#Ethiopia #HumanRights #QilintoFire #FreeDereje
ስም፡- ደረጀ መርጋ ደበሎ
ዕድሜ፡- 29
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 02
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡– ቂሊንጦ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብርተኝነት ተጠርጥረሃል የሚል ነው፡፡
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- አሁን ላይ ሁለት የሽብር ክሶች አሉብኝ፡፡ አንደኛው በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል መሆን፣ አባላትን መመልመልና ከሽብር ቡድን አመራሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ በሚል ከሰውኛል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ቂሊንጦ እስር ቤትን በማቃጠልና በቃጠሎው ወቅት ለሰዎች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ ናችሁ ከተባሉት ሰዎች መካከል አንደኛው ተከሳሽ ነኝ፡፡ ይህኛውም ክስ የሽብር ክስ መሆኑ ነው፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡
ሀ. ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እያለሁ (በመጀመሪያው ክስ ምርመራ ሲደረግብኝ)
1. ማታ ማታ እየተጠራሁ ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡
2. ከፍተኛ ድብደባ በምርመራ ሰዓት ይፈጸምብኝ ነበር፡፡
3. ጠያቂ ተከልክየ በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስሬያለሁ፡፡
ስድብና ዛቻ ደርሶብኛል፡፡
4. ተገድጄ ቃል እንድሰጥና ቃሉ ላይ እንድፈርም ተደርጌያለሁ፡፡
ለ. ቂሊንጦና ሸዋሮቢት እስር ቤቶች የተፈጸሙብኝ የመብት ጥሰቶች፡-
1. ከፍተኛ ድብደባና ስቃይ ተፈጽሞብኛል፡፡
2. ቂሊንጦን ያቃጠሉ ሰዎች አሉ፣ እነሱ ላይ ትመሰክራለህ እያሉ ቀንና ሌሊት በካቴና አስረው አሰቃይተውኛል፡፡
3. ምግብ ከቤተሰቦቼ እንዳይገባልኝ ተከልክያለሁ፡፡
4. ፖሊስ ለሚጠይቀኝ ጥያቄ በኦሮምኛ መልስ ስሰጥ በግድ የማልችለውን ቋንቋ ካልተናገርህ ተብዬ ተደብድቤያለሁ፡፡
5. የታሰርሁበት ክፍል ቀንና ሌሊት እንዲዘጋብኝ ተደርጌያለሁ፡፡
6. ከሌሎች እስረኞች ጋር በቁርኝት በአንድ ላይ ሌሊት ሳይቀር በካቴና ታስሬ እንዳድር ተገድጃለሁ፡፡
የኋላ ታሪክ: —
ከእስር በፊት በመምህርነት ስራ ተሰማርቼ ኑሮየን የምመራ ነበርሁ፡፡ ሀገር ውስጥ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ለለውጥ በሚታገለው ኦፌኮ ውስጥ አባል ሆኜ እንቀሳቀሳለሁ፡፡ በተለይ በወጣቶች ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡
Average Rating