0
0
Read Time:42 Second
(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዘገባ የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ሳሌም ከበደ መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል:: ወ/ሮ ሳሌም ከቀድም ባለቤታቸው የወለዱትን ልጃቸውን ድረው መልሱን ሳይበሉ ዘብጥያ የወረዱ ሲሆን ባለቤታቸው አባይ ጸሐዬ የፖለቲካ ስልጣናቸውንና እርሳቸውን የሚደግፉ ሕወሓቶችን በማስተባበር ሚስታቸው እንዲፈቱ አድርገው የነበረ ቢሆንም ከሰዓታት ፍቺ በኋላ ወ/ር ሳሌም ዳግም ዘብጥያ መውረዳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት አብዛኞቹ ነጋዴዎች ከአባይ ጸሐዬ ጋር የንግድ ንክኪ ያላቸው ናቸው:: አባይ ጸሐዬ የተለያዩ ጀነራሎች ጋር በመደወል ሚስታቸውን ለማዳን ቢጥሩም እንዳልተሳካላቸውና እርሳቸውም ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
አባይ ጸሐዬ በሕወሓት መንግስት ውስጥ የፖለቲካ ስልጣን እንጂ ሃይል ያለው ስልጣን የለውም የሚሉት የዘ-ሐበሻ የፖለቲካ ተንታኞች ሃይል ያለው የነደብረጽዮን (ስብሃት ነጋ) ቡድን እንደሆነና ይህም የአባይ ጸሐዬን ቡድን እያሽመደመደው መሆኑን ይገልጻሉ:: በተለይም የነብርሃኔ ገብረክርስቶስ ወደ ቻይና በአምባሳደርነት መሄድ ከዚሁ በሕወሓት ውስጥ ከተፈጠረው ግብ ግብ ጋር የተያያዘ ነው ይላሉ::
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating