0
0
Read Time:43 Second
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዛሬ ሐምሌ 26/2009 ዓ.ም ከቂሊንጦ ወሕኒ ቤት ተፈቷል።
ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ተይዞ የታሰረው እና በከፍተኛ ፍትህ መጓደል በማረሚያ ቤት ከአንድ አመት በላይ ቆይታውን ያደረገው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዛሬ ከእስር መለቀቁ ተገለፀ ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መዝገብ ቤት ሰራተኛ የዳንኤል ሺበሺን መፈቻ በጊዜ ባለመላኩ የተነሳ ዳንኤል ሺበሺ ሊለቀቅ አልቻለም። ዳንኤል ሺበሺ ነገ ሐምሌ 27/2009 ዓ ም ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የተለያዩ ክሶችም የተከሰሰ ቢሆንም በአሁን ሰአት ከእስር ተለቆ ከአዲስ አበባ ክልል እንዳይወጣ የፍርድቤቱ ትእዛዝ አመልክቷል ይላሉ እንደ ምንጮቻችን መሰረት
ባሳለፍነው ሳምንት ይለቀቃል ተብሎ የነበረው እና የሃምሳ ሺህ ብር ዋስትና እንዲያሲዝ የተጠየቀበት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በሰአቱ እንዳይፈታ የተደረገበት ምክንያት ከከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የተሰጠው የዋስትና ተመን በስህተት በመሆኑ እና የፍርድ ቤት ዳኛው በድጋሚ ክሱን መመልከት እንደሚፈልጉና ቆይታውን በእስር ቤት እንዲያደርግ ማዘዣ ማቅረባቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በጋዜጠኛው መታሰር ስትጨነቁ የነበራችሁ ወዳጅ ዘመድ ጓደኞች እንዲሀም የስራ አጋሮች እንኳን ደስ አላችሁ ።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating