ሰበር መረጃ በሐጅ ዙሪያ ፣
=================
===================
* የሐጅ ጸሎት ልክ የዛሬ ሳምንት ነሐሴ 24 ቀን ይጀምራል ! * ” የሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መግለጫ አውጥቷል
ሰኞ ጨረቃ አለመታየቷን ተከትሎ ትናንት ማክሰኞ ምሽት የተሰበሰበው የሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጨረቃ ስለመታየቷ የተሰበሰበውን መረጃ ከመረመረ በኋላ ውሳኔ አስተላልፏል። በከፍተኛው የሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተላለፈው ውሳኔ እንደሚያስረዳው በእስልምናው የሒጅሪያ የቀን መቁጠሪያ ቀመር የዙል ሒጃ Dul-Hijjah ወር የመጀመሪያ ቀን ረቡዕ ነሐሴ 17 ቀን 2009 ወይም እአአ August 23, 20017 እንደሚጀምር አስታውቋል ።
መግለጫው በማከልም የሐጅ ጸሎት የሚጀመረው በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ነሐሴ 24 ወይም እአአ August 30, 2017 መሆኑ አስታውቋል ። የሐጅ ጸሎተኞች ጸሎታቸውን ወደ ሚና በመጓዝ ጀምረው ሚና ጸሎታቸውን ከውነው በቀጣዩ ቀን ሀሙስ ነሐሴ 25 ቀን 2009 ወይም እአአ August 31, 2017 ወደ አረፋት ኮረብታ በመሄድ ጸሎት እንደሚያደርጉ ከከፍተኛው የሳውዲ ፍርድ ቤት የወጣው መግለጫ ይጠቁማል ። ። የኢድ አልአድሃ በዓልም በቀጣዩ ቀን አርብ ነሐሴ 26 ቀን 2009 ወይም እአአ September 1, 2017 እንደሚሆን የተሰራጨው መረጃ ያስረዳል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዘንድሮው የሐጅ ጸሎት ለመሳተፍ
እስከ ትናንት ማምሻ ድረስ 1,253,759 ምዕመናን ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ታውቋል። ይህ ቁጥር ከአለፈው አመት ጋር ሲወዳደር በ27 እጅ ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል።
ፈጣሪ ይታረቀን ፣ የምዕመኑንም ጸሎት ይቀበል !
ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 17 ቀን 2009 ዓም
Average Rating