www.maledatimes.com በአዲስ አበባ ግብረሰዶማውያን አዳራሽ ተከራይተው ሰርግ መደገስ ደረጃ መድረሳቸው ታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአዲስ አበባ ግብረሰዶማውያን አዳራሽ ተከራይተው ሰርግ መደገስ ደረጃ መድረሳቸው ታወቀ

By   /   July 31, 2017  /   Comments Off on በአዲስ አበባ ግብረሰዶማውያን አዳራሽ ተከራይተው ሰርግ መደገስ ደረጃ መድረሳቸው ታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 7 Second

Source #BBN


በአዲስ አበባ ግብረሰዶማውያን አዳራሽ ተከራይተው ሰርግ መደገስ ደረጃ መድረሳቸው ታወቀ

በአዲስ አበባ ግብረሶዶሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ ሲሆኑ አዳራሽ ተከራይተው ሰርግ መደገስ ደረጃ ድረስ መድረሳቸውን ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይም በፒያሳ እና ቦሌ አካባቢ በስፋት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
አዳራሽ እና የሰርግ መኪና ተከራይተው ሰርግ ሲደግሱ የገዢው መንግሰት ባለስልጣናት የሚያቁ ቢሆንም ትኩረት ባለመስጠት እንደማያቁ እንደሚሆን ከታማኝ ምንጭ ባገኘነው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ብዙ ጊዜ አዳራሹን የሚያከራዩት የህወሀት ሰዎች ንብረት የሆኑ ሆቴሎች እና ህንፃዎች እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ከ14 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ወንዶች ልጆች በተደጋጋሚ በግብረሰዶሞች የመደፈር አደጋ የሚያጋጥማቸው ቢሆንም በመንግስት በኩል ምንም አይነት ትኩረት እንዳልተሰጠው ታውቋል፡፡ ከሶስት አመት በፊት አስኮ በሚገኘው ሚኪላንድ ኮንዶሚነየም ስድስት ወንድ ህፃናትን ደፍሯል ተብሎ በቁጥጥር ስር ቢውልም በመንግስት በኩል ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጠበት ተገልጿል፡፡
በማህበረሰቡ ዘንድም ልጆቻቸው የመደፈር አደጋ ሲያጋጥማቸው ነገሩ አደባብሰው ከማለፍ ውጪ ጉዳዩን ወደ አደባባይ አውጥተው ፍትህ ለማግኘት እንደማይጥሩ ባገኘነው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ወላጆች ልጆቻች የመደፈር አደጋ አጋጠማች ብለው ወደ አደባባይ ቢወጡ በመንግስት በኩል ትክክለኛ ፍትህ አናገኝም ብለው የሚያስቡ ሲሆን በህብረተሰቡ ዘንድም ከፍተኛ የሆነ የመገለል ችግር ያጋጥመናል ብለው ስለሚሰጉ ጉዳዩን አፍነው መያዝን ይመርጣሉ ሲሉ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ያስረዳሉ፡፡
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በነበሩበት ወቅት የአለም የHIV ኤድስ ቀን በኢትዮጵያ በሚከበርበት ወቅት ግብረሶዶሞች በጁፒተር ሆቴል መብታችን ይከበር በሚል የተሰበሰቡ ሲሆን የሁሉም እምነት የሀይማኖት አባቶች እነሱን በመቃወም በኢትዮጵያ ሆቴል ተሰብስበው ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ ባሉበት ወቅት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ትእዛዝ በፖሊስ እንዲታገዱ መደረጉ ይታወቃል፡፡
ያነጋገርነው አስተያየት ሰጪ ሲያስረዳ ‹‹ ህወሀት ትውልድን የሚያመክኑ ነገሮችን በሀገሪቱ እንዲስፋፋ ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ነው ግብረሰዶሞች ሰርግ እስከ መሰረግ ደረጃ ደርሰው በዝምታ የሚያልፋቸው፡፡ መብቴ ይከበር ብሎ በአደባባ የወጣውን ህዝብ ግን በጥይት ግባሩ ብሎ ይገድላል›› ሲል ሀዘን እና ቁጭት በተሞላበት ሁኔታ አስተያየቱን ገልጿል፡፡
ኢህአዲግ መራሹ መንግስት በተደጋጋሚ ከምሳራቅ አፍሪካ ካሉ መሪዎች የተሻለ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሆኖም እንደ ኬንያ ያሉ ሀገሮች ደግሞ ግብረሶዶምን በተመለከተ ድርድርም ሆነ ርህራሄ የላቸው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ አንድ ሰው ግብረሶዶም መሆኑ ከታወቀ አንገቱ ላይ ጎማ አስገብተው እስከ ማቃጠል ይደርሳሉ፡፡
በ2015 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ኬንያን በጎበኙበት ወቅት ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሀገሪቱ የግብረሶዶሞች መብት እንዲከበር እንዲፈቅዱ ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹ እኛ ከአሜሪካኖች ልንጋራቸው የምንችለው ባህል ዲሞክራሲን ፤ ስራ ፈጠራን ፤ የትምህርት እድሎች ፤ የሴቶች መብትን በተመለከተ እንጂ ይሄ የኛ ባህልም ሆነ የሚያሳስበን ጉዳይ አይደለም›› የሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ ነበር የሰጡት፡፡
ሆኖም በተመሳሳይ ወቅት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ባመሩበት ወቅት በይፋ ጥያቄውን አቅርበው ቢሆን ኖሮ ገዢው መንግስት ለሚያገኘው ፍርፋሪ እርዳታ ሲል ጥያቄውን በደስታ ይቀበል ነበር፡፡ በማለት አስተያየት ሰጪዎቻችን ያስረዳሉ፡፡
እንደሚያሳየው ኢህአዲግ መራሹ መንግስት ለሱ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ የሚያሳስበው ህዝቡ ጭቆና በቃኝ ብሎ የሚያደርገው ህዝባዊ ተቃውሞ እንጂ ሀይማኖትን ፣ ባህልን ፣ ትውልድን የሚያጠፋ ችግሮች ለነሱ ቦታ እንደሌላቸው ነው፡፡ እንዲያውም በስፋት እንዲስፋፉ የሚፈልጋች ጉዳይዎች እንደሆኑ የፓለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 31, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 31, 2017 @ 8:11 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar