www.maledatimes.com ‹‹ዋቄ ፈናን ሐይማኖት አናውቅም ተብዬ በይፋ አምልኮ ተደርጌያለሁ›› ለማ ባየ ጉተማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹‹ዋቄ ፈናን ሐይማኖት አናውቅም ተብዬ በይፋ አምልኮ ተደርጌያለሁ›› ለማ ባየ ጉተማ

By   /   August 3, 2017  /   Comments Off on ‹‹ዋቄ ፈናን ሐይማኖት አናውቅም ተብዬ በይፋ አምልኮ ተደርጌያለሁ›› ለማ ባየ ጉተማ

    Print       Email
0 0
Read Time:59 Second

ስም፡- ለማ ባየ ጉተማ

ዕድሜ፡- 30

አድራሻ፡- ኦሮሚያ ክልል፣ ፊንፊኔ ዙሪያ ዞን ሱሉልታ ወሰርቢ ቀበሌ

አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ ጊዜ ቀጠሮ እስር ቤት

ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡– በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተቃውሞዎቹ ተሳትፎ አለህ በሚል ነው ያሰሩኝ፡፡

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበብኝ ክስ በእነ ደስታ ዲንቃ የክስ መዝገብ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) በመተላለፍ በማናቸውም መልኩ በሽብር ድርጅት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ የሚል ነው፡፡ የኦነግን አላማ ለማሳካት የአመጽ ጥሪ አድርገሃል ነው የሚለው ክሱ፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡ 

  1. ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በተደጋጋሚ ቀናት ድብደባ ደርሶብኛል፡፡
  2. ዕኩለ ሌሊት እየተጠራሁ ምርመራ ተካሂዶብኛል፡፡
  3. ጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል አስረውኛል፡፡
  4. በሐይማኖቴና በማንነቴ ላይ ተመስርተው ስድብ አድርሰውብኛል፡፡
  5. በሐይል ቃል እንድሰጥ አስገድደውኛል፡፡
  6. ክስ ተመስርቶብኝ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተዛወርሁ በኋላም የዋቄ ፈናን ሐይማኖት ተከታዮች ጸሎት ለማድረግ ስንሞክር ‹‹ከክርስትናና ከእስልምና ውጭ ሐይማኖት አናውቅም›› በማለት ጸሎት እንዳላደርግ ተከልክያለሁ፡፡

የኋላ ታሪክ

ትዳር መስርቻለሁ፡፡ ልጅም አለኝ፡፡ በቢዝነስ አድምኒስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ አለኝ፡፡ በዋናነት ለእስር ተዳርጌያለሁ ብዬ የማስበው በሐይማኖታዊ ስራዎች የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡ የምከተለው ሐይማኖት ዋቄ ፈናን ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዋቄ ፈናን አማኞች ማህበር ጸሐፊ ነኝ፡፡ በተጨማሪም በመላ ሸዋ የዋቄ ፈናን ማህበር ስራ አስኪያጅ ነኝ፡፡ በዚህ የኃላፊነት ቦታ መሰራት የሚገባቸውን ስራዎች አከናውን ነበር፡፡ ሐይማኖቱን አስተምራለሁ፡፡ ይህ እንቅስቃሴዬ ለእስር ሊያበቃኝ ባልተገባ ነበር፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on August 3, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 3, 2017 @ 8:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar