www.maledatimes.com ‹‹እጅና እግሬን ከእንጨት ጋር ታስሬ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ›› ክበር አለማየሁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹እጅና እግሬን ከእንጨት ጋር ታስሬ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ›› ክበር አለማየሁ

By   /   August 1, 2017  /   Comments Off on ‹‹እጅና እግሬን ከእንጨት ጋር ታስሬ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ›› ክበር አለማየሁ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

ስም፡- ክበር አለማየሁ

ዕድሜ፡- 36

አድራሻ፡- ምዕራብ ጎጃም፣ ማንኩሳ

አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ እስር ቤት

ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለፖለቲካ ለውጥ በሚታገለው መኢአድ ፓርቲ አባል ሆኜ በማደርገው የፖለቲካ ተሳትፎ ምክንያት ለእስር ተዳርጌያለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- በፌደራል አቃቤ ህግ በይፋ የተመሰረተብኝ ክስ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) መተላለፍ የሚል ሲሆን፣ በዋናነት የአርበኞች ግንቦት ሰባት የሽብር ድርጅት ውስጥ ተሳትፎ አለህ የሚል ይዘት ያለው ክስ ነው ያቀረቡብኝ፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡

ሀ. በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የደረሰብኝ የመብት ጥሰት

ጨለማ ክፍል ውስጥ ለአንድ ወር ታስሬያለሁ።
ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፤ ብልቴን የሚጎዳ ድርጊት ተፈጽሞብኛል፡፡
በደረሰብኝ ድብደባ የተጎዳ አካሌን እንዳልታከም ተደርጌያለሁ፡፡
ማንነትን ላይ የተመሰረተ ጸያፍ ስድብ ተሰድቤያለሁ፡፡
ሌሊት ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡
ለ. ቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰብኝ የመብት ጥሰት፣

እጅና እግሬን ከእንጨት ጋር ታስሬ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ፡፡
ቤተሰብ እንዳይጠይቁኝ ተከልክዬ ለሳምንታት እንድቆይ ተደርጌያለሁ፡፡
ከወንበር ጋር ታስሬ ውስጥ እግሬን ተደብድቤያለሁ፡፡
ዛቻና ማስፈራሪያ በተደጋጋሚ ደርሶብኛል፡፡
የኋላ ታሪክ:

የመኢአድ ፓርቲ አባል ነኝ፡፡ በምዕራብ ጎጃም የመኢአድ አባላትን በመመልመልና በማደራጀት ህጋዊ የፖለቲካ ስራ እሰራ ነበር፡፡ ጎጃም ሳለሁ በንግድና በግብርና ስራ ቤተሰቤን እመራ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በምኖርበት አካባቢ የመኢአድ አባል ስለሆንሁ በመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲበረታብኝ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የተለያዩ ጊዜያዊ ስራዎችን እየሰራሁ ቤተሰቤን በማገዝ ላይ እያለሁ ነው ለእስር የተዳረግሁት፡፡

Image may contain: 1 person, text
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on August 1, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 1, 2017 @ 12:21 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar