0
0
Read Time:34 Second
ምንጭ (ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ አምባገነኑ የሕወሓት መራሹ መንግስት በቴዲ አፍሮ ላይ በተደጋጋሚ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አወገዘ::
“ገዥው አካል ለቴዲ አፍሮ የሚያቀርበውን ትርዒት በተደጋጋሚ በመሰረዙ ተገቢ ያልሆነ እና ኢፍትሃዊ ውሳኔ ነው” ያለው ጀዋር በቴዲ ላይ መንግስት የሚወስደው ክልከላ “ይህ ሁሉ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና ዒላማው የኪነጥበብ ጥቃትን ስለሚያካትት ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል” ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል::
ይህ የመንግስት ኪነጠብን የማፈን ተግባር አዲስ ነገር አይደለም ያለው ጀዋር “መንግስት ከማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል የበለጠ ስነ-ጥበብ እና አርቲስቶችን ይፈራል::” ካለ በኋላ ሥርዓቱ በኦሮሞ አርቲስቶች ላይም ከስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የወሰደውን ጥቃት ጠቅሷል::
እንደጀዋር ገለጻ ሕወሓት መራሹ መንግስት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ የኦሮሞ አርቲስቶችን ገድሏል፣ አስሯል እና ከሃገር እንዲሰደዱ አድርጓል::
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating