www.maledatimes.com GERRETA ግርታ የተሰኘው ኢትዬጵያዊ አጭር ፊልም በአለም አቀፍ ደርጃ ሽልማትን አገኘ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

GERRETA ግርታ የተሰኘው ኢትዬጵያዊ አጭር ፊልም በአለም አቀፍ ደርጃ ሽልማትን አገኘ

By   /   August 9, 2017  /   Comments Off on GERRETA ግርታ የተሰኘው ኢትዬጵያዊ አጭር ፊልም በአለም አቀፍ ደርጃ ሽልማትን አገኘ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

በማንተጋፍቶት ስለሺ ተሰርቶ ለእይታ የበቃው GERRETA ግርታ የተሰኘው ኢትዬጵያዊ አጭር ፊልም በአለም አቀፍ ደርጃ ሽልማትን አገኘ። ይህ ፊልም ሽልማቱን ያገኘው ጣልያን ላይ ተካሄዶ በነበረው The 9 river film festival, Padova ሲሆን ፣ በያዝነው ወር አጋማሽ (ከ 17-26 august 2017) በአምስተርዳም የሚካሄደው የዓለም-አቀፍ ሲኒማ ፌስቲቫል ላይም ይቀርባል።

ግርታ አጭር ፊልም በ2017 በዚፍ ZIFF (2017) የፊልም ፌስቲቫል ፣ በቡርኪና ፋሶ FESPACO (Ouagadougou, Burkina Faso 2017) እንዲሁም በርሊን ላይ ተደርጎ በነበረው 31ኛው አለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተወዳድሮ የአሸናፊነት መታጨቱን የአለም ሲኒማ ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፊልሙን የሰራው ማንተጋፍቶት ስለሺ በአሁን ሰዓት በጀርመን ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው አገልሎት ፕሮዲዩሰር ሲሆን ፣ በመጭው ሳምንት በአምስተርዳም ላይ በሚደረገው ዓለም-አቀፍ ሲኒማ ቀን በመገኘት ለተመልካቾች ስለ ፊልሙ ይዘት ማብራርያ ይሰጣል።

ፊልሙ በአንድ በድህነት የተበሳጨ አባት ታሪክ ዙርያ ያጠነጥናል። ይህ አባት ለልጆቹ የሚበላ ፍለጋ ከቤቱ ይወጣል። እመንገዱ ላይ አንድ ሃብታም ቤተሰብ ያገጥመውና የሸክም አገልግሎት በትንሽ ክፍያ ይሰጣቸው ዘንድ ቢጠይቅ እምቢኝ ብለው ያመናጭቁታል። ግርግር ወደበዛበት ስፍራ የተጓዘው ይህ አባት፣ በማያውቀው የዳቦ ቤት ሌብነት ወንጀል እሱ ጦስ በመሆን “ሌባ” እየተባለ የአባሮሽ ሰለባ ሲሆን ያሳያል። በፊልሙ 35 ያህል ካራክተሮች የተካተቱ ሲሆን ቀረጻው በተለያዩ የአዲስ አባባ ክፍሎች መከናወኑን የፊልሙ ዲያሬክተር ገልጿል። ፊልሙ የተሰራው በአማርኛ ሲሆን የእንግሊዝኛ ሰብታይትል አለው።

በመጭው ሳምንት ፊልሙን በአምስተዳም ለማየት የሚሹ RIALTO ሲኒማ ብቅ በማለት አልያም በዚህ ሊንክ መጠቀም ይቻላሉ። http://worldcinemaamsterdam.nl/en/portfolio-item/gerreta/

https://youtu.be/vgao55J26oI

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on August 9, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 9, 2017 @ 7:39 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar