ስም፡- ቴዎድሮስ አስፋው
ዕድሜ፡- 27
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ
አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ እስር ቤት
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲዎች ባለኝ የሰላማዊ ትግል ተሳትፎ መንስኤነት እንደታሰርሁ አምናለሁ፡፡
በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- የፌደራል አቃቤ ህግ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) መተላለፍ በሚል በማናችም መልኩ በሽብር ቡድን ውስጥ ተሳትፎ አለህ ብሎ ነው ክስ ያቀረበብኝ፡፡ ጉዳዬን በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ እየተከታተልሁ እገኛለሁ፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡
- በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለአራት ወራት በቆየሁባቸው ጊዜያትበተያዝሁ ዕለት የፍ/ቤት ትዕዛዝ ሳያሳዩኝ ነው ያሰሩኝ፡፡
- በዕለቱ ስያዝ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
- ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ አራት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ደብድበውኛል፡፡
- ሌሊት ሌሊት ምርመራ ተካሂዶብኛል፡፡
- ስድብና ዛቻ ደርሶብኛል፡፡
- በጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ለሶስት ወራት ታስሬያለሁ፡፡
- ጠያቂ ተከልክየ በእስር እንድቆይ ተደርጌያለሁ፡፡
- በግዳጅ በሰጠሁት ቃል፣ ተገድጄ እንድፈርም ተደርጌያለሁ፡፡
2. ቂሊንጦ እስር ቤት በእስር ባለሁበት ወቅት የተፈጸሙብኝ የመብት ጥሰቶች፡-
- ለሶስት ወራት (ከነሐሴ 2008 እስከ ጥቅምት 2009 ዓ.ም) ጨለማ ክፍል ታስሬያለሁ፡፡
- በእነዚህ ሦስት ወራት ቤተሰቤን እንዳላይ (እንዳልጠየቅ) ተከልክያለሁ፡፡
- ምግብ ከቤተሰቦቼ እንዳላገኝ ተደርጌያለሁ፡፡
- ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶብኛል፡፡
የኋላ ታሪክ:
ተወልጄ ያደግሁት አዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት አዲስ አበባ የተማርሁ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪየን ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አጠናቅቄያለሁ፡፡ እስከታሰርሁበት ጊዜ ድረስ የመንግስት ሰራተኛ ነበርሁ፡፡ የምኖረው ከቤተሰቦቼ ጋር ነበር፡፡
በአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ሆኜ በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት የበኩሌን አስተዋጽኦ እያደረግሁ ነበር፡፡ አንድነት ሲዳከም ሰማያዊ ፓርቲን በመቀላቀል በፖለቲካው ተሳትፎ አድርጌያለሁ፡፡
Average Rating