መንግስት ግን በሽታው ኮሌሯ ብሎ የጠሩ ዜጎች እንደ ወንጀሎኞች ይመለከታቸዎል !!! ———————————————————
የኮሌሯው ወረርሽን በወልቃይት ሕሞራ በኣዲ ጎሹ በመዘጋ በጸለምት ቆላማ ወረዳዎች ፣ በባድመ ፣በሸራሮ ፣ በሰዬምት ኣድያቦ ፣ በእስገደ ፣ በጽንብላ ፣ በታሕታይ ቆራሮ ፣ በዛና ፣ በመደባይ ፣ በሰለክለካ ፣ወረዳዎች እንዲሁም የሽሬ ኣውራጃ ኩቷ ገጠም የሆኑ የኣክሱም ኣውራጃ ወረዳዎች በሽታው ተስፋፍታል ። በኮሌራው የተለከፉ ወገኖች በጣም በርከት ያሉ የሞቱ ሲሆን ፣ኣብዛኞቹ ህመምተኞች ግን በጤና ጣቢያውች የተሰጣቸው ህቡእ ማረፍያ ቦታ የተመቻቸ ማረፍያ የላቸውም ፣ በሽተኞች በተሰበሰቡበት ዝቅተኛ ነርሶች ካልሆኑ ከፍተኛ ሃኪሞች ኣታዩም ። ፡
በዚሁ በወረርሽኑ የተጠቁ ወረዳዎች ንጹህ የሚጠጣ ውሃ የሚባል የለም ። ኣርሶ ኣደሩ ፣ወርቂ ለቃሚው ከወንዝ ጎርፍ ያመጣለት የደፈረሰ ውሃ ነው የሚጋተው ያለው ። እነዛ በዬመንደሩ የውሃ ፓንፕ በመትከል የህዝብ የንጹህ የውሃ ኣገልግሎት ሰጥተናል እያሉ የሚጎረኑባቸው የውሃ ጉድጓዶች ጥቂቶች ካልሆኑ በስተቀር፡ ኣብዛኞቹ ሳይሰሩ የጠፉ ናቸው ። ከላይ የዘረዘርኩት መረጃ የመንግስት ይሁኑ የህወሓት ኢህኣደግ ፓርቲዎች ፣ተለብዝን ፣ሬድዮ ጣቢያዎች ፣ ኤፍ ኤሞች ፣ ጋዜጦች እስከኣሁን ትንፍሽ ኣላሉም ። የግል ፕሬሶቹም ምንም የተነፈሱት የለም ። ታድያ ይህ ህዝብ ማን ይድረስለት ?????
ከኣስገደ ገብረስላሴ ሰለክለካ ፣ 29 / 12 / 2009
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating