0
0
Read Time:40 Second
ስም፡- ባንችአምላክ ፋንታሁን
ዕድሜ፡- 22
አድራሻ፡- ሱሉልታ ከተማ ቀበሌ 02
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ሱሉልታ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- አመጽ ታነሳሻለሽ የሚል ነው፡፡
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- በይፋ ክስ አልመሰረቱብኝም፡፡ ግን በምርመራ ወቅት ክስሽ ለአመጽና ለሁከት የሚያነሳሳ ጽሁፍን ጽፈሻል፣ ጽሁፉንም በትነሻል የሚል ነው፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡
1. ከታሰርሁ አራት ወራት ቢሆነኝም ኮማንድ ፖስቱ ነው ያሰረሽ በሚል እስካሁን ፍ/ቤት አልቀረብሁም፡፡
2. ጠበቃ ለማነጋገር ተከልክያለሁ፡፡
3. ክብርን የሚነኩ ስድቦች ተሰድቤያለሁ፡፡ በሴትነቴ ንቀትና ማንኳሰስ ድርሶብኛል፡፡
4. ተደብድቤያለሁ፡፡
5. ዛቻና ማስፈራሪያ በተደጋጋሚ ደርሶብኛል፡፡
6. ጠያቂ ሳያየኝ እንድቆይ ተደርጌያለሁ፡፡
7. በጠባብ ክፍል ውስጥ ከሌሎች እስረኞች ጋር በብዛት በመታሰሬ በቂ አየርና የጽሐይ ብርሃን እንዳላገኝ ተደርጌያለሁ፡፡
የኋላ ታሪክ:
ለእስር የሚያበቃኝ ወንጀል አልፈጸምሁም፡፡ ከመታሰሬ በፊት በሱሉልታ ከተማ ጽሁፎችን በኮምፒውተር በመተየብ ኑሮየን የምመራና ቤተሰብ የምረዳ ወጣት ነኝ፡፡ መቼ እንደምፈታ መቼ ወደህግ እንደምቀርብ ሳላውቀው በእስር እገኛለሁ፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating