መቼም ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በዓይነቱ ይለያይ እንጅ እሾህ እየበቀለ አስቸግሯል። ቀናኢ ምእመናንን ከእውነት እንዲሸሹ፣ ፅድቅን የሚሽቱትን ከጽድቅ ጎዳና እንዲወጡ የሚያደርጉ በየቦታው ተሰግስገው ገብተው ብዙወችን እየጎዱ ያለበት ዘመን ነው ለዚህም በችካጎ ደብረ ገነት ቤተ ክርስቲያን ያሉ እናውቃለን የሚሉ አንዳንዶች ብዙዎችን እያሳቱ ይገኛሉ። ወዮ እነርሱን አያድርገኝ። ባትፈጠሩ በተሻላችሁ ነበር።
በባለፉት ሳምንታት አንዳንድ የተባሉ ነገሮችን ስሰማ ገረመኝና ሳቅሁ።
1. ጥፋት አንድ፤ የሃይማኖት ችግር ያለበትን ሰው አምጥተው ቅዳሴ እነዲቀድስ እና እንዲያስተምር አድረጉ።
2. ጥፋት 2 & 3፤ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ ቀን አስተዋዋቂ ነኝ ብሎ ራሱን የሰየመውና ለቤተ ክርስቱያናችን ትልቁ እንቅፋት የሆነው ሰው የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሃይለ ሚካኤል ብሎ ማለቱን ስሰማ ገረመኝ። በዚህም አላቆመም ምን ያመጣሉ እኔ አሸናፊ ነኝ። ከዚህ ኣካባቢ የመጡ ሰዎች አበቃላቸው አለ እየተባለ የከተማ ወሬ ሆኖአል። ለመሆኑ እርሱ ነው የሾማቸው? እኛ እንደ እርሱ እና መሰሎቹ አይደለንም። በህገ እግዚአብሔር እና በሥርዓት የምንመራ ነን። ህግ ከፈረሰ ለእውነት እስከሞት የምንሄድ ሰዎች ነን። ይህንን ደግሞ ካላወቃችሁት ቢቀሰቅሷችሁም የማትነቁ ናችሁ። በህጋችን መሰረት ምዕመኑ ስብስባ ተጠርቶ ተውያይቶ አባ ሃይለ ሚካኤል የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ይሁኑ ካለ በግል ተቃውሞ የለኝም ያለበለዚያ አንተና መሰሎችህ ስለፈለጋችሁ በጉልበት ይሆናል ካላችሁ አስተዳዳሪህ እንዲሆኑ ሌላ ቦታ ይዘህ መሄድ ትችላለህ። እዚህ ኮማንድ ፖስት የለም አትሞኙ። ከዚህ ቀደም 4 ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በፖሊስ ልታስፈራሩ መሞከራችሁ ምን ያህል የእግዚአብሔር ሰዎች እንደሆናችሁ ያሳያል። መጀመሪያ በኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንሁን ስንል እኮ አንዳነዶች ሊቀ ጳጳሱ ሌላ አለቃ ሊያመጡብን ስለሚችሉ በኢትዮጵያ አንሁን ሲሉ እነርሱን ለማሳመን እኮ ነው አንዲት አንቀፅ በህጋችን ያስገባን። ይህችን አንቀፅ ደግሞ ሊቀ ጳጳሱም ሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ አይቶ አምኖበት ነው በሲኖዶሱ ስር የሆንነው። ይህችም አንቀፅ እንዲህ ትላለች ” የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ የሚሆኑትን አባት የደብረ ገነት አጠቃላይ ጉባኤ ይመርጣል”። የሚገርመው ይህችን ህግ መፍረስ አለባት የሚሉት መጀመሪያ የህጉ አርቃቂ የነበሩ መሆናቸው ነው። ዓላማቸዉ ምን እንደሆነ አይታወቅም። ምን ያመጣሉ ከሆነ በደብራችን አባላት ሁላችን እኩል መብት ነው ያለን። አፋቸውን አዘጋለሁ እኔ ያልሁት ነው የሚሆነው???? በጣም አስቂኝ ልዩነታችን እኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን ሁሉም ነገር መንፈሳዊነትነ እንዳይለቅ ስለምንል እነጅ ….
3. ጥፋት 4፤ አንዳንድ እሾህ የሆኑ ሰዎች ደግሞ ብዙወችን እንዳሳቱት ሁሉ ከእኛ መሀል ካሉት አንዱን ነው የምንፈልገው እነጅ ሌላው ሁሉም ገለባ ነው ቤተክርስቲያን አይምጡ በማለታቸው ባለፈው እሁድ ያን ሰው ለማግኘት ደፋ ቀና ሲባል አየን። በጣም አስቂኝ በመጀመሪያ እናንተ ክርስቲያን ሳትሆኑ እሾህ መሆናችሁን ነው የተናገራችሁ። በባለፉት 8 ዓመታት ምን እንደሠራችሁ ስንቱን እነዳሳሳታችሁ ሁሉም ግልፅ ነው መናገርም አያስፈልግ። ለመሆኑ እናንተ የቤት እኛ የውጭ መሆናችን ነው? ማን ከውጭ ማን ከውሰጥ እንደሆነ እናየዋለን።
4. ጥፋት 5፤ ይህ ደግሞ ከአስመራጭና ከቦርድ (ሰበካ አመራርነትን ስለማያሟሉ) ያለ ስህተት ነው። በባለፈው ስምምነት የደረስንበትን ነገር ሰለመሻራችሁ። ባለፈው አመት ለምርጫ ስነነገር ከነበረው የመራጭ ቁጥር በ41% ጨምሯል። ስህተት እንዳይኖር ባለፈው ምርጫ ቢደረግ የሚያሟሉት ብቻ እንዲገቡ መዝገብ እና የከፈሉበት ቀን receipt እነዱመሳከር ነበር የተስማማነው። ሆኖም ግን በ41% ጨመረ ማለት ችግር አለ ማለት ነው።
Average Rating