www.maledatimes.com በሸዋሮቢት ከተማ የሚገኘው ግብር ከፋዪ ነጋዴ ተቃውሞውን አሰማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በሸዋሮቢት ከተማ የሚገኘው ግብር ከፋዪ ነጋዴ ተቃውሞውን አሰማ

By   /   August 4, 2017  /   Comments Off on በሸዋሮቢት ከተማ የሚገኘው ግብር ከፋዪ ነጋዴ ተቃውሞውን አሰማ

    Print       Email
0 0
Read Time:33 Second

#ሰበር መረጃ !!!

በሸዋሮቢት አድማው እንደቀጠለ ነው ተባለ ! !!

አድማውን በሃይል ለማስቆም ሞክረው ያልተሳካላቸው ካድሬዎች ስልት በመቀየር በከባድ ስፒከር (ሞንታርቦ) በመጠቀም ነጋዴው እንዲሰበሰብ ጥሪ ባደረጉት መሰረት በውሃ ልማት መጋዘን (መቀመጫ የሌለበት) ነጋዴው ተሰብስቧል።
የተሰበሰበውን ህዝብ ለማስፈራራትም ፌደራል እና የአካባቢው ፖሊሶችን የጫኑ ከአራት በላይ መኪኖች የመሰብሰብያውን ስፍራ ከበውት ነበር። የከተማው ከንቲባ ጥላሁን ሰጣርጌ ስብሰባውን በወቀሳ ጀመረ “አዋርዳችሁናል፣ የከተማችን ገጽታ ተበላሸ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሳችሁታል” በማለት ደሰኮረ።
ነጋዴዎቹም መለሱ “ነጋዴው ፖሊስ ይፈራል ብላችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል አንፈራም! ኢህአዴግ በስብሷል! ካላስተካከላችሁ አንከፍልም! ብታርፉ ይሻላችኋል! ከተማውን በወታደር ወራችኋል፣ አንላቀቅም!” ከዚህ በኋላ ካድሬዎቹ መናገር ሲጀምሩ ነጋዴው እየጮኸ ጥሏቸው ወጥቷል።
ካድሬዎቹ ነጋዴውን ለመመለስ ጥረት ሲያደርጉም ታይተዋል “እባካችሁ ተመለሱ፣ ታዘን ነው፣ ይስተካከላል…” ሲሉ ተደምጠዋል። ስብሰባውም በዚህ መልኩ ያለውጤት ተቋርጧል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar