www.maledatimes.com ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን አግኝቶ ስለግንቦት 7D ሳይጠይቃቸው ቀረ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን አግኝቶ ስለግንቦት 7D ሳይጠይቃቸው ቀረ?

By   /   October 24, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 2 Second

(ከሮቤል ሔኖክ) ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም የቀድሞው የአዲስ ዜና ጋዜጣ አዘጋጅ አሁን በአምስተርዳም በቴሌቭዥን አዘጋጅነት እየሠራ ይገኛል። ጋዜጠኛው ዛሬ በዩቲዪብ በኩል ለሚሰራበት ቲቪ ያዘጋጀውን  ከግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ አቅርቧል። 1፡20፡08 በፈጀው በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ዶ/ር ብርሃኑን በወቅታዊው የሙስሊሞች ጥያቄ ዙሪያ ሰፊ ጥያቄ አንስቶ አቅርቦላቸዋል።  ዶ/ር ብርሃኑም መለሰዋል። ሆኖም ግን እኔ የዶ/ር ብርሃኑን ቃለምልልስ በዩቲዩብ ላይ ቀርቦ ሳይ የጠበቅኩት ጥያቄ አለመኖሩ በጣም ገርሞኛል። ከሰሞኑ ከግንቦት 7 የወጡ ሰዎች (አንድም ይሁኑ 3) በየሚዲያው እየቀረቡ ግንቦት 7 D የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸውንና ለምን ይህን ድርጅት ሊለቁ እንደቻሉ ሲናገሩ ነበር። ይህን በማስመልከት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መልስ ይስጡበት የሚል አንድ ጽሁፍ ለመጻፍ እያሰብኩ ባለሁበት ወቅት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ዛሬ በዩቲዩብ የሳቸውን ቃለምምልስ ይዞ ቀረበ። በቃለ ምልልሱ ላይ ግን ስለ ግንቦት 7 ዲ ሳይጠይቃቸው እንደቀረ ነው ይህ የ 1፡20፡08 ቪድዮ የሚያሳየው።
ታዲያ ይህ ጥያቄ አለመነሳቱን ሳይ እንደ ነጻ ጋዜጠኝነቴ የተወሰኑ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ላይ መጡ።
1ኛ. ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም የግንቦት 7 ዲ መፈጠሩን አልሰማ ይሆን?
2ኛ. ዶ/ር ብርሃኑም እንደ አቶ መለስ ይህኔን ጥያቄ ልጠየቅ ይህን አልጠየቅ ብለው ጥያቄ አውጥተው ለጋዜጠኛው ሰጥተው ይሆን?
3ኛ. ምናልባት ስለግንቦት 7 ዲ የጠየቃቸው ጥያቄን ለዜና አስቀምጦት ይሆን?
4ኛ. ዶ/ር ብርሃኑ ስለ ግንቦት 7 ዲ ከመለስኩኝ እውቅና እንደሰጠኋቸው ይቆጠርብኛል ብለው ይሆን?
5ኛ. በተለይ ዶ/ር ብርሃኑ ከአማራ ህዝብ ጋር በተያያዘ በግንቦት 7 ዲ በኩል “ዶ/ር ብርሃኑ ለንድን ላይ አንድጊዜ “የትግሬን አምባገነን በአማራ አምባገነን” መተካት አልፈልግም አይነት ንግግር ተናረዋል” እየተባሉ በመወንጀል ላይ ያሉበትን ጉዳይ ጋዜጠኛው አለማንሳቱ እርሳቸውም መልስ አለመስጠታቸው እንታገልለታለን የሚሉትን ዴሞክራሲ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው።
6ኛ. ኢሕ አዴግን ስለምንቃወም ተቃዋሚ ፓርቲዎች መተቸት የለባቸውም ብለን እናስብ ይሆን?
7ኛ. ዋነኛው ጥያቄዬ ግን ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን አግኝቶ ስለግንቦት 7D ሳይጠይቃቸው ቀረ?
ሌሎቹን ጥያቄዎች ለትዝብት ትቼዋለሁ።
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ከዩቱትዩብ አግኝቼዋለሁ፤ እነሆ-

ESAT Yesamintu Engida Dr. Berhanu Nega October 2012 Ethiopia

http://www.youtube.com/embed/451rxtWZcfo

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 24, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 24, 2012 @ 8:34 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን አግኝቶ ስለግንቦት 7D ሳይጠይቃቸው ቀረ?

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar