በዛሬው ምሽት ይካሄዳል ተብሎ ታስቦ የነበረው የኢትዮጵያ አልበም የሙዚቃ ምረቃ ስርአት የመንግስት ሀይሎች መከልከላቸውን እና ልዩ ፈቃድ ያስፈልግሀል ብለው መወሰናቸውን ቴዲ አፍሮ ባቀረበው የፕረስ ደብዳቤ ገልጣል ።
ይህም ደብዳቤ እንደሚገልፀው ዝግጅቱን አጠናቀን ለእንግዶች የጥሪ ወረቀት ተላልፎ በጉጉት በሚጠበቁበት የመጨረሻው ሰአት በተለይም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተዘጉበት መረሀግበሩን አታካሂዱም መባላችንን በጥልቅ ሀዘን ነው ሲል ገልፀፇል ።
ለአድናቂዎቹና ጥሪ ለተደረገላቸው ወገኖችም ይቅርታን እንጠይቃለን በማለት ለብን በሚያሸብር መንፈስ መናገሩን ያመለክታል የተላከው ደብዳቤ።
〉የተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ዛሬ ምሽት በሂልተን ሆተል ሊካሄድ የነበረው የሲዲ ምረቃ በአዘጋጆቹ መሀከል በተነሳ አለመግባባት መሰረዙ የተባለው ይታረም እና በመንግስት ሃይሎች በሚል ይነበብልን በደረሰን ዘገባ ስህተት መሆኑን ከይቅርታ ጋር እየገለጽን። ከቅርብ ምንጭ ተሰምቷል። ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አመት ሙዚቃ ዝግጅቱ ከፍተኛ እሰጣ ገብቶ የነበረው ቴዲ አፍሮ በመንግስት ባለስልጣናት ግፊት ፕሮግራሙ እንዲሰናከል መደረጉን የማለዳ ሪፖርተሮች መዘገባቸው ይታወሳል።
ዛሬ የቁም ነገር መፅሄት አዘጋጅ ታምራት ሀይሉ እና የለዛ ሬዲ አዘጋጅ ብርሀኑ ድጋፌ እንደገለፁት ዝግጅቱ የተሰረዘበት ምክንያት አዘጋጆቹ በተቆረጠለት እለት ጭቅጭቅ በመፍጠራቸው እና የአለመገባባት መንፈሳቸው የበላቴናውን ልዩ ዝግጅት እንዲቋረጥ ተገዷል ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላም በኩል ሰሞኑን ለቴዲ አፍሮ የተሰጠው እና የተሰየመው የሽለማት ስያሜ ከእርሱ ጋር አይሄድም የሚሉ መከራከሪያዎች ከመላው አለም ሲሰራጭ ተሰምቶአል ።
የሎሬ ነት ማእረግ እንዲህ ቀላል አይደለም የሽልማት ዝግጅት ክፍሉ አንስቶ የሰየመው ብዙ አይነት መስፈርቶች መሟላት አለበት በዚያም ላይ ደርጅቱ ሎሬት ብሎ ሲሰይም ምን ያህል አለም አቀፍ ተቀባይነት እና ሀይል ኖሮት ነው ፣በምንስ አይነት መሰፈርት የሚያሟላው ነገርቢኖር ነው የሚሉ እና ሌሎችም ጭብጥ ሀሳቦችን ይዟል፣ ዝርዝሩ መረጃው ይቀጥላል።።
Average Rating