎታል ሲሉ ምንጮቻችን ገልጠዋል ። የግብር አሰባብሰብ ሂደቱ ትክክል ባለመሆኑ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ሌሎች  ክልሎችም ይቀጥላሉ ፣ይህ መንግስት ፋታ እስካልሰጠን እና ስር አታዊ አስተዳደር እስካላመጣ ድረስ ወደ ስራችን አንመለስም ፣እረሃቡን እና ችግሩን እንደሆነ ተላምደነዋል ፣ድሮም እየተራብን ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ነበር የምንኖረው አሁንም እንኖረዋለን ሲሉ ወይዘሮ አስካለ ደርሰህ ከመገናኛ ጠቁመዋል።

በአሁን ሰአት የመርካቶ ነጋዴዎች ወደ ኪሳራ እንዲዳረጉ ተደርገው ፣የቀድሞው መገናኛ እና ሃያ ሁለት አካባቢ በአዲሱ ስሙ ትግራይ ሰፈር ከፍተኛውን የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት መንደር እንደሆነ እና የተለያዩ የውጭ ምንዛሬዎች በትግራይ ተወላጅ ሱቆች ውስጥ እንደሚካሄድ እና መንግስት ይህንን እያወቀ ምንም እንዳላዘጋቸው ሆኖም ግን የሌሎች ማህበረሰቦችን በማዘጋት እና ንብረታቸውን በመውረስ እስከሞት የዳረጋቸው እንደነበሩ የሚታወስ ነው ፣ በአንድ ሃገር ሁለት አይነት ዜግነት ኖሮን ነው የምንኖረው ሲሉ ወይዘሮ አስካለ የውስጥ ስሜታቸውን እንባ እየተናነቃቸው ገልጸዋል ።

የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ግን ይህ ሊሆን አይገባውም ሲሉ የተነተኑ ሲሆን ፣ የቀን ገቢያቸው አነስተኛ ናቸው ከሚባሉት ማህበረሰቦች ላይ ዝርፊያ ከሚያካሂድ ይልቅ ፣ በሃገሩ ውስጥ አስገብቶአቸው በግብርናውም ዘርፍ ይሁን በውጭ እና በውስጥ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩትን የውጭ ኩባንያዎችንም ሆነ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጥሩትን እንደነ ትምኒት ላይ ከፍተኛ ጫና ቢያደርግ ያሰበውን ገንዘብ መመለስ ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

በተለይም በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች በእያንዳንዳቸው ከ500 በላይ ቅርንጫፎችን ይዞ በግዙፍነቱ የሚታወቀው ድርጅት ስታርባክስ ነው ፣ይህ ድርጅት ከፍተኛውን ቡና የሚያስገባው ከኢትዮጵያ ነው ፣ከኢትዮጵያ ገበሬ በ0.5 ሳንቲም የአሜሪካን የገንዘብ መጠን ከኢትዮጵያ ገበሬ ይገዛል ፣አንድ ቡና በኩባያ $2.53 በዶላር ይሸጣል ፣ ይህ ማለት ከአንድ ኩንታል ቡና ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ያፍሳል ፣ የእኛ ደሃ ገበሬ ድህነቱን ታቅፎ ፣የሃገሬ መንግስት ከውጭ ባለሃብት ጋር ተመሳጥሮ ደሃ ገበሬውን ይበዘብዛል ሲሉ ይገልጣሉ ።

በሌላም በኩል ሲጠቁሙ የአበባ ምርት አምራች ገበሬዎች በሃገሪቱ ውስጥ አምርተው ለውጭ ገበያ ሲያቀርቡ 2 እግር አበባ ከ$8.00 የአሜሪካ ዶላር እስከ $16.00 የአሜሪካ ዶላር ያወጣል ይህ ማለት ደግሞ የሃገሬውን ህዝብ ጉልበት እና የመሬት ልማት ማልማት አቅሙ ተበዝብዞ የሚከፈለው የቀን ገቢ ሲነጻጻር የሰው ጉልበትም ሆነ አንጡራ ሃብት በነጻ እንደመውሰድ ይቆጠራል ፣ ይህንን ማነጻጸር እና የቀን ገቢ በጀት መበጀት ያቃታቸው እነዚሁ ትምህርት የሌላቸው የግብር ተንታኞች ህዝቡን ያጎሳቁላሉ ፣ መንግስት ግብር መሰብሰብ የሚገባው ከሆነ ከፍተኛ ጥናት አድርጎ በውጭ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛውን ትኩረት በመሳብ ኢሆን ይገባዋል ሲሉ ጠቁመዋል።

በመርካቶ የሚገኙ ሱቆች አብዛኛዎቹ ተዘግተዋል ምክንያቱ የቀን ገቢ ግምቱ ነው ተብሏል፡፡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በበኩሉ የተወሰኑ ሱቆች በመክፈት ላይ ናቸው ብሏል,

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 24, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 24, 2017 @ 8:46 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar