www.maledatimes.com የቴዲ አፍሮን የሲዲ ምረቃ እንዳይካሄድ ያገደው የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መሆኑ ታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የቴዲ አፍሮን የሲዲ ምረቃ እንዳይካሄድ ያገደው የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መሆኑ ታወቀ

By   /   September 4, 2017  /   Comments Off on የቴዲ አፍሮን የሲዲ ምረቃ እንዳይካሄድ ያገደው የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መሆኑ ታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 19 Second

ይልቅ ወሬ ልንገርህ

በታምራት ሀይሉ

በትላንትናው እለት ሊካሄድ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረው የተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ የሲዲ ምረቃ ፕሮግራም ሊካሄድ ያልቻለው በአዘጋጁ ጆርካ ኤቨንት በኩል መቅረብ የነበረበት የእውቅና/ፍቃድ ወረቀት ባለማቅረቡ እንደሆነ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ም/ኮምሽነር ሽመልስ ሽፈራው ዛሬ ለቁም ነገር መጽሄት ተናግረዋል።
ባለፈው ሀሙስ ጠዋት የፖሊስን ድጋፍ የሚጠይቅ ደብዳቤ የጆርካ ኤቨንት ሰዎች ይዘው መምጣታቸው የጠቀሱት ሀላፊው ከፕሮግራሙ ይዘትና ትኩረት አንፃር የእውቅና ወረቀት ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት እንዲያመጡ ቢነገራቸውም ለሲዲ ምረቃ ፍቃድ አያስፈልግም በሚል ሀሳቡን እንዳልተቀበሉትና አዛዡን ለማነጋገር እንደሚፈልጉ ሲጠይቁ ስብሰባ ላይ በመሆናቸው እንዲጠብቁ ተነግሮአቸው እስከ ቀኑ 6 ሰአት ድረስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መጠበቃቸውን ተነግረዋል።
አዛዡ ከስብሰባ ሲወጡ ከ6 ሰአት እስከ ቀኑ 8 ሰአት ድረስ ፈቃድ ያስፈልጋል አያስፈልግም በሚል አለመግባባት የተከሰተ ሲሆን ፈቃዱን በጊዜ ካላመጡ የፖሊስ ሀይል እንደማይመደብና ሀላፊነቱን የሚወስድ አካል በሌለበት ሁኔታ ዝግጅቱን ለማካሄድ እንደማይቻል እንደተገለጸላቸው የተናገሩት ሀላፊው የሲዲ ምረቃ ፈቃድ እንደማያስፈልው በያዙት አቋም በመጽናት ከበላይ አካል ስልክ በማስደወል እንዲፈቀድ እንደሚያስደርጉ ተናግረው መሄዳቸውን ሀላፊው ተናገረዋል።

ከሀሙስ እስከ ቅዳሜ ድረስ ሲጠበቁ ምንም አይነት ፈቃድ ሳያመጡ ቀዳሜ ምሽት የሙዚቃ መሳሪያዎችን ጭነው በመምጣት ለማውረድ መሞከራቸውን የገለጹት ሀላፊው በፖሊሶች መከልከላቸውን አምነዋል።
ያም ሆኖ ለሲዲ ምረቃ ፈቃድ የሚያስጠይቅ ህግ ስለመኖሩ የተጠየቁት ሀላፊው ለማንኛውም የሙዚቃ ዝግጅትና ቁጥራቸው ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የሚገኙበት ፕሮግራምን ለማካሄድ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው ይንንም ጆርካ ኤቨንቶች ከዚህ ቀደም ኮንሰርት አዘጋጅተው ስለነበር ግትርነት ካልሆነ በቀር እንደሚያውቁት ተናገዋል።
አልበሙን ያሳተመው የጆይ ኢቨንት ፖርትነር አቶ ሰማው በበኩሉ ዝግጅቱን ለማካሄድ ከሂልተን ሆቴል ጋር ውል የፈፀመው ጆርካ ኤቨንት እንደሆነ ገልፆ የፈቃድ ጉዳይን በተመለከተ በጊዜ እንዲጨርሱ እንደተነገሯቸው ገልጸዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ አስተያየታቸውን ለማካተት የጆርካ ኤቨንት አባል አቶ ሙሴን በስልክ አግኝተን ብንጠይቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ቀጣይ ውይይቶች በአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ላይ ይቀርባል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar