ሆን ተብሎ በተፈጸመ ግፍ ነው የሞቱት…
በግሩም ተ/ሀይማኖት
24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት ጀልባ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ጉዳት ደረሰባቸው። ከትላንትና ወዲያና ትላንትና በደረሰው አሳዛኝ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊያን የተጎዱበት አደጋ መሆኑን የዓለም ዓቀፍ ስደኛተኞች ጉዳዮች ድርጅት (የIOM ዳይሬክተር ገልጸዋል።
ከትላንትና ወዲያ ከሶማሊያ ወደ የመን የሚሻገሩ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን ሆን ተብሎ እየተገፈተሩ ወደ ባህር መጣላቸውን ታውቋል። ከተጣሉት ውስጥ ከ50 በላይ እንደሞቱ (IOM) አስታወቋል።
ትላንትና ደግሞ ከጅቡቲ ወደ የመን ሲሻገሩ የነበሩ 180 ኢትዮጵያውያን ሆን ተብሎ እየተገፈተሩ ወደ ባህር መጣላቸውን። ይህን የሚያደርጉይ ህገ-ተብሎ ወጥ አጓጓዦች ሲሆኑ በሰሜናዊ የመን አካባቢ ሞካ አቅራቢያ መሆኑ ታውቋል። የስድስት ሰው አስክሬ መገኘቱን የ13 ሰው አስክሬን መጥፋቱን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል።
ሆን ተብሎ እየተገፈተሩ የሚለውን የIOM ሀላፊዎች አባባል ግልጽ ላድርግ። የባህሩ ጠረፍ ጋር ሲደርሱ ድንበር ጠባቂዎቹ ስለሚይዙና ገንዘብ ስለሚቀበሏቸው መውራጃው ጋር ከመድረሳቸው መቶ እና ሁለት መቶ ሜትር ሲቀር እየገፈተሩ ወደ ባህር ይጥላቸዋል። ወይም ይገለብጧቸዋል። ዋና የቻለ ቻለ ያልቻለ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አጋጣሚ ብሎ ከደረሱ ያወጡታል። ካልሆነም ሬሳውን ይለቅማሉ። እሱም ከተገኘ ነው።
ከላይ በልለጽኩት በሁለቱ አደጋዎች እስካሁን የ69 ሰው ህይወት ማለፉንና ከ60 በላዩ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ድርጅቱ አሳውቋል።.
IOM ይህን ያሳውቅ እንጂ የድርጅቱ መግለጫ ግልጽነት የጎደለው ነው። የሟቾች ቁጥር ከዚህም የበለጠ እንደሆነ ለማወቅ አይከብድም። ምክንያቱም 180 ሰዎች ሆን ተብሎ እየተገፉና እየተወረወሩ ባህር መከተታቸውን አምኖ የተረፉትን ቁጥር በይፋ ያስቀመጠው የለም። በሸቡዋ አካባቢ ከፍተኛ የማዳን ጥረት ቢደረግም የባህሩ ዳርቻ በጣም ርቆ ስለሆነ ወደ ባህር የወረወሩዋቸውን ሰዎች ለማዳን ቦታውም አመቺ አለመሆኑ በዛ በኩል የገባን ሰዎች እናውቃለን። 180 ሰው 161 አትርፈናል የሚለው አሳማኝ አይደለም።….
በሌላ በኩል በዚህ ወቅት ህንድ ውቅያኖስን የሚያናውጥ ማዕበል እና ሀይለኛ ንፋስ ያለበት ሁኔታ ነው። እና የሟቾቹ ቁጥር የተድበሰበሰ ነው።
የ IOM ዋና ኃላፊ የሆኑት ዊሊያም ሊሲ ስዊንግ በትዊተር ላይ በተለጠፉት ቪዲዮ ሲናገሩ “ስፍር ቁጥር የሌላቸው ልጆች ሆን ተብሎ እና በጥፋተኞች ግፍ ሞተዋል..” ብለዋል። የሀላፊውን ገለጻ በቪዲዮ ይመልከቱት…..
Average Rating