አሳዛኝ ሰበር መረጃ 🙁
===============
=================================
* አቶ ሐብተሥላሴ ታፈሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ለኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት ይባላሉ፡፡ በፎቶግራፈርነት፣ በአስጎብኚት፣ በቱሪዝም ኮሚሽነርነትና የኢትዮጵያ ባህላዊ እሴቶች በአለም እንዲተዋወቅ ሰርተዋል – አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ፡፡
“ምድረ ቀደምት” ወይም “ላንድ ኦፍ ኦሪጅን” በዚህ አመት የሃገሪቱ መለያ ከመሆኑ በፊት ኢትዮጵያ ለረጅም አመታት የቱሪዝም መለያዋ አድርጋው ለነበረው “የ13 ወር ፀጋ” ወይም “Thirteenth month of sunshine” ፈጣሪ ናቸው፡፡
እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ዛሬ ረፋድ በተወለዱ በ90 አመታቸው በባልቻ ሆስፒታል ማረፋቸውን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰምተናል፡፡
አቶ ሀብተስላሴ ለሀገሪቱ የቱሪዝም እድገት ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ በዚህ አመት በተደረገው 6ኛው የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ጉባኤ በምክር ቤቱ ስብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ የእውቅና የወርቅ ፒን ተበርክቶላቸዋል፡፡
ባለፈው አመት ሐምሌ ወር ዮኒቲ ዩኒቨርስቲ ለዚህ ታላቅ ሰው የሊቀመንበሩን የእውቅና ሽልማት ሰጥቷቸዋል፡፡ የአቶ ሃብተስላሴን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ለመፈፀም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኮሚቴ አቋቁሞ እየተንቀሣቀሰ መሆኑን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የህዝብና አለማቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ተናግረዋል፡፡
ሸገር ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ባለሞያዎች በእኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሞት የተሰማውን ሐዘን ይገልፃል..
( የመረጃዬ ምንጭ በሸገር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ምስክር አወል የተሰራጨው መረጃ ነው )
ነፍስ ይማር 🙁
ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓም
Average Rating