በቀጣዩ ሳምንት እንደሚደረግ በሚጠበቀው የኬንያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቁ የነበሩት የምርጫ ኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ተገድለው መገኘታቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዛሬ አስታውቀዋል፡:
===============
ከጥቂት ቀናት በፊት መጥፋታቸው ተነግሮላቸው የነበሩት የምርጫ ኃላፊው ክሪስቶፈር ምሳንዶ ሞርጉ በተባለች ከተማ አንገታቸውና ጭንቅላታቸው አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሞተው መገኘታቸውን ሊቀመንበሩ በሐዘን ተውጠው ተናግረዋል፡፡የኃላፊው ተገድለው መገኘትም በምርጫው ላይ መጥፎ የሆነ ምስል እንደሚፈጥር ተገምቷል፡፡
‹‹የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ቺቡካቲ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት ‹‹የኮሚሽኑን ሰራተኛ ማንና ለምን እንደገደለው ማወቅ እንፈልጋለን፡፡መንግስት ለሁሉም የኮሚሽኑ አባላት ጥበቃ እንዲሰጥም እንጠይቃለን››ብለዋል፡፡
ተገድለው የተገኙት ሓላፊ በኮሚሽኑ የኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ተመድበው ይሰሩ ነበር፡፡በምርጫው ወቅትም እርሳቸው የሚመሩት ዲፓርትመንት የመራጮችን ድምጽ ከስርቆት ለመታደግ የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኤሎክትሮኒክስ ዘዴ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለመቆጣጠር ተዘጋጅቶ ነበር፡፡
በኬንያ የሚገኙ የአሜሪካና የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች የባለስልጣኑ መገደል እንዳሳዘናቸው በመግለጽ መንግስት በአስቸኳይ የግድያቸውን ምስጢር እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡
በኬንያ ምርጫውን ተከትሎ የሚሰማው ነገር ከቀን ወደቀን የተለየ መልክ እየያዘ በመሆኑ በአገሪቱ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን የጭንቀት ህይወት መምራት ጀምረዋል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating