www.maledatimes.com ‹ነክ ስድቦችን ተሰድቤያለሁ፣ ድብደባም ተፈጽሞብኛል›› አየለች አበበ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

‹ነክ ስድቦችን ተሰድቤያለሁ፣ ድብደባም ተፈጽሞብኛል›› አየለች አበበ

By   /   August 9, 2017  /   Comments Off on ‹ነክ ስድቦችን ተሰድቤያለሁ፣ ድብደባም ተፈጽሞብኛል›› አየለች አበበ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 6 Second

ስም፡- አየለች አበበ

ዕድሜ፡- 33

አድራሻ፡- ደቡብ ክልል፣ አርባ ምንጭ ከተማ

አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- አዲስ አበባ፣ ቃሊቲ እስር ቤት

ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- የወንድሞቼን የተቃውሞ ፖለቲካ ትደግፊያለሽ በሚል ሰበብ ለእስር እንደተዳረግሁ ነው የማምነው፡፡

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- በፌደራል አቃቤ ህግ በእነ ሉሉ መሰለ የክስ መዝገብ የተከሰስሁ ሲሆን፣ የቀረበብኝ ክስ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) በመተላለፍ በማናቸውም መልኩ በሽብር ድርጅት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ የሚል ነው፡፡

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡

  • በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ከአራት ወራት በላይ በቆየሁባቸው ጊዜያት፣
  1. ቤተሰቦቼን ታስሬ አዲስ አበባ እንደመጣሁ ለማሳወቅ ተከልክየ ቆይቻለሁ፡፡
  2. ጠያቂ እንዳያናግረኝ ተደርጌያለሁ፡፡
  3. በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
  4. በምርመራ ወቅት ማንነቴንና ሴትነቴን መሰረት በማድረግ ክብረ ነክ ስድቦችን ተሰድቤያለሁ፡፡
  5. ሌሊት ሌሊት ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡
  6. በምርመራው ወቅት የቤተሰቦቼን (የወንድሞቼን) ስም እያነሱ ጉዳት እንደሚያደርሱብን ዝተውብኛል፡፡
  7. ተገድጄ በሰጠሁት ቃል ላይ በግዳጅ እንድፈርም አድርገውኛል፡፡
  • አሁን በምገኝበት ቃሊቲ እስር ቤት ከተዛወርሁ በኋላም የጠያቂ ገደብ ተጥሎብኛል፡፡ አሁን ላይ ከወላጅ አባቴ ውጭ የሚጠይቀኝ ሰው አይፈቀድለትም፡፡

የኋላ ታሪክ: 

ትውልዴና እድገቴ ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ነው፡፡ ለእስር እስከተዳረግሁበት ጊዜ ድረስ በመምህርትነት ሳገለግል ነበር፡፡ ከቤተሰባችን እኔ ለእስር ስዳረግ ሦስተኛዋ ነኝ፡፡ ሁለት ወንድሞቼ (በፍቃዱ አበበ እና ባንተወሰን አበበ) በቂሊንጦና በዝዋይ እስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ አባቴም ለእስር ተዳርጎ ለወራት ታስሮ ነው የተፈታው፡፡ ይሄ ሁሉ በቤተሰባችን ላይ የሚደርሰው በፖለቲካ አመለካከት ልዩነታችን ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ በእኔ ላይ የመጣው እስር እንደ ቤተሰብ ለወንድሞቼ በምሰጣቸው ፍቅርና የእነሱ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ልንቀበለው የሚገባ ስለመሆኑ በግልጽ ስለምናገር እንደሆነ ነው የምገምተው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 9, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 9, 2017 @ 8:11 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar