www.maledatimes.com የኬንያ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ውሳኔ አሳለፈ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኬንያ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

By   /   September 17, 2017  /   Comments Off on የኬንያ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 1 Second

 

BBN news
የኬንያን ድንበር ህጋዊ ባልሆነ ሁኔታ ጥሳችሁ ገብታችኋል በተባሉ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በቁጥር 67 የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ኬንያ በህ ወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን መዘገባችን ይታወቃል፡፡ ስደተኞቹ ትላንት በአንድ የኬንያ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ከመካከላቸው 40 የሚሆኑት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ 27ቱ ስደተኞች ደግሞ የሀገሪቱን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ ጥሰው አለመግባታቸውን እና ህጋዊ ሰነድ እንዳላቸው በመናገራቸው፣ ፍርድ ቤቱ ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት አርባዎቹ ስደተኞች 800 ሺህ የኬንያ ሺሊንግ እንዲከፍሉ እና አንድ ወር እንዲታሰሩ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲያሳልፍ፣ ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲያቀልላቸው ተማጽነዋል፡፡ ስደተኞቹ፣ ፍርድ ቤቱ የበየነባቸውን ገንዘብ የመክፈል አቅም እንደሌላቸው እና ስራ አጥ መሆናቸውን በእንባ ጭምር መግለጸቸውን ተከትሎ፣ ፍርድ ቤቱ የገንዘብ ቅጣቱን ወደ 20 ሺህ ሺሊንግ ዝቅ አድርጎላቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት እያንዳንዳቸው ሃያ ሺህ የኬንያ ሺሊንግ ከፍለው ለአንድ ወር እንዲታሰሩ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ የእስር ጊዜያቸውን ሲጨርሱም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግ ተነግሯቸዋል፡፡

በሌላ በኩል 27ቱ ስደተኞች ወደ ኬንያ የገቡት ህጋዊ ስርዓቱን ጠብቀው እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በሚውሉበት ወቅት ፖሊስ የጉዞ ሰነዳቸውን ጨምሮ ገንዘብ እንደወሰደባቸው ለፍርድ ቤቱ በመናገራቸው፣ የእነሱን ጉዳይ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለአስራ አምስት ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በአንድ መኖሩያ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ሳለ ሲሆን፣ ወደ ኬንያ የገቡትም ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓጓዝ ሲሉ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on September 17, 2017
  • By:
  • Last Modified: September 17, 2017 @ 12:27 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar