www.maledatimes.com አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ) ከዚህ ዓለም በ94 ዓመታቸው ተለዩ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ) ከዚህ ዓለም በ94 ዓመታቸው ተለዩ።

By   /   July 31, 2017  /   Comments Off on አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ) ከዚህ ዓለም በ94 ዓመታቸው ተለዩ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 6 Second
    አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ) ከዚህ ዓለም በ94 ዓመታቸው ተለዩ።

አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ(አባባ ተስፋዬ) ከዚህ ዓለም በ94 ዓመታቸው ተለዩ።  ከስድሳ አመታት በላይ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ፣ሀገር ፍቅር፣ሲኒማ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ሬዲዮ እንዲሁም በድምፃዊነት ያገለሉት አንጋፋው አርቲስት ፣የአሰማት ተጨዋች ፣ህፃናትን አስተማሪና አጫዋች የነበሩት አባባ ተስፋዬ ሳህሉ በ94 አመታቸው መለየታቸውን ከጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን  ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል ። አባባ ተስፋዬ ያለምንም ድርድር ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ የልጆች ክፍለ ጊዜ ልዩ ዝግጅት ፕሮግራምን አቋርጠው እንዲወጡ እስከ ተገደዱበት ድረስ በትጋት ብዙሀኑን ማህበረሰብ ሲያስደስቱ እና ሲያስተመሩ ኖረዋል “አባባ ተስፋዬ”  ።                                 ከዚያም በኃላ ጎዳና ላይ መፅሀፎችንና ካሴቶችን በመሸጥ ቢተዳደሩም በሰይፉ ፋንታሁን ሾው እርዳታ መሰረት አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ አድርገዋቸው ነበር!  አባባ ተስፋዬ 94ኛ አመታቸውን በቅርብ ወራት ያከበሩ ሲሆን ከእርጅናው ጋር የነበራቸውን በሽታ መቋቋም እንዳልቻሉት የደረሰን ዘገባ ያመለክታል! 

አባባ ተስፋዬ አንድ ሙሉ የሙዚቃ ዘፈን አልበም በብሄራዊ ቴአትር በሚሰሩበት ዘመን በ1960 መዝፈናቸውን እና ለህዝብ ማበርከታቸውን የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ አክሎ ይገልጣል ።

 

 

 

 

 

ደህና ሁኑ ልጆች! / RIP

***
ጤና ይስጥልኝ ልጆች! … የዛሬ አበባዎች፤ የነገ ፍሬዎች! … እንደምን አላችሁ ልጆች! … አያችሁ ልጆች! … የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅት እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰዓቱ ይገኛል።

አባባ ደሞ የልጆች ሰዓት እንዳያልፍባቸው በሩጫ ዲ ዲ ዲ ከተፍ ፤ እናንተ ደግሞ ቆማችኃል። ይሄ በጣም ጥሩ ነው ልጆች። አንድ አባት ሲመጣ በአክብሮት መነሳት አስፈላጊ ነው ።

***
ደህና ሁኑ ልጆች! …
ደህና ሁኑ ልጆች!
ደህና ሁኑ ልጆች!

***
ነፍስ ይማር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 31, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 31, 2017 @ 8:33 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar