www.maledatimes.com ‹‹በደረሰብኝ ድብደባ ግራ ጆሮዬ መስማት ተስኖታል›› ዳንኤል ሺበሽ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹በደረሰብኝ ድብደባ ግራ ጆሮዬ መስማት ተስኖታል›› ዳንኤል ሺበሽ

By   /   July 26, 2017  /   Comments Off on ‹‹በደረሰብኝ ድብደባ ግራ ጆሮዬ መስማት ተስኖታል›› ዳንኤል ሺበሽ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 7 Second

#Ethiopia #HumanRights #FreeDanielShibeshi

ስም፡- ዳንኤል ሺበሺ ከምሮ
ዕድሜ፡- 41
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፋኝነት ምክንያት እንደታሰርሁ ነው የማምነው፡፡ ለእስር የሚያበቃኝ ወንጀል የሰራሁ ሆኜ አልነበረም ለእስር የበቃሁት፡፡
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- በፌደራል አቃቤ ህግ የቀረቡ፣ ሁለት ክሶች አሉብኝ፡፡ አንደኛው ቀደም ሲል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 4 መተላለፍ በሚል የተከሰስሁበትና በኋላ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ የተባልሁበት ሲሆን፣ አቃቤ ህግ ይግባኝ ብሎ ጠ/ፍርድ ቤት አንቀጹን በመለወጥ የአዋጁን አንቀጽ 7(1) መተላለፍ ተከላከል ተብዬ ወደ ከፍተኛው ፍ/ቤት ተመልሼ ጉዳየ እየታየ ነው፡፡ ሁለተኛው ክስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2009 አንቀጽ 2 መተላለፍ የሚል ክስ ነው፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡
1. ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡ በዚህ ምክንያት ግራ ጆሮየ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡
2. ሌሊት ሌሊት ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡
3. ጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ታስሬ ነበር፡፡
ጠያቂ ተከልክያለሁ፡፡
4. ህክምና እንዳላገኝ ተደርጌያለሁ፡፡
5. ፍርድ ቤት ሳልቀርብም ሆነ የታሰርኩበት ምክንያት በግልጽ ሳልሰማ ለስድስት ወራት ታስሬያለሁ፡፡

የኋላ ታሪክ
የተወለድሁት ደቡብ ክልል ጋሞ ምድር ነው፡፡ ባለትዳር ነኝ፡፡ ቀደም ሲል በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እሰራ ነበር፡፡ በፖለቲካ ተሳትፎዬ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ነበርሁ፡፡ በዚህ ፓርቲ ውስጥ የፓርቲው ምክትል አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ ነበርሁ፡፡ከመጀመሪያው እስሬ በፊት በፖለቲካ ተሳትፎዬ በተለይ የቁጫ ህዝብ የማንነትና የመብት ጥያቄ ሲያነሳ ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ ህጋዊና ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኝ የተቻለኝን ህጋዊ ስራ ስሰራ ነበር፡፡

የEthiopia Human Rights Project ምስል
ይውደዱተጨማሪ የስሜት መግለጫዎችን አሳይ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 26, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 26, 2017 @ 10:38 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar