=======================================
* በብላቴናው ጉዳይ የደረሰኝ አሳዛኝ መረጃ
የብላቴናው መሀመድ ፍትህ እጦት ጀርባ ብዙ ያለተሰማ ሸፍጥ እየተፈጸመ ነው ። ሸፍጥ ግፉን የጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በብላቴናው መሐመድ ላይ ከሁለት አመት በፊት የሰራው ዘገባ አደለም ያስታወሰኝ ከቀናት በፊት የጅዳ ቆንስል ፍትህ ፈላጊዋን ተገፊ የብላቴናው መሀመድ እናት ሀሊማ ሙዘይን ስልክ ደውላ ያደረሰችኝ መልዕክት ቢያመኝ ልተነፍሰው ፈቀድኩ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ባሳለፍነው ሳምንት ጉዳዩዋን ለመከታተል ወደ ቢሯቸው ጎራ ያላለችው እናት ሀሊማ ልብ የሰበረ መረጃ እንደሰጧት አጫውታኛለች ።
የጅዳ ቆንስል ሃላፊ አምባሳደር ውብሸት ለአመታት የብላቴናውን ቤተሰቦች ሲያጉላላ የከርመው መስሪያ ቤታቸው የብላቴናውን ጉዳይ ወደ ፍር ቤት መውሰድ እንደማይችል ለእናት ሀሊማ አሳውቀዋታል። በአጭሩ እናት ሀሊማ በግልሽ የህግ ጠበቃ ቅጥረሽ ተከራከሪ ተብላለች ያለፈውን ትተን በቅርብ አመታት የተገባውን ቃል ብንመለከት የሪያዱ አንባሳደር አምባሳደር አሚን በተገኙበት አንድ ስብሰባ ቆንስል ሙንትሃ ከፍር በአንድ ስብሰባ ላይ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ፤ በህግ አዋቂዎች ፤ በውጭ ጉዳይ ጋር ፣ በዶር ቴዎድሮስ መያዙን ነግረውን ነበር ። በዚሁ ስብሰባ አምባሳደር አሚንም ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉ ቃል ገብተው ነበር ። የተባለው እና የተገባው ቃል ሁሉ ግን ዛሬ እንዳልሆነ አረዱን
(በስብሰባው የተናገረችው የእናት ሀሊማ አቤቱታ ፣ የአንባሳደር አሚንን ቃል ፤ የቆንስል ሙንትሃ ከድር ጉዳዩ በከፍተኛ ሁኔታ ስለመያዙ የተናገሩትን በቅርብ ደግሜ አቀርበዋለሁ )
እናም በተወካዮቻችብ በአደባባይ የተገባው ሁሉ ቃል ከንቱ ቀርቷል ። የብላቴናው መሀመድ ቤተሰቦች ዛሬም በፍትህ እጦት ያለቅሳሉ ፣ በምሬት ” ሁሉን ለፈጣሪ እንሰጣለን ፣ ፍትህንም እንሻለን ” በማለት ” ሀገር ወገን መንግስት ይፍረደን ይላሉ !
የብላቴናውን ጉዳይ በቅርብ የምንከታተል በሳውዲ የመንግስት ተወካዮች ከ9 ዓመት በኋላ ጉዳዩዋን መከታተል በመጀመራቸው ደስ ብሎ ነበር። ደስታችን በኖ የጠፋው ግን ብዙ ሳይቆይ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በአደባባይ ጉዳዩን እየተከታተልን ነው ቢሉም እስካሁን እንኳንስ ለመሀመድ ፍትህ ሊያስገኙ ከሆስፒታሉ ስትባረር መብቷን ሊያስከብሩላት አልቻሉም ። ባሳለፍናቸው ሁለት አመታት ኢንባሲው ፤ ቆንስሉና የውጭ ጉዳይ የዜጋውን ጉዳይ ጉዳየ ብሎ ያደረገው ድጋፍም ሆነ የፈየዱት አንዳችም ነገር የለም ።
የጤና ጥበቃ የህክምና ጉዳዮች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ለሁለት አመታት ለማስከበር ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማድረስ አለመቻል የአቅምና የባጀት ጉዳይ ነው ሊባል ይችላል። እኔ የማውቀውን ልንገራችሁ ። አንድ በጎ ላድርግ ያሉ ታዋቂ ሳውዲ ጠበቃ ጉዳዩን ልከታተልለት ብለው ፍላጎት ባሳዩኝ ማግስት ለጅዳው ቆንስል አምባሳደር ውብሸት ደምሴ አሳውቄ በአካል አገናኝቻቸው አውቃለሁ ። ዳሩ ግን ለጠበቃው ውክልና ለመስጠት ወደ ውጭ ጉዳይ ህግ ክፍል ተላከ የተባለ ምክንያት ተሰጠን። ቆየና ጉዳዩ ለዶር ቴዎድሮስ ቀርቦ ውሳኔ አላገኘም ሲባል ሲንከባለለ ከርሞ ደጋግመን ስንጠይቅ ምላሽ ተነፈገን ! ዛሬ በድንገት አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን እንደመደገፍ “ጠበቃ ቅጠሩ ” ብሎ ለብላቴናው መሀመድ ጉዳይ ምላሽ መስጠት በብላቴናው ላይ ከተፈጸመው ግፍ ያልተናነሰ ግፍ በቤተሰቡም ላይ መፈጸም ነው
ዶር ቴዎድሮስን ዛሬም በልጆችዎ እንማጸንዎታለን !
============================= የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ለዛሬው የአለም ጤና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም የብላቴናውን ጉዳይ አሳምረው ያውቁታል። እኔም በትዊተር አግኝቻቸው ጉዳዩን በሳውዲ ተወካዮች በኩል እንድከታተል መክረውኝ ያውቃሉ ። ዶር ቴዎድሮስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኃላፊነታቸው ወቅት የሚያውቁት ግን ያላሳኩት ጉዳይ የብላቴናው መሀመድ ጉዳይ ነው ። ይህን የጅዳ ስል የቆንስል ሃላፊ የነበሩት ቆንስል ሙንትሃ ሳይቀር በአደባባይ ጉዳዩ ለዶር ቴዎድሮስ መድረሱን መረጃ ሰጥተውን ያውቃሉና ነው።
ዛሬ በአለም ጤና ጥበቃ ትልቅ ኃላፊነት የተቀመጡት ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም የብላቴናው ፍትህ እጦት ጉዳይ ቀዳሚ ጉዳያቸው ሊሆን ይገባል። በህክምና ስህተት ፍትህ ላጣው ዜጋቸው ስለ ብላቴናው ፍትህ መስፈን ከሳውዲ ከኢትዮጵያ መንግስት ፣ ከሳውዲ የውጭ ጉዳይና ከሚመለከታቸው የሳውዲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይነጋገሩ ዘንድ በልጆቻቸው እማለዳቸዋለሁ ፤ እማጸናቸዋለሁ !
ለቆንስልና ኢንባሲው መልዕክቴ
================== የብላቴናው መሀመድ የ12 ዓመት የፍትህ እጦትን እንደ መንግስት ተወካይ ጉዳዩን ወደ ሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማድረስ ያለበት የጅዳ ቆንስልና የሪያድ ኢንባሲ የብላቴናውን ደካማ ቤተሰቦች ጠበቃ ቅጠሩ ማለት ፍጹም ፍትሃዊ አይደለም ። የኢትዮጵያ መንግስት በፍትህ እጦት ለሚንከራተተው ብላቴና ጠበቃ ማቆም ካልቻለ እኛ እንደ ዜጋ ያገባናልና ጠበቃ እንቀጥርላታለን ! ኢንባሲና ቆንስሉ የጠበቃ ማቆሚያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ በአለም እናሰባስብ ዘንድ ፍቃድ ይስጠን ወይም በራሱ በኩል እርዳታውን ያሰባስብ ዘንድ እንማጸናለን !መላ በሉን ፤ መላ ስጡን ፤ የፍትህ እጦት እንባ ይድረቅ ፤ ተወካይ በማጣት ብቻ ፍትህ በብላቴናው ላይ አይስተጓጎል !
በጅዳና ሳውዲ የምትገኙ የእስልምና ሐይማኖት አባቶች ፤የጃሊያና የዳዕዋ ማህበራት በብላቴናው መሀመድ ፍትህ ጉዳይ ዝምታችሁን ስበሩት ! ስለ ሰብዕናና ፍትህ መስክሩ ፤ ስለ ብላቴናው መሀመድ አብድልአዚዝ የዘገየ ፍትህ ለሳውዲ የሐይማኖት አባቶች አሳውቁ !
ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ !
ወዳጆቸ ይህን መረጃ ለሚመለከታቸው ሁሉ ይደርስ ዘንድ LIKE & SHARE በማድረግ በማሰራጨት ተባበሩኝ !
ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 18 ቀን 2009 ዓም
የማለዳ ወግ … የፍትህ ፈላጊ እናት እንባና በሳውዲ ላይ የዘገየው ፍትህ !

Average Rating