www.maledatimes.com አጫጭር ወሬዎች | አቤ ቶኪቻው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አጫጭር ወሬዎች | አቤ ቶኪቻው

By   /   October 25, 2012  /   Comments Off on አጫጭር ወሬዎች | አቤ ቶኪቻው

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 47 Second
አንድ

በመጀመሪያ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወዳጆቼ እንኳን ለኢድ አልድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ነገ የአረፋ በዓል በሚደረግባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች በሙሉ ለኢህአዴግ ሁለተኛው ቢጫ ሊሰጠው መሆኑን ሰምቻለሁ።

አዲሳባ ስታድየምን ጨምሮ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “መንግስት ከሀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ” ብለው ለብዙኛ ጊዜ ደግመው ሊነግሩት ተነስተዋል። ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ይመሰረትባቸዋል ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በመዋላቸው “ሊለቀቁ ይሆን” የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ አጭሮ ነበር። ነገር ግን ክሱ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መዛወሩን ዛሬ ሰምተናል።

ሁለት ቢጫ እንደ ቀይ ይቆጠራልና መንግስት አጨዋወቱን ቢያሳምር ጥሩ ነው ብለን እንመክራለን! (መምከር አይደክመን!)

ሁለት

ብሄራዊ ቡድናችን ደቡብ አፍሪካ ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ከናይጄሪያ፣ ዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ ጋር ተመደበ።

እንደ ስያሜው “ዋሊያ” ከሀገር ወጥቶ የመታየት እጥረት ሲፈታተነው የነበረው ቡድናችን ባለፈው ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ሲያረጋግጥ የመንግስት ሰዎች ውጤቱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታሰቢያ ሲያደርጉት የፌስ ቡክ ሰፈር ልጆች ደግሞ “መለስ ሲሞቱ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፍን ኢህአዴግ ቢወርድማ ለአለም ዋንጫ እናልፋለን ማለት ነው!” ሲሉ ማሽሟጠጣቸው ይታወሳል (የማይታወስ ከሆነ ይታወስ!)

እዝችው ላይ አንድ ወዳጄ ባደረሰኝ ወሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሱዳንን ከአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ውጪ ባደረገበት ወቅት በሱዳን፤ ሱዳንያውያንን አግብተው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርቶች ትዳራቸው አደጋ ላይ ወድቆ ነበር ብሎኛል። እንደ ወዳጄ ገለፃ በዚህ የተነሳ የተፋቱ ሁሉ አሉ ብሎ ምሎ ነግሮኛል። በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ወሬ ከተገኘ አመጣዋለሁ!

ሶስት

ምንድነው የምሰማው? በአዲሳባ አንድ ባለ ክላሽንኮቭ ሰውዬ ከዚህ በፊት አግብቷት ከዛም “በቃ ይቅርብን ይቅርብን” ተበብለው የተፋቱትን የሁለት ልጆቹን እናት በጥይት ደብድቦ ገደላት የሚባል ወሬ ሰማሁ!

እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ተገዳይ ፍሬህይወት ታደሰ ህይወቷን ያጣችው ፖሊሶች አጠገብ ነው። ከሪፖርተር ልቀንጭብላችሁ…

…ከኋላቸው ከፍተኛ የሆነ የተሽከርካሪ ጥሩንባ በመስማታቸው፣ ሟች ‹‹ምንድነው?›› ብላ በመኪናዋ ስፖኪዮ ስትመለከት ተጠርጣሪው መሆኑን ማወቋን የገለጹት እናቷ፣ ‹‹እሱ ነው›› በማለት ወደፊት እየፈጠነች ነድታ ደንበል ሲቲ ሴንተርን እንዳቋረጠች ፖሊሶች በማየቷ ስታቆም፣ ገዳይ እንደበረረ መጥቶ በመውረጃዋ በር በኩል መኪናውን በማስጠጋት የእሷ በር እንዳይከፈት ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
እናቷ ባሉበት በር በኩል እንድትወጣ ቢስቧትም አሥራው የነበረው የአደጋ መከላከያ ቀበቶ ከነበረው ድንጋጤ ጋር ተዳምሮ አልፈታ በማለቱ፣ ተጠርጣሪው ክላንሽኮቭ ጠመንጃ በማውጣት ውስጡ ያሉ ጥይቶችን እንዳርከፈከፈባት አስታውቀዋል፡፡

ይሄ ሁሉ ሲሆን ተማምናቸው መኪና አጠገባቸው ያቆመችው ፖሊሶች ምን እየሰሩ ነበር? እግዜር ይወቀው!

ለማንኛውም ለፍሬህይወት ቤተሰቦች መፅናናትን፣ ለገዳይ መፀፀት እና ጥሩ ቅጣትን፣ ለፖሊስ ቅልጥፍና እና ነቃ ማለትን እመኛለሁ!

አጫጭር ወሬዎች | አቤ ቶኪቻው

www.abetokichaw.com

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 25, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 25, 2012 @ 6:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar