በሙስና ወንጀል ጠረጠርናቸው የሚሉአቸውን ባለስልጣናት እና ነጋዴ ማህበረሰብን ማደን ከተያዘ ሦስተኛ ሳምንቱን መያዙ የተገለፀ ነው ። በአሁን ሰአት የህወሀት መንግስት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነው በተባለበት በዚህ ጊዜ ፣በስሩ የነበሩትን የከፈተኛ ባለሥልጣን አመራሮችን ከቦታቸው አንስቶአል ፣ የድርጅቱ ሚስጥር ጠባቂ ተብለው በሙስና ውስጥ የተዘፈቁትን በአምባሳደርነት ሹመት ወደ ተለያዩ ቦታዎች አሸጋሽጎአቸዋል።
ሆኖም ግን በመንግስት እና በውጭ አገራት የተመሰረቱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሙስና መንሰራፋት መንግስት በይፋ እያወቀ በሌሎች ትንንሽ ገዳዮ ላይ ትኩረቱን መጣሉ የሃገሪቱን ደህነንት የማይፈልግ መንግስት መሆኑን ያሳያል ሲሉ አንድ የመንግስቱ ባለስልጣን ለማለዳ ታይምስ የፃፉት ደብዳቤ ይገልጣል ።በተለይም ይላሉ እኝሁ ባለስልጣን በዩኤስ አይድ እና በህወሃት መንግስት ባለስልጣን የተካሄደው ስምምነት የሀገሪቱን ውስጣዊ ደህንነት አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ የተነሳ የሀገርና የአካባቢ ጥበቃ ተብሎ የተመደበውን ገንዘብ ቢመለስም ሆነ ይህነኑ ጉዳይ ለማስፈፀም ተብሎ ከውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ዋና ሚንስትር ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ምንስትር መስሪያ ቤቱ ድርስ የዩኤስ ኤይድ ድርጅት ለስራ ማስኬጃቸው ይሆን ዘንድ ለሚንስትሮቹ በግላቸው የሰጠውን ገንዝብ እንዲመረምር እና ሚንስትሮችም ከፍተኛውን ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል ። በተለይም ይህንን ጉዳይ እንዲፈጸም ፊርማውን ያጸደቁት አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ከፍተኛው ምርመራ እንዲካሄድባቸው ጥሪ መቅረብ ይገባዋል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ሀገሪቱን የውስጥ ችግሮቿን እያዩ ችግር ፈጣሪ አካላትን በበጎ አድራጎት በኩል መፍቀድ አሳፋሪ ቢሆንም ፣በአሁን ሰአት ሀገሪቱን ለማፍረስ እና የእር በእርስ ግጭት ለመቀስቀስ ቀላል እንደሆነ በደንብ አጥንተውበት ስር የሰደደ ሂደት ውስጥ መሆናቸውን እና በየክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ተብሎ የተመሰረተው ይህንን አሜሪካ ድርጅት ጥናት በአስቸኳይ መንግስት ስራውን ማስቆም አለበት አለበለዚያ ግን ህዝቡን ለማጫረስ በዝግጅት ላይ መሆኑን ያመላክታል በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ይሄው የአሜሪካ ድርጅት የኢትዮጵያ ችግሮች የቱ ጋር እንደሆነ የትኛው ቦታ ላይ የብሄሮች ግጭት እንዳለ ፣መንግስት ከየትኛው ማህበረሰብ ጋር አየተፋለመ እንዳለ ጠንቅቆ በጥናቱ ላይ ያወቀው ሲሆን ካለበት መንበረ ስልጣን ለማውረድም ይሁን ህዝቡን እርስ በእር ለማጫረስ ከፍተኛ የሆነ አማራጭ ያለው ስልት መሆኑን አውቆታል።
በመቀጠል ለዚህም ላካሄዱበት እያካሄዱበት ላለውም ጥናት ከሚንስትር መስሪያቤቶችም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ መስሪያቤት እስከ ታች ድረስ በሙስና ተጨማልቀው ሀገሪቱን ለውጭ ድርጅት ወስጣዊ ደህንነቷን አሳልፈው ሰጥተዋል ሲሉ ሀሳባቸውን ቋጭተዋል።
ፖሊስ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ዛይድ ወልደገብርኤልንና ያለመከሰስ መብታቸው በዛሬው እለት በፓርላማ የተነሳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ አለማየሁ ጎጆን በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር አዋለ።
ዛይድ ወልደገብርኤል ከሁለት አመት በፊት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርነት ተነስተው ዋና ጽህፈት ቤቱን ሞንትሪያል ካናዳ ባደረገው አለም አቀፍ የስቪል አቬሽን ድርጅት; የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።ከገንዘብ በተጨማሪ ሙሉ ወጪ ተሸፍኖ ሀርቫርድ መማርና ከነቤተሰባቸው አሜሪካ ሽርሽርን ያከተተው አሰገራሚው የአቶ አለማየሁ ጉቱ የተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል
………………………………………………………………………..
✔ተጠርጣሪው በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ እና የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ አለማየሁ ጉቱ ናቸው፡፡
✔የፌዴራል አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው ግለሰቡ የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል በዝርዝር ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡
✔ከግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ይሁንታ ውጪ ያለ ጨረታ ለአንድ የውጭ ኩባንያ ከ20 ሚሊየን ዶላር በላይ ውል እንዲታሰር በተደረገበት ሂደት የጥቅም ትስስር ነበራቸው ተብሏል፡፡
✔ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከቀረጥ ነፃ ተፈቅዶ የገቡ 8 ተሽከርካሪዎችም ከህግ ውጭ ለባንክ የብድር ማስያዣነት በመፍቀድ ተጠርጥረዋል ተብሏል፡፡
✔በ2 ነጥብ 2 ሚለየን ዶላርም ያለ ጨረታ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ሁለት ወለሎች በነበራቸው የጥቅም ትስስር እንዲታደስና እስከ 500 ሺ ብር የሚደርስ ጉቦም ተቀብለዋል ተብሏል፡፡
✔በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይካሄድ በነበረ ፕሮጀክት ለአንድ የአሜሪካ ኩባንያ በ4 ሚሊየን ዶላር ያለ ጨረታ ሥራው እንዲሰጠው አድርገዋል የተባሉት አቶ አለማየሁ በዚሁ ኩባንያ ተወካይ ጋባዥነትም ለአንድ ወር ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአሜሪካ ስለመቆየታቸው ማስረጃ ተገኝቷል ብለዋል አቃቤ ህጉ፡፡
✔በዚሁ አሜሪካዊ አመቻችነትም በሀርባርድ ዩኒቨርስቲ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ትምህርታቸውን እንደተከታተሉ ማስረጃዎችም ተገኝተዋል ተብሏል፡፡
✔ያለመከሰስ መብታቸው የተነሣው የምክር ቤቱ አባል አቶ አለማየሁ በበኩላቸው መንግሥት ሙስናን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ከልባቸው እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
✔ባለፉት ዘጠኝ ዓመታትም በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በተሰጠኝ ኃላፊነት ህዝብና መንግሥትን በታማኝነት አገልግያለሁ ህሊናዬን የሚቆረቁረው ነገርም የለም ብለዋል፡፡
✔ጉዳዩ እዚህ ከመድረሱ በፊት ግን በፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ደረጃ መታየት ነበረበት የሚል የግል አስተያየታቸውንም ሰጥተዋል፡፡
✔አቶ አለማየሁ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የቀረበው የውሣኔ ኃሣብ በ1 ድምፀ ተአቅቦና በሙሉ ድምፅ ምክር ቤቱ አፅድቆታል፡፡ማለዳ ታይምስ
(ሰበር ዜና ፓርላማ) ያለመከሰስ መብታቸው በፓርላማ የተነሳው የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ዴኤታ በፖሊስ ቁጥጥር ዋሉ
Read Time:2 Minute, 51 Second
- Published: 7 years ago on August 4, 2017
- By: maleda times
- Last Modified: August 4, 2017 @ 10:04 am
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating