0
0
Read Time:28 Second
(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በምሳ ሰዓት አካባቢ አንድ የሕወሓት መንግስት ፒክ አፕ መኪና በ እሳት መውደሟ ተዘገበ::
እንደ ዜና ምንጮች ገለጸ ይህን መኪና ያወደሙት በአምቦ በሕቡዕ የሚንቀሳቀሱት ወጣቶች (ቄሮዎች) ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል:: በይፋ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ይህች በጤና ጥበቃ ስም የምትንቀሳቀሰው መኪና የሕወሓት ሰላዮችን እና ወታደሮችን ለማመላለሻ መጠቀሚያነት መዋሏ ስለተደረሰበት ነው የሚሉ የዜና ምንጮች ከአምቦ አካባቢ ዘግበዋል::
የሕወሓት መንግስት የጤና ጥበቃ የቀይመስቀል እንዲሁም የሌሎች ድርጅቶችን ስም በመኪኖች ላይ እየለጠፈ በየከተማው ስለላ እንደሚያደርግ ከዚህ በፊት መጋለጡ አይዘነጋም::
በአምቦ መኪናዋ በ እሳት ስትጋይ በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ለማጣራት ሞክረን አልተሳካልንም::
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating