#የአራተኛውን_ተከሳሽ_ማንነት_እና_ክስ_ልብበሉልኝማ
__=================<<
በሙስና ወንጀል ተጠጥርው በቁጥጥር ስር የዋሉት አራት
ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።
በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎችም ቀድሞ
የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ
አለማየሁ ጉጆ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና
ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የመስኖ
እና ቤቶች ልማት ዘርፍ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ
ደስታ እና የሀዚ አይ.አይ ኮንስትራክሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ
ዛኪር መሃመድ ናቸው።
ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች በድምሩ ከ1 ቢሊየን 256
ሚሊየን 356 ሺህ ብር በላይ ጉዳት በመንግስት ላይ አድርሰዋል
በሚል የሙስና ወንጀል ነው።
ፖሊስም ተጠርጣሪዎቹ ላይ የማደርገው ተጨማሪ ምርመራ አለኝ
በሚል የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም ከአቶ ዛኪር መሃመድ ውጪ ሌሎቹ ላይ ፖሊስ
ያቀረበውን የ14 ቀን ጭማሪ ቀን የፈቀደ ሲሆን፥ የሀዚ አይ.አይ
ኮንስትራክሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ዛኪር መሃመድ ላይ ግን
የ9 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ነው የፈቀደው።
ቀድሞ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ
አለማየሁ ጉጆ፥ “የስኳር ህመሜ መጠን ከፍ በማለቱ ህክምና
የማገኝበትና የምግብ ሁኔታዬ ታሳቢ ቢደረግልኝ” ሲሉ ፍርድ ቤቱን
ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ህክምና በአስቸኳይ እንዲያገኙ እና
ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለፖሊስ ትእዛዝ አስተላልፏል።
በተያያዘ ችሎቱ በዛሬ ውሎው በህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም
የህዝብ ቅሬታ መርማሪ የነበሩትን የአቶ በላቸው ደበሎን ጉዳይ
ተመልክቷል።
አቶ ጌታቸው ቤት ፈርሶብናል በሚል ቅሬታ ካቀረቡ የቡራዩ ከተማ
102 የልማት ተነሺ ሰዎች ካርታ አሰራላችኋለሁ በሚል 510 ሺህ
ብር ጉቦ ተቀብለዋል ተብለው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት።
ፖሊስ አገኘሁት ባለው መረጃም ተጠርጣሪው ካርታ አሰራላችኋለሁ
በሚል ከእያንዳንዱ ቅሬታ አቅራቢ 5 ሺህ ብር ተቀብለዋል የሚል
ነው።
በዚህም መሰረት 210 ሺህ ብሮ በባንክ የሂሳብ ቁጥራቸው
እንዲገባላቸው አድርገዋል፤ ቀሪውን ገንዘብ ደግሞ በእጅ
ተቀብለዋል ይላል የፖሊስ ማስረጃ።
ፖሊስ በአቶ ጌታቸው ላይም ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ የጠየቀ
ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም ፈቅዷል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የወንጀል ችሎት
ለነሃሴ 15 ቀን 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዜና ሙስና በፍርድ ቤት ውሎ ፖሊስ የምርመራ ጊዜ እንዲራዘምለት ጠየቀ
Read Time:1 Minute, 26 Second
- Published: 7 years ago on August 7, 2017
- By: maleda times
- Last Modified: August 7, 2017 @ 10:45 pm
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating